ዝውውር ፡ መሃመድ ናስር ወደ መድን ተመለሰ

አምና የኢትዮጵያ መድን ከፍተኛ ግብ አግቢ የነበረው መሃመድ ናስር ከ6 ወራት የሱዳን ቆይታ በኋላ ወደ መድን ተመልሷል፡፡

በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር ኢትዮጵያ መድንን ለቆ ለአልአህሊ ሼንዲ በ800ሺህ ብር ሂሳብ የፈረመው መሃመድ በሱዳኑ ክለብ ያልተሳኩ 6 ወራትን አሳልፎ በ300ሺህ ብር ሰማያዊዎቹን ተቀላቅሏል፡፡

ከፍተኛ የአጥቂ እጥረት ያለበት የአስራት ኃይሌው መድን በሊጉ ባለፉት 5 አመታት ከታዩ ድንቅ አጥቂዎች አንዱ የሆነውን መሃመድ በእጁ ማስገባቱ በሁለተኛው ዙር ከሊጉ ላለመውረድ ለሚያደርገው ትግል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያድግለታል ተብሎ ይታመናል፡፡

ከጅማ ከነማ የሚነሳው የመሃመድ ናስር የእግርኳስ ህይወት በኒያላ አድርጎ መከላከያ ፣ መብራት ኃይል ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና አህሊሼንዲን አዳርሷል፡፡ አሁን መድንን እያሰለጠኑ የሚገኙት አስራት ኃይሌም በመሃመድ ናስር የእግርኳስ ህይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ አላቸው፡፡በመከላከያ ወደ ተስፈኛ አጥቂነት በመብራት ኃይል ደግሞ ደረጃውን ወደጠበቀ አጥቂነት አሸጋግረውታል፡፡ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ካሳለፈፈው አስቸጋሪ ጊዜ በኋላ ደግሞ በድጋሚ በመድን ነፍስ እንዲዘራ አድርገውታል፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ