አዳነ ግርማ ወደ ቀድሞ ቤቱ ተመልሷል

በቅዱስ ጊዮርጊስ በርካታ ታሪኮችን የፃፈው አዳነ ግርማ በአዲስ ሀላፊነት ክለቡን ዳግም መቀላቀሉ ታውቋል።

ከ2000-2010 ድረስ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት በርካታ ዋንጫዎችን በተጫዋችነት ያገኘው አዳነ ግርማ 2012 ላይ እግርኳስ መጫወት በቃኝ ካለ በኋላ ወደ ስልጠናው ዓለም ለመግባት እንቅስቃሴ ላይ ይገኝ ነበር። አዳነ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የባህር ዳር ከተማ ምክትል አሠልጣኝ ይሆናል የሚል ወሬ ቢሰማበትም ዛሬ ዳግም ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት በቡድን መሪነት መሾሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።