ሀምበሪቾ ዱራሜ የአሰልጣኝ ቅጥር ፈፅሟል

በቅርቡ ከዋና አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ጋር የተለያዩት ሀምበሪቾዎች የአሰልጣኝ ቅጥር ፈፅመዋል።

ከአሰልጣኝ ግርማ የተለያየው ሀምበሪቾ አሰልጣኝ ዳዊት ሀብታሙን ዋና አሰልጣኝ አድርገው መምረጣቸው ታውቋል። በ2013 ውድድር ዓመት በወላይታ ድቻ በምክትልነት ሲገለግል የነበረው ወጣቱ አሰልጣኝ ዳዊት ሀብታሙ በአዳማ ተስፋ ቡድን የአሰልጣኝነት ህይወቱን ጀምሮ በለገጣፎ ለገዳዲ ከረዳት አሰልጣኝነት እስከ ዋና አሰልጣኝነት ሰርቷል። አሰልጣኙ በከፍተኛ ሊግ ቆይታው ለገጣፎ በተከታታይ ዓመት ጠንካራ ቡድን በመስራት ቡድኑን ተፎካካሪ ሲያደርጉት ቆይተዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በወላይታ ድቻ በምክትል አሰልጣኝነት የቆየው ዳዊት ሀብታሙ በቀጣይ የሀምበሪቾ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ የምንመለከተው ይሆናል።

ያጋሩ