ፍቅሩ ተፈራ ወደ ህንዱ አትሌቲኮ ካልካታ ሊያመራ ይችላል

የህንዱ ክለብ አትሌቲኮ ካልካታ የቀድሞውን የአዳማ ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ፍቅሩ ተፈራ ሊያስፈርም እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።

አትሌቲኮ ካልካታ በህንድ ባለሃብቶች እና በስፔኑ ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ ጥምረት በካልካታ ከተማ የተመሰረተ ክለብ ነው። በክለቡ የሚጫወቱ የውጪ ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾችን የሚያስፈርምለት አትሌቲኮ ማድሪድ ሲሆን ፍቅሩ ተፈራም ለአንድ ወር የሙከራ ጊዜ ወደ ስፔን የሚጓዝ ይሆናል።

በአዲስ መልኩ የተመሰረተው የህንድ ሱፐርሊግ የመጀመሪያ የውድድር ዘመኑን በሚቀጥለው ዓመት የሚያደርግ ይሆናል። በሊጉ ህግ መሠረት እያንዳንዱ ክለብ ስምንት የውጪ ሀገር ተጫዋቾችን ማስፈረም የሚችል ሲሆን ከነዚህ ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነ ተጫዋች (marquee signing) መሆን ይኖርበታል። ፍቅሩ ተፈራ የሙከራ ጊዜውን በስኬት ካጠናቀቀም ከቀድሞው የባርሴሎና እና ሊቨርፑል ኮከብ ሉዊስ ጋርሺያ ጋር የመጫወት ዕድል ያገኛል።

ያጋሩ