ዳዊት ፀሐዬ (Page 48)

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምሯል፡፡ በምድብ ሀ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከመመራት ተነስቶ ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፓርት አካዳሚን ሲረታ በምድብ ለ አዲስአበባ ከተማ ባለፈው ሳምንት በሀዋሳ ከተማ የደረሰበትን ሽንፈት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ላይ አወራርዷል፡፡ የአበበ ቢቂላ ስታድየም ለእድሳት በመዘጋቱ ምክንያት በፕሮግራም ለውጦች እየታመሰ በሚገኘው የኢትዮጵያዝርዝር

በቶታል ካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያን ወክሎ በመካፈል ላይ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ የኮንጎ ሪፐብሊኩ ኤሲ ሊዮፓርድስን 3-0 በሆነ የድምር ውጤት በማሸነፍ በኢትዮጵያ ክለቦች ታሪክ የመጀመሪያው የምድብ ድልድሉን መቀላቀል የቻለ ክለብ መሆን ችሏል፡፡ ከዚህ ታሪካዊ ድል በኃላ በትላንቱ የመልስ ጨዋታ ላይ ቡድኑን በአንበልነት እየመራ ወደ ሜዳ የገባው አዳነ ግርማዝርዝር

ፈረሰኞቹ የዘመናት ህልማቸውን እውን አድርገዋል በቶታል ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ ወደ ዶሊሴ አቅንቶ ምንተስኖት አዳነ ብቸኛ ግብ 1-0 አሸንፎ የተመለሰው ቅዱስ ጊዮርጊስ በዛሬው የመልስ ጨዋታ በሰልሀዲን ሰኢድ ሁለት ግቦች ኤሲ ሊዮፓርድስን በድምር ውጤት 3-0 በማሸነፍ በኢትዮጵያ ክለቦች ታሪክ ለመጀመሪያ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ወደ ምድብ ድልድል መግባትዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃግብር የሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክን ያገናኘው ጨዋታ ያለግብ ተፈጽሟል፡፡ ተመጣጣኝ ፉክክር በታየበት የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ አጋማሽ ጨዋታ እንደመጀመሪያው ጨዋታ ሁሉ ይህ ነው የሚባል ሳቢ የሆነ እንቅስቃሴ ሳይታይበት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡ ሁለቱም ቡድኖች በአመዛኙ በመሀል ሜዳ ላይ በተደገደቡ አጫጭርዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መርሃግብር ጅማ አባቡናን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታውን ያለ ግብ በአቻ ውጤተት ፈፅሟል፡፡ ቀዝቃዛ በነበረው የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ አጋማሽ ጨዋታ በመሃል ሜዳ ላይ ሁለቱም ቡድኖች ቶሎ ቶሎ የሚቆራረጡና የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቾቹ በርቀት ተነጥለው ሲባክኑ የተስተዋሉበት ጨዋታ ሆኖ አልፏል፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽም ይህ ነው የሚባል ኢላማውን የጠበቀዝርዝር

ኤልያስ ኢብራሂም – የደደቢት ምክትል አሰልጣኝ ስለ ጨዋታው “ጨዋታው በሁለተኛው ዙር መጀመሪያ ካደረግናቸው ሁለት ጨዋታዎች የተሻለ እንቅስቃሴ እና የተሻለ ውጤት ያገኘንበት ጨዋታ ነበር፡፡” በጉዳት ቡድናቸው ስለመሳሳቱ “ትኩረት አድርገን እየሰራን የምንገኘው ወጣቶች ላይ ነው፡፡ ምንም እንኳን በርካታ ተጫዋቾችን በጉዳት ብናጣም ብቁ የሆኑ ወጣት ተጫዋቾች ስላሉን የሚፈጠሩ ክፍተቶችን በወጣቶቹ ለመሸፈን እየሞከረን እንገኛለን፡፡”ዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት የእለተ ቅዳሜ ብቸኛ መርሀ ግብር አዲስአበባ ስታዲየም ላይ ወልዲያን ያስተናገደው ደደቢት በጌታነህ ከበደ ብቸኛ ግብ 1-0 በማሸነፍ ነጥቡን ወደ 31 አሳድጎ ነገ ጨዋታውን የሚያደርገው ሲዳማ ቡናን በግብ ልዩነት በመብለጥ በሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡ ደደቢቶች ባሳለፍነው ሳምንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ከተሸነፈው ቡድናቸው የ6 ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግዝርዝር

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን መርሃግብር ዛሬ በአዲስአበባ ስታድየም ቀጥሎ ሲውል ሀዋሳ ከተማ  መከላከያ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ በቅድሚያ 9፡00 ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ መካከል የተደረገው ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ በአቃቂ ቃሊቲ የሜዳ አጋማሽ አመዝኖ በተካሄደው የመጀመሪያው አጋማሽ ሀዋሳ ከተማዎች በ13ኛው ደቂቃ አይናለምዝርዝር

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ውሎ በእኩል 16 ነጥብ 12ኛ እና 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኙ የነበሩት ኢትዮ ኤሌክትሪክን እና ድሬዳዋ ከተማን 09:00 ላይ አገናኝቶ ኤሌክትሪክ 3-1 በሆነ ውጤት ተጋጣሚውን መርታት ችሏል፡፡ በጨዋታው ከተቆጠሩ 4 ጎሎች መካከል ሶስቱን ያስቆጠሩት “በረከት” የሚል መጠርያ ያላቸው ተጫዋቾች መሆናቸው የጨዋታው አስገራሚ ክስተት ነበር፡፡ዝርዝር

ማርት ኑይ – ቅዱስ ጊዮርጊስ  ስለ ጨዋታው እና ስለ ዋንጫ ግስጋሴያቸው ” ቡድኔ ከሳምንት ወደ ሳምንት ጥሩ መሻሻሎችን እያሳየ ይገኛል፡፡ በተለይም በሁለቱ መስመሮች በኩል ፕሪንስ እና በሀይሉ ጥሩ ነበሩ፡፡ የሁለተኛው ዙር ሁለተኛ ጨዋታ ላይ ስለምንገኝ አሁን ላይ ሆኖ በርካታ ጨዋታዎች እየቀሩን ስለ ዋንጫ መናገርያ ጊዜው አይደለም፡፡” ከመጀመሪያው ዙር በተሻለ ቡድኑዝርዝር