የቀድሞ ተጫዋች እና አሰልጣኝ አረፉ

ቀድሞ ተጫዋች እና አሰልጣኝ፤ እንዲሁም የወቅቱ የአዲስ አበባ እግርኳስ አሰልጣኞች ማኀበር ፕሬዝደንት አስናቀ ደምሴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ለረጅም ዓመታት በኢትዮጵያ እግርኳስ ውስጥ በተጫዋችነት በአሰልጣኝነት ሲያገለግሉ የቆዩትና በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የአሰልጣኞች ማኅበር ፕሬዝደንት ሆነው እየሰሩ የነበሩት አሰልጣኝ አስናቀ ደምሴ በድንገተኛ ህመም በዻውሎስ ሆስፒታል ህክምና ሲከታተሉ ቢቆዩም በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አሰልጣኝ አስናቀ ደምሴ በእርሻ ሠብል፣ ኪራይ ቤት እና በሌሎች ክለቦች ከመጫወታቸው ባሻገር የኪራይ ቤት አሰልጣኝ በመሆን አገልግለዋል።

ሶከር ኢትዮጵያ በአሰልጣኝ አስናቀ ደምሴ ህልፈት የተማትን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀች ለቤተሰቦቻቸው፣ ለባልደረቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናትን ትመኛለች።


© ሶከር ኢትዮጵያ