Soccer Ethiopia

Archives

የዳኞች ገፅ | ባለግርማ ሞገሱ የቀድሞ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ኪነ ጥበቡ

በአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያን በመወከል ካጫወቱ ዳኞች መካከል የሚመደበው እና በሀገር ውስጥ ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸውን ጨዋታ በመዳኘትም እውቅና ያተረፈው የቀድሞ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ኪነ ጥበብ የዛሬው የዳኞች ገፅ እንግዳችን ነው። ኑሮውን በሀገረ አሜሪካ ካደረገ ዓመታት አስቆጥሯል። አልፎ አልፎ ወደ ትውልድ ሀገሩ በመምጣት ያለውን ልምድ በተለያዩ ጊዜዓት አካፍሏል። ከአስራ አምስት ዓመት በላይ በቆየው የዳኝነት ህይወቱ በሀገር ውስጥ […]

​ፌዴሬሽኑ ለሰበታ ጥያቄ ምላሽ ሰጠ

የሰበታ ከተማ ክለብ የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የኮንትራት ክፍያን አስመልክቶ ቀሪ ገንዘብ ይመለስልኝ በማለት ለፌዴሬሽኑ ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ አገኘ። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በ2012 ሰበታ ከተማን ለማሰልጠን የሁለት ዓመት የውል ኮንትራት በመፈረም ቡድኑን ለአንድ ዓመት ማሰልጠናቸው ይታወቃል። አሰልጣኝ ውበቱ የአንድ ዓመት ኮንትራት እየቀራቸው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዲያሰለጥኑ ጥሪ የቀረበላቸው መሆኑን ተከትሎ ከሰበታ ጋር በስምምነት በመለያየት በአሁኑ ወቅት […]

​ፋሲሎች ለመልሱ ጨዋታ ዝግጅታቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ

በአፍሪካ መድረክ ያላቸውን ተሳትፎ ለማስቀጠል የፊታችን እሁድ ወሳኝ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ዐፄዎቹ በአዲስ አበባ ስታዲየም ልምምዳቸውን እየሰሩ ይገኛል። በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን እያደረጉ የሚገኙት ዐፄዎቹ የፊታችን እሁድ የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን አዲስ አበባ ስታዲየም ያከናውናሉ። ባለፈው ሳምንት ወደ ሞናስቲር በማቅናት 2-0 ተረተው የተመለሱት ፋሲሎች የመልሱን ጨዋታ ለማድረግ ወደ አዲስ አበባ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ጠንካራ […]

​በወቅታዊ ሁኔታ የመሳተፉ ነገር አጠራጣሪ የነበረው ክለብ በፕሪምየር ሊጉ እንደሚሳተፍ ተረጋገጠ

የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ከዚህ ቀደም ባልነበሩ የተለያዩ በጎ ነገሮች ታግዞ የፊታችን ታኅሣሥ ሦስት ቀን በይፋ እንደሚጀመር የሊጉ አወዳዳሪ አካል ማሳወቁ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ አብዛኛው ክለቦች ቅድመ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ የውድድሩን መጀመር በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙም ይታወቃል። ሆኖም ባለው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት በተለይ ሦስቱ በትግራይ ክልል መቀመጫቸውን ያደረጉት መቐለ ሰባ እንደርታ፣ ወልዋሎ እና ስሑል ሽረ በውድድሩ የመሳተፋቸው […]

የታዳጊ ቡድኑ ለሴካፋ ዋንጫ ዝግጅቱን እያደረገ ነው

በሩዋንዳ አስተናጋጅነት በሚካሄደው ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ዋንጫ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል። ከታኅሣሥ 13-28 ጀምሮ በሩዋንዳ አስተናጋጅነት ይደረጋል ተብሎ መርሐግብር በወጣለት ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ዋንጫ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዋና አሰልጣኝ  እንድርያስ ብርሀኑ፣ በምክትልነት አሰልጣኝነት አሳምነው ገብረወልድ እና የግብጠባቂ አሰልጣኝ አዳሙ ኑመሮ እየተመራ አያት በሚገኘው የካፍ አካዳሚ ዝግጅቱን ከጀመረ ሳምንታት አስቆጥሯል። […]

ስለ በቀለ እልሁ ሊያውቋቸው የሚገቡ ዕውነታዎች

ሜዳ ውስጥ ለለበሰው መለያ ሟች ነው። ሁሉን ሳይሳሳ አውጥቶ በመስጠት፣ በአልሸነፍ ባይነቱ፣ በታጋይነቱ እና በጠንካራ ሠራተኝነቱ ይታወቃል። ጥቂት በማይባሉ ክለቦች በነበረው የእግርኳስ ሕይወቱ በአመዛኙ በቋሚነት የተጫወተው ያልተዘመረለት የዘጠናዎቹ ኮከብ በቀለ እልሁ (እልሁ) ማነው ?  በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ውስጥ በቀደመውም ሆነ በአሁኑ ዘመን በርካታ ተጫዋቾችን እያፈራች መሆኗ ብዙም በማይነገርላት ቢሸፍቱ (ደብረ ዘይት) ከተማ ነው የዛሬው ባለታሪካችን […]

​ሊግ ኩባንያው እና ዲኤስቲቪ ይፋዊ ስምምነት ሊያደርጉ ነው

በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየቱን ተከትሎ ጥያቄ ሲነሳበት የነበረው የሊግ ኩባንያው እና ዲኤስቲቪ ይፋዊ ስምምነት በዚህ ሳምንት በሸራተን ሆቴል ሊያደረግ ነው። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የ2013 የፕሪምየር ሊግ ውድድር የቀጥታ ቴሌቭዥን ስርጭት ማስተላለፍ ለሚችሉ ድርጅቶች በአወጣው ጨራ መሠረት ሱፐር ስፖርት ውድድሩን በዲ ኤስቲቪ (Dstv ) በቀጥታ ለማስተላለፍ ማሸነፉ ይታወቃል፡፡ ስምምነቱ በግልፅ አለመታወቁን ተከትሎ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲነሱ […]

​”በምንችለው አቅም ውጤቱን ለመቀልበስ እየሠራን ነው” ሱራፌል ዳኛቸው

በካፍ ኮፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመጀመርያ ጨዋታ የቱኒዚያው ሞናስቲርን ከሜዳ ውጪ ገጥሞ ሽንፈት ያስተናገደው ፋሲል ከነማ ውጤቱን ለመቀልበስ ባሉት ቀሪ ቀናት እየተዘጋጁ እንደሆነ ይታወቃል። ዐፄዎቹ  ከወራት ዝግጀት በኋላ ባደረጉት የመጀመርያ ጨዋታ ምንም እንኳን ሸንፈት አስተናግደው ቢመለሱም በነበራቸው ክፍተቶች መሻሻል ካደረጉ ውጤቱን መቀልበስ እንደሚችሉ የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች ሱራፌል ዳኛቸው ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ ተናግሯል። […]

የ20 ዓመት ብሔራዊ ቡድን ​አሰልጣኝ ተመስገን ዳና በታንዛንያ ቆይታ ዙርያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

በታንዛንያ አስተናጋጅነት በተካሄደው የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ላይ አመርቂ ያልሆነ ውጤት አስመዝግቦ የተመለሰውን ብሔራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ስለነበረው ቆይታ አሰልጣኙ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ወሎ ሠፈር በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት በዘጠኝ ሰዓት ላይ ሠላሳ ደቂቃ በቆየው አጭር ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ተመስገን ዳና በመግቢያ ንግግራቸው ይህኖ ብለዋል። ” ወደ ታንዛንያ ልንጓዝ ሰባ ሁለት […]

የዲኤስቲቪ እና የሊግ ኩባንያ የውል ስምምነት ይፋዊ በሆነ መንገድ ለመግለፅ ለምን ዘገየ?

በተለያዩ መንገዶች ከሚሰሙ መረጃዎች ውጭ ይፋዊ በሆነ መንገድ እስካሁን በዲኤስቲቪ እና የሊግ ኩባንያው መካከል የተደረሰው የውል ስምምነት ለምን ይፋ ሳይሆን ቀረ?   የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የሊጉን የቴሌቪዥን ስርጭት መብት መግዛት የሚፈልጉ ተቋማትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ DStv’ም ከተወዳዳሪዎቹ የተሻለ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ፕሮፖዛል በማቅረብ መብቱን መግዛቱ ከተሰማ ቆይቷል። ሆኖም በተለያዩ መንገዶች ከሚወጡ መረጃዎች ውጭ የስምምነቱ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top