አዳማ ከተማ የግብ ጠባቂውን ውል አድሷል

ከደቂቃዎች በፊት ተከላካይ ያስፈረመው አዳማ ከተማ የጊኒያዊውን የግብ ዘብ ውል ለአንድ ዓመት አራዝሟል።

ጥቅምት 8 ለሚጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አሠልጣኝ በመሾም እንቅስቃሴ የጀመረው አዳማ ከተማ በርካታ ተጫዋቾችን እያስፈረመ እንደሆነ ይታወቃል። ከአዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪም የወሳኝ ነባር ተጫዋቾችን ውል በማደስ ላይ የሚገኘው ክለቡ የቁመታሙን ግብ ጠባቂ ሴኩባ ካማራን ውል ለተጨማሪ ዓመት ማራዘሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረ28ለች።

በውድድር ዘመኑ አጋማሽ አዳማን የተቀላቀለው የግብ ዘቡ ካማራ ከዚህ ቀደም ለጊኒው አትሌቲኮ ዴ ኮናክሪ እና ኤ ኤስ ካሉም እንዲሁም ለእስራኤሉ ሃፖኤል ራና ተጫውቶ አሳልፏል። አሁን ደግሞ በአዳማ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለመቆየት በይፋ ፊርማውን አኑሯል።

ያጋሩ