ዳንኤል መስፍን

የደቡብ ሱዳኑ ክለብ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ እንደማይሳተፍ ሲታወቅ በምትኩ አንድ የፕሪምየር ሊግ ክለብ መግባቱ ተረጋግጧል። በሁለት ምድብ ተከፍሎ ከመስከረም 15-30 ድረስ በሚካሄደው የመዲናዋ ትልቅ ውድድር ላይ በተጋባዥነት እንደሚካፈል በፌዴሬሽኑ በኩል ማረጋገጫ ተሰጥቶት የቆየው ሙኑኪ ኤፍ ሲ በምድብ ሀ መደልደሉ ይታወሳል። አሁን ባገኘነው መረጃ መሠረት በአዲስ አበባ በሚኖረው ቆይታ ለሆቴልዝርዝር

ባለፈው የውድድር ዓመት ወጥ የሆነ አምበል ያልነበረው አዳማ ከተማ ለአዲስ የውድድር ዓመት ሦስት አንበሎችን መርጧል። በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በመመራት ለ2014 የውድድር ዘመን በአዳዲስ ተጫዋቾች ብቅ የሚለው አዳማ ከተማ ቡድኑን በአንበልነት የሚመሩ ሦስት ተጫዋቾችን መምረጣቸው ታውቋል። በበርካታ ክለቦች እና በብሔራዊ ቡድን በመጫወት ከፍተኛ ልምድ ያለው ግብጠባቂው ጀማል ጣስው በአዳማም ተመራጭ አንበልዝርዝር

በኮፌዴሬሽን ካፕ የመልስ ጨዋታ ዩአርኤን የሚገጥመው ኢትዮጵያ ቡና አቡበከርን ያልተጠቀመበት ምክንያት ምን ይሆን ? ኢትዮጵያ ቡና የዛሬ ሳምንት ዩጋንድ አቅንቶ በዩአርኤ በጠባብ ውጤት 2-1 ተሸንፎ መመለሱ ይታወሳል። ውጤቱን የመቀልበስ ግዴታ ውስጥ በመግባት በባህር ዳር የመልሱን ጨዋታ የሚያደርገው ኢትዮጵያ ቡና በአሰላለፉ ውስጥ አቡበከርን እንደማይጠቀም ተረጋግጧል። በተጠባባቂ ወንበር ላይ የምንመለከተውም ይሆኗል። ባልተለመደዝርዝር

በስምንት ቡድኖች መካከል የሚካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫን አስመልክቶ የምድብ ድልድል ይፋ የማድረግ እና ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠበት መድረክ ዛሬ ከሰዓት ተካሂዷል። በቤስት ዌስተርን ሆቴል በተካሄደው የምድብ ድልድል የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ አስተባባሪ ዣንጥረር ዓባይ፣ የስፖርት ኮሚሽን ከሚሽነር በላይ ደጀን፣ የአዲስ አበባ እግርኳስዝርዝር

በሁለትም ምድብ ተከፍሎ የሚካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ድልድል በቤስት ዌስተርን ሆቴል ይፋ ሆኗል። አስራ አምስተኛ የውድድር ዓመቱን ያስቆጠረው የመዲናዋ ትልቁ ውድድር የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ስምንት ክለቦችን በማሳተፍ ከመስከረም 15-30 ድረስ የሚከናወን ይሆናል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስ አገልግሎት ሰጪ አስተባባሪ ዣንጥረር አባይ የስፖርት ኮሚሽን ከሚሽነር አቶ በላይ ደጀንዝርዝር

ከመስከርም አጋማሽ ጀምሮ በሚካሄደው የመዲናዋ ትልቁ ዋንጫ ላይ ወልቂጤ ከተማ ከውድድሩ ውጭ በመሆኑ በምትኩ አንድ አዲስ ቡድን ተሳታፊ ይሆናል። ለ15ኛ ጊዜ የሚዘጋጀው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር ከመስከረም አስራ አምስት ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት ስምንት ቡድኖችን በማሳተፍ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚደረግ ይታወቃል። ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ አዲስ አበባ ከተማ፣ መከላከያ፣ አዳማዝርዝር

የከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ በበላይነት በማጠናቀቅ ወደ ፕሪምየር የሊግ የተቀላቀለው አዲስ አበባ ከተማ በመዲናው መስተዳደር ሽልማት ተበርክቶለታል። በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል በተካሄደው የዕውቅና ምሽት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የአአ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሺነር በላይ ደጀን እና የካቢኔ አባላት ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት መርሐግብሩ ተካሄዷል። የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግዝርዝር

በትናትናው ዘገባችን ከሲዳማ ቡና ጋር ድርድር መጀመሩን ዘግበን የነበርነው ጌታነህ ከቀድሞ አሰልጣኙ ክለብ ጋር ልምምድ መጀመሩ ታውቋል። ቀሪ የአንድ ዓመት ኮንትራት እያለው ፈረሰኞቹ ጋር የመለያየቱ ነገር እርግጥ የሆነው የዋልያዎቹ አንበል ጌታነህ ከበደ ቀጣይ ማረፊያው የት ይሆናል በሚል በትናትናው ምሽት ዘገባችን ለጊዜው ከስምምነት አይድረሱ እንጂ ከሲዳማ ቡና አመራሮች ጋር መነጋገሩን ገልፀንዝርዝር

ከፈረሰኞቹ ጋር የመለያየቱ ነገር እርግጥ የሆነው የዋልያዎቹ አንበል ጌታነህ ከበደ ቀጣይ ማረፊያው የት ይሆናል? በሚሌንየሙ መጀመርያ በደቡብ ፖሊስ ከእግርኳስ ቤተሰብ ጋር የተዋወቀው ጌታነህ ከደደቢት ጋር የሊጉን ዋንጫ በማንሳት ለአምስት ዓመታት ተጫውቶ አሳልፏል። በማስከተል ወደ ቢድቬትስ ዊትስ አምርቶ ለሦስት ዓመታት በደቡብ አፍሪካ ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ደደቢት በመመለስ ለሁለት ዓመት ቆይታዝርዝር

አዲስ አበባ ከተማ ወደ ሊጉ ማደጉን ተከትሎ ቃል የተገባለትን ሽልማት በነገው ዕለት ይረከባል። የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ’ን በበላይነት በማጠናቀቅ የሀገሪቱን ከፍተኛ የሊግ እርከን የተቀላቀለው አዲስ አበባ ከተማ በመዲናው መስተዳደር ሽልማት እንደሚበረከትለት ቃል ተገብቶ ነበር። መስተዳደሩም ዘግየት ብሎም ቢሆን ቃል የገባውን የማበረታቻ ሽልማት በነገው ዕለት እንደሚያበረክት ታውቋል። በሀዋሳ እና ወልዲያዝርዝር