የሴካፋ ውድድር ሙሉ መርሐ-ግብር

በሀገራችን የሚካሄደው የሴካፋ ውድድር ሙሉ መርሐ-ግብርን እንደሚከተለው አዘጋጅተነዋል።

41ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከሦስት ቀናት በኋላ በባህር ዳር ከተማ መደረግ ይጀምራል። በውድድሩ ላይ ስምንት የቀጠናው እና አንድ ተጋባዥ ሀገር ተሳታፊ እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን የእጣ ማውጣት መርሐ-ግብሩም በበይነ መረብ አማካኝነት በትናንትናው ዕለት ተከናውኗል። በዚህም ዘጠኙ ብሔራዊ ቡድኖች በሦስት ምድብ ተከፋፍለዋል። አሁን ደግሞ በአዲስ መልክ የውድድሩ ሙሉ መርሐ-ግብር ከቀን እና ሰዓቱ ጋር ወጥቷል። እኛም አንባቢዮቻችን የውድድሩን ቀን እና ሰዓት እንዲያውቁት መርሐ-ግብሩን እንደሚከተለው አስቀምጠነዋል።

ሐምሌ 11 (እሁድ)

ጨዋታ 1 – ዩጋንዳ ከ ዲ.ሪ. ኮንጎ (8:00)
ጨዋታ 2 – ኢትዮጵያ ከ ኤርትራ (10:00)

ሐምሌ 12 (ሰኞ)

ጨዋታ 3 – ጂቡቲ ከ ኬንያ (10:00)

ሐምሌ 14 (ረቡዕ)

ጨዋታ 4 – ቡሩንዲ ከ ኤርትራ (10:00)

ሐምሌ 15 (ሀሙስ)

ጨዋታ 5 – ደቡብ ሱዳን ከ ኬንያ (8:00)
ጨዋታ 6 – ታንዛኒያ ከ ዲ.ሪ. ኮንጎ (10:00)

ሐምሌ 17 (ቅዳሜ)

ጨዋታ 7 – ኢትዮጵያ ከ ቡሩንዲ (10:00)

ሐምሌ 18 (እሁድ)

ጨዋታ 8 – ጂቡቲ ከ ደቡብ ሱዳን (8:00)
ጨዋታ 9 – ዩጋንዳ ከ ታንዛኒያ (10:00)

ሐምሌ 20 (ማክሰኞ) ደረጃ ለመለየት የሚደረጉ ጨዋታዎች

ጨዋታ 10 – 5ኛ የወጣው ቡድን ከ8ኛ ከወጣው ቡድን (8:00)
ጨዋታ 11 – 6ኛ የወጣው ቡድን ከ7ኛ ከወጣው ቡድን (10:00)

ሐምሌ 21 (ረቡዕ) የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች

ጨዋታ 12 – የምድብ 1 አሸናፊ ከምርጥ 2ኛ ቡድን
ጨዋታ 13 – የምድብ 2 አሸናፊ ከምድብ 3 አሸናፊ

ሐምሌ 23 (ዓርብ) ደረጃ ለመለየት የሚደረጉ ጨዋታዎች

ጨዋታ 14 – (7ኛ እና 8ኛ ቦታን ለመያዝ) የጨዋታ 10 ተሸናፊ ከጨዋታ 11 ተሸናፊ (8:00)
ጨዋታ 15 – (5ኛ እና 6ኛ ቦታን ለመያዝ) የጨዋታ 10 አሸናፊ ከጨዋታ 11 አሸናፊ (10:00)

ሐምሌ 24 (ቅዳሜ) የደረጃ እና የፍፃሜ ጨዋታዎች

ጨዋታ 16 – (3ኛ እና 4ኛ ቦታን ለመያዝ) የጨዋታ 12 ተሸናፊ ከጨዋታ 13 ተሸናፊ (8:00)
ጨዋታ 17 – (የፍፃሜ) የጨዋታ 12 አሸናፊ ከጨዋታ 13 አሸናፊ (10:00)

ጠቃሚ መረጃዎች

* በውድድሩ 17 ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
* የምድባቸው አንደኛ የሆኑ ሦስት ሀገራት በቀጥታ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ፍልሚያ ያላፋሉ።
* ከሦስቱ ምድቦች አንድ ምርጥ ሁለተኛ ቡድን ግማሽ ፍፃሜውን ይቀላቀላል።
* ሁሉም ጨዋታዎች 8 እና 10 ሰዓት ይደረጋሉ።
* አንድ ቡድን አራት ጨዋታዎችን (ሁለት የምድብ፣ አንድ የግማሽ ፍፃሜ እንዲሁም አንድ የፍፃሜ) አሸንፎ ዋንጫውን ሊያነሳ ይችላል።
* የውድድሩ ጨዋታዎች በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃሉ።
* የሁሉንም የውድድሩ ተሳታፊ ሀገራት ደረጃ ለመለየት የደረጃ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
* ሁሉም ጨዋታዎች በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ይደረጋል።