ጅማ አባጅፋር ወጣቱን ተጫዋች አስፈርመዋል

በአሠልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመሩት ጅማ አባጅፋሮች በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በቅዱስ ጊዮርጊስ ያሳለፈውን ተጫዋች የግላቸው አድርገዋል።

ወጣት እና አንጋፋ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው በመቀላቀል ጥቅምት 8 የሚጀመረውን የ2014 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እየተጠባበቁ የሚገኙት ጅማ አባጅፋሮች አዲስ አማካይ ማግኘታቸው ታውቋል። ቡድኑን በሁለት ዓመት ውል የተቀላቀለው ተጫዋቾችም የአብስራ ሙሉጌታ ነው።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ የታዳጊ ቡድን የተገኘው የአብስራ ምንም እንኳን ዋና ቡድኑን በወጥነት ባያገለግልም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በጥቂት ጨዋታዎች ላይ የመጫወት ዕድል ያገኘ ሲሆን በሌላኛው የሊጉ ክለብ በሀገሪቱ ከፍተኛ የሊግ እርከን ለመጫወት ጅማ አባጅፋርን መቀላቀሉ ታውቋል።

ያጋሩ