ዳዊት ፀሐዬ

አጭር ዕድሜ፤ የተለየ የጨዋታ መንገድ፤ ፈጣን ዕድገት… ይህ ሁሉ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ለአንድ ተጫዋች ዝውውር ከሚያወጡት ገንዘብ ባነሰ ዓመታዊ በጀት ብዙዎችን አስደምሞ የፕሪምየር ሊግን በር አንኳክቶ የተመለሰው የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ እግርኳስ ክለብ መለያ ነው። በዚህ ፅሁፍም የክለቡን ጉዞ እና ከዚህ ግስጋሴ ጀርባ ስላለው ቁልፍ ሰው ሀሳቦችን ለማንሳት ወደናል። በኢትዮጵያ እግርኳስዝርዝር

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት የሙዚቃ ቪዲዮ ሊሰሩ እንደሆነ ይፋ ተደርጓል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን እና በደመራ ሚዲያና ኮሚውንኬሽን ትብብር የሚዘጋጀው ይህ የሙዚቃ ቪዲዮ በዋናነት በሀገራችን እየተስተዋሉ የሚገኙ ወቅታዊ ችግሮች ለመቅረፍ የእግርኳሱን በጎ ተፅዕኖ ለመጠቀም እንዲሁም በሴካፋ ውድድር ላይ ለሚሳተፉ ወጣት ተጫዋቾች በቀጣይ ሀገራቸውን ለአፍሪካ ዋንጫ እንዲያበቁ አደራ ለመስጠት እንደሆነ የፌደሬሽኑ መረጃዝርዝር

ረፋድ ላይ ስድስተኛ ተጫዋቻቸውን ያስፈረሙት ሲዳማ ቡናዎች አሁን ደግሞ ተጨማሪ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች አስፈርመዋል። አዲሱ ፈራሚ ከቀናት በፊት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የተለያየው የመሐል ተከላካዩ ምንተስኖት ከበደ ነው። ከዚህ ቀደም በደደቢት ፣ አዳማ ከተማ እና መከላከያ ተጫዋውቶ ያሳለፈው ተከላካዩ ባሳለፍነው የክረምቱ የዝውውር መስኮት እንዲሁ በወቅቱ በገብረመድኅን ኃይሌ ይመራ ወደ ነበረው መቐለዝርዝር

የኢትዮጵያ ቡና የቀኝ ተከላካይ መስመር ተጫዋች የሆነው ኃይሌ ገብረተንሳይ በኢትዮጵያ ቡና የሚያቆየውን ውል ስምምነት በዛሬው ዕለት ፈፅሟል። በፈንሳዊው አሰልጣኝ ዲዲየ ጎሜስ ከቡድኑ የ20 ዓመት በታች ስብስብ ወደ ዋናው ቡድን የማደግ የቻለው ተጫዋቹ ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት በኢትዮጵያ ቡና መለያ በግሉ ጥሩ የሚባልን ጊዜ ማሳለፍ ችሏል። እርጋታ እና በራስ መተማመን የተላበሰውዝርዝር

በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ሲዳማ ቡናን ተረክበው ቡድኑን ከመውረድ መታደግ የቻሉት አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ በክለቡ ውላቸውን አድሰዋል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ታሪክ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ከተለያዩ ክለቦች ጋር የሊጉ አሸናፊ በመሆን ደማቅ ታሪክን ማፃፍ የቻሉት አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ በሲዳማ ቡና ያላቸውን ቆይታ አራዝመዋል። አሰልጣኙ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በቀላሉ ግብ ይቆጠርበት የነበረውን ቡድንዝርዝር

የዝውውር መስኮቱ በይፋ ከተከፈተ አንስቶ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች በዛሬው ዕለት ተጨማሪ ተጫዋችን ወደ ስብስባቸው መቀላቀል ችለዋል። በዛሬው ዕለት ሲዳማ ቡናን የተቀላቀለው አማካዩ ቴዎድሮስ ታፈሰ ነው። በመከላከያ ባለፉት ዓመታት ድንቅ ብቃቱን ማሳየት የቻለው ይህ አማካይ እጅግ ጥቂቶች ብቻ የታደሉትን በመከላከሉ ሆነ በማጥቃት ያለው የላቀ አበርክቶ እንዲሁም አስደናቂ የቆመ ኳስዝርዝር

ዘንድሮ ከቀደመው ጊዜያት ተዳክሞ የቀረበው ቡድናቸውን ለማጠናከር በዝውውር መስኮቱ ጠንካራ ሥራዎችን እየሰሩ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች የተከላካይ መስመር ተጫዋቾች አስፈርመዋል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና፣ መከላከያ፣ አዳማ ከተማ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በሀዲያ ሆሳዕና ያሳለፈው ተስፋዬ በቀለ የቡድኑ አራተኛ ፈራሚ ሆኖ ቡድኑን ተቀላቅሏል። የተጫዋቹ መፈረምም በቀላሉ ግብ ያስተናግድ ለነበረው የሲዳማዝርዝር

ለዘመናት ያለበቂ የማሻሻያ ስራዎች አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የአዲስ አበባ ስታዲየም የዕድሳት ሥራ በዛሬው ዕለት መጀመሩን የኢፊዲሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል። የኢፊዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ከሁለት ሳምንታት በፊት ለወራት ከዘለቀ የጨረታ ሒደት በኃላ ከተመረጠው ፍሬንድስ ኢንጅነሪንግ ኃ.የተ. የግል ኩባንያ ጋር በገባው የውል ስምምነት መሠረት ስራው በዛሬው ዕለት የተጀመረ ሲሆን በዕድሳቱ የመጀመርያ ምዕራፍ ከሚከናወኑዝርዝር

በውድድር ዘመኑ የመጨረሻ ትኩረታችን ሌሎች ትኩረት የሳቡ ጉዳዮችን ዳሰናል። 👉 የውድድር ዘመኑ ፍፃሜውን አግኝቷል በታህሳስ 3 ቀን 2013 ረፋድ አራት ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከሰበታ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ሀ ብሎ የጀመረው የ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግንቦት 20 ቀን 2013 ሀዲያ ሆሳዕና ከጅማ አባ ጅፋር ባደረጉት ጨዋታ ፍፃሜውን አግኝቷል። አንድዝርዝር

የውድድር ዘመኑ የማሳረጊያ በነበረው የጨዋታ ሳምንት የታዘብናቸው አሰልጣኝ ነክ ጉዳዮች በዚህኛው ፅሁፋችን ተዳሷል። 👉 የቅድመ እና ድህረ ጨዋታ አስተያየቶች ሊጋችን የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ማግኘቱን ተከትሎ አሰልጣኞች ከጨዋታዎች መጀመር አስቀድሞ እና መጠናቀቅ በኃላ ቅድመ ጨዋታ እና ድህረ ጨዋታ አስተያየቶችን በዘመነ ሱፐር ስፖርት እየተመለከትን እንገኛለን። እርግጥ ድህረ ጨዋታ አስተያየቶች በሀገራችን እግርኳስ ባለፉትዝርዝር