ለተጫዋቾች ጥሪ ያደረጉት ሉሲዎቹ ዝግጅት ሊጀምሩ ነው

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ሊጀምሩ ነው።

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ከፊቱ ጨዋታ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ሊጀምር መሆኑን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል። በዚህም የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ለዩጋንዳው ጨዋታ ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ በካፍ የልህቀት ማዕከል ዝግጅታቸውን ሊጀምሩ መሆኑ ታውቋል። አሠልጣኙ ጥሪ ያቀረቡላቸው ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው።

ግብ ጠባቂዎች

ታሪኳ በርጋና – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ንግስቲ መዓዛ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ቤተልሄም ዮሐንስ – አዲስ አበባ
እምውድሽ ይርጋሸዋ – አዳማ ከተማ
ዓባይነሽ ኤርቄሎ – መከላከያ

ተከላካዮች

ቅድስት ዘለቀ – ሀዋሳ ከተማ
መንደሪን ክንድይሁን – ሀዋሳ ከተማ
መስከረም ካንኮ – መከላከያ
ቤተልሄም በቀለ – መከላከያ
እፀገነት ብዙነህ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ዓለምነሽ ገረመው – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ትዝታ ኃይለሚካኤል – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሀሰቤ ሙሶ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ብዙአየሁ ታደሰ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ናርዶስ ጌትነት – አዳማ ከተማ
ሊዲያ ጌትነት – ባህር ዳር ከተማ
ሠናይት ሰጎ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

አማካዮች

ኤደን ሽፈራው – መከላከያ
የውብዳር መስፍን – አዲስ አበባ ከተማ
እመቤት አዲሱ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ህይወት ደንጌሶ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አረጋሽ ካልሳ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሰናይት ቦጋለ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ብርቱካን ገብረክርስቶስ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ትዕግስት ያደታ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ቤዛዊት ተስፋዬ – መከላከያ
ሲሳይ ገብረዋህድ – ሀዋሳ ከተማ
መሳይ ተመስገን – መከላከያ

አጥቂዎች

ረድዔት አስረሳኸኝ – ሀዋሳ ከተማ
ሴናፍ ዋቁማ – መከላከያ
ሥራ ይርዳው – መከላከያ
ሣራ ነፍሶ – ሀዋሳ ከተማ
መዲና ዓወል – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሎዛ አበራ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ጥሪ የቀረበላቸው ተጫዋቾች ከነገ በስትያ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉም ተመላክቷል።