ዳንኤል መስፍን (Page 2)

ከመከላከያ በ2012 ኢትዮጵያ ቡናን በአነስተኛ የደሞዝ ለተቀላቀለው አማካይ የወርሀዊ ደሞዝ እርከኑ ላይ ማሻሻያ ተደርጎለታል። በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የእግርኳስ ህይወቱን መነሻ በማድረግ በመከላከያ ተስፋ ቡድን እና ዋናው ቡድን መጫወት የቻለው ዊልያም ሰለሞን በ2012 ኢትዮጵያ ቡናን ለሦስት ዓመት ለማገልገል ፊርማውን ማኖሩ ይታወቃል። በጊዜው ዊልያም ከቡናማዎቹ ጋር ሲፈራረም በአነስተኛ ወርሀዊ ደሞዝ የነበረዝርዝር

ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ጅማ አባ ጅፋርን የተጫወቱት ሁለት አማካዮች ክለቡ ጋር መለያየታቸው ተሰምቷል። በ2013 በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም ይመራ በነበረው የጅማ አባ ጅፋር ስብስብ ውስጥ በውድድሩ አጋማሽ ላይ የተቀላቀሉት አማኑኤል ተሾመ እና ዋለልኝ ገብሬ ከጅማ አባጅፋሮች ጋር መለያየታቸው ታውቋል። ቀሪ የስድስት ወር ኮንትራት ያላቸው ሁለቱ አማካይ ከቡድኑ ጋር ቢሸፍቱ በመግባትዝርዝር

በቅርቡ ከቡድን መሪው ጋር የተለያየው ኢትዮጵያ ቡና በዛሬው ጨዋታ የቡድን መሪ ሚናውን ማን ይወጣለት ይሆን? በካፍ ኮፌዴሬሽን ካፕ ዛሬ አስር ሰዓት ላይ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጭ ከዩጋንዳው ዩአርኤ ጋር የሚያደርጉት ኢትዮጵያ ቡናማዎች አሰልጣኝ ካሣዬ አራጌ የካፍ መስፈርትን አለሟሟላቱን ተከትሎ ከተመልካች ጋር ቁጭ ብሎ ጨዋታውን የመከታተል ግዴታ ውስጥ ገብቷል። በዚህምዝርዝር

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የዩጋንዳው ዩ አር ኤን ለመግጠም ወደ ስፍራው ካቀኑ የቡድኑ አባል መካከል ኃይሌገብረ ትንሳኤ ስለጨዋታው ይናገራል። ኢትዮጵያ ቡና በ2003 የሊጉን ዋንጫ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ባነሱ ማግስት በአፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን በመወከል ተሳታፊ መሆናቸው ይታወሳል። ለአስር ዓመት ከመድረኩ የራቁት ቡናማዎቹ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግን 2ኛ ሆነው በማጠናቀቃቸው ዳግም አህጉራዊዝርዝር

ከ2004 በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ምድረክ ብቅ ያሉት ኢትዮጵያ ቡናዎች ከደቂቃ በፊት በሁለተኛ ምዕራፍ ወደ ዩጋንዳ ጉዞ ሲጀምሩ ጨዋታውን በግብ ጠባቂ አሰልጣኝ እየተመሩ ያደርጋሉ። ቡናማዎቹ የፊታችን እሁድ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታቸውን ከዩጋንዳው ዩ አር ኤን የሚያደርጉ ሲሆን በትናትናው ዕለት የቡድኑ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ አቅንተው ነበር። ዛሬዝርዝር

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የዩጋንዳው ዩ አር ኤን የሚገጥመው ኢትዮጵያ ቡና በቢሾፍቱ ከተማ ሲያደርግ የሰነበተውን ዝግጅት ሶከር ኢትዮጵያ እንዲህ ተመልክታዋለች። በኢትዮጵያ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ለዋንጫ ሲፎካከሩ የቆዩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በመጨረሻም ፋሲል ከነማን በመከተል ሊጉን በሁለተኝነት አጠናቀዋል። ይህንን ተከትሎም ከ2004 የአፍሪካ መድረክ ተሳትፎ በኋላ ዳግም ወደ አህጉራዊ ውድድር ብቅ ያሉትዝርዝር

ድሬዳዋ ከተማዎች ልምድ ያለውን ግብጠባቂ አስፈርመዋል። የመጀመርያ ምዕራፍ ቅድመ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተወሰኑ ቀናት ዕረፍት የሰጡት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ በዛሬው ዕለት ግብጠባቂውን ደረጄ አለሙን ለአንድ ዓመት አስፈርመዋል። ከግብጠባቂው ወንደሰን አሸናፊ ጋር በስምምነት ከተለያዩ በኋላ በቦታው ያለውን ክፍተት ለመሙላት ያሰቡት ድሬዎች ከቀናት በፊት ከቡድኑ ጋር በሀዋሳ ከተማ ሲዘጋጅ የቆየውዝርዝር

በካፍ ኮፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን የሚወክሉት ብናማዎቹ ቅድመ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ ነገ ወደ ስፍራው ያቀናሉ። በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ከዩጋንዳው ዩአርኤ ጋር የተደለደሉት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ለስድስት ሳምንታት በቢሸፍቱ ከተማ ሲዘጋጁ ቆይተዋል። የፊታችን እሁድ ከሜዳቸው ውጭ የመጀመርያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ኢትዮጵያ ቡናዎች ነገ አመሻሽ ላይ ወደ ስፍራ ሲያቀኑ ከቡድኑ የሚጓዙት 20 ተጫዋቾች ተለይተውዝርዝር

አስቀድሞ ወደ ሀድያ ሆሳዕና አምርቶ የነበረው ግብጠባቂ ለሲዳማ ቡና ፈርሟል። በአሰልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ እየተመራ መቀመጫ ከተማው በሆነችው ሀዋሳ ከተማ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው ሲዳማ ቡና ግብጠባቂውን መክብብ ደገፋን ለሁለት ዓመት አስፈርሟል። ለሀድያ ሆሳዕና መፈረሙን ከዚህ ቀደም ዘግበን የነበረው መክብብ በትናንትናው ዕለት ፌዴሬሽን በመገኘት ለሲዳማ ፊርማውን አኑሯል። ከዚህ ቀደም በሀዋሳ ከተማ፣ አዳማዝርዝር

በባቱ ከተማ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው ከየኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ውድድር በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ተሳትፎ ያደረገው አርባምንጭ ከተማ አሸናፊ ሆኗል። ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በአስራ ስድስት የከተማ እና የክልል ቡድኖች መካከል ከነሐሴ 16 ጀምሮ በባቱ ከተማ ሲካሄድ የቀ ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ፍፃኔውን አግኝቷል። ሦስት ሰዓት በጀመረው የኢትዮጵያ ቡና እናዝርዝር