የግራ መስመር ተከላካዩ ለአዳማ ከተማ ፈረመ

የግራ መስመር ተከላካዩ ሀዋሳ ከተማን ለቆ ማረፊያው አዳማ ከተማ ሆኗል፡፡

በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ከሳምንታት በፊት ያስፈረመው እና በዛሬው ዕለት የጀማል ጣሰው፣ የምንተስኖት አዳነ እና ዮሴፍ ዮሐንስን ዝውውር የፈፀመው አዳማ ከተማ አሁን ደግሞ የግራ መስመር ተከላካዩ ደስታ ዮሐንስ (አባትን) በሁለት ዓመት ውል ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

በሀዋሳ ከተማ የተስፋ ቡድን የክለብ ህይወቱን የጀመረውና ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኃላ ከ2007 ጀምሮ በመሐል ወደ መከላከያ ካመራበት ጥቂት ወራት በቀር በወጥነት ክለቡን በግራ መስመር ተከላካይነት ያገለገለው ደስታ ከስድስት ዓመታት የክለብ ቆይታው በኋላ ሀዋሳ ከተማን ለቋል። ደስታ ከተለያዩ ሶስት ክለቦች ጋር ስሙ ቢያያዝም ማረፊያው አዳማ ከተማ መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡

ደስታ በትናንትናው ዕለት ይፋ በተደረገው የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የዋልያዎቹ ስብስብ ጥሪ እንደተደረገለት ይታወሳል፡፡