ዋልያዎቹ በወርሀዊ የሀገራት ደረጃ ባሉበት ተቀምጠዋል

የፊፋ ወርሀዊ የሀገራት ደረጃ ዛሬ ይፋ ሲሆን የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን የተቀመጠበት ደረጃም ታውቋል።

በዚህ ወር በፊፋ እውቅና እንደተሰጠው በተነገረው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ውድድር ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ137ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ይህም ባለፈው ወር ከነበረበት ደረጃ ጋር ተመሳሳይ ነው። ቡድኑ ከአፍሪካ ሀገራት ደግሞ በ39ኙ ተበልጦ 40ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ቤልጅየም አሁንም የሰንጠረዡ አናት ላይ መቀመጥ ስትችል ብራዚል እና ፈረንሳይ ቀጣዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።

ያጋሩ