የወልቂጤ ከተማ የቡድን አባላት የአንድ ወር ደሞዝ ላለመቀበል ወስነዋል

በአስገዳጁ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መነሻ እረፍት ላይ የሚገኙት የወልቂጤ ከተማ ቡድን አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ላለመቀበል ወስነዋል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በመጀመሪያ የሊጉ ተሳትፏቸው ውድድር እስከተቋረጠበት ጊዜ መልካም የሚባል የውድድር ጊዜን እያሳለፉ የነበሩት የወልቂጤ ከተማ ቡድን አባላት በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በክለባቸው ላይ ሊፈጠር የሚችለውን የፋይናንስ ጫና ለመቀነስ በማሰብ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ከክለባቸው ላለመቀበል መወሰናቸው ተሰምቷል። የቡድኑ አባላት ከዚህ ቀደም ከወር ደሞዛቸው ላይ ተቀናሽ በማድረግ በሽታውን ለመዋጋት ለሚደረገው ጥረት ለጉራጌ ዞን አስተዳደር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ጠንካራ የፋይናንስ መሠረት ላይ የሚገኙ የዓለማችን ክለቦች ጭምር እያራደ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያስከትለውን የፋይናንስ ጫና ለመመከት በደካማ የፋይናንስ መሠረት ላይ የሚገኙት ሀገራችን ክለቦችን ይህን ጊዜ እንዴት ይወጡታል የሚለው ጉዳይ ትኩረት የሚስብ ሆኗል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ