ዳዊት ፀሐዬ (Page 49)

ወላይታ ድቻ በአንደኛው ዙር ከቀድሞ ጊዜያት የተዳከመ እንቅስቃሴ ቢያደርግም በዛብህ መለዮ በግሉ ድንቅ የውድድር ዘመን በማሳለፍ ላይ ይገኛል፡፡ የአጥቂ አማካዩ 4 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን 3 ጎል የሆኑ ኳሶችንም አመቻችቶ አቀብሏል፡፡ በዛብህ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ባደረገው ቆይታ ጠንክሮ መስራቱ በድንቅ አቋም ለመገኘት እንደረዳው ተናግሯል፡፡ “በግሌ ሁልጊዜም ቢሆን የተሻለ ነገርን ለመስራት ጥረትዝርዝር

ሲዳማ ቡና አንደኛውን ዙር 5ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል፡፡ ቡድኑ በአንደኛው ዙር ተፎካካሪ እንዲሆን ቁልፍ ሚና ከተወጡት ተጫዋቾች መካከልም ሙሉዓለም መስፍን በዋነኝነት ይጠቀሳል፡፡ ሙሉአለም በጥሩ አቋም ላይ ስለመገኘቱ ፣ ስለቡድኑ የአንደኛ ዙር ጉዞ እና የ2ኛ ዙር አላማቸው ከዳዊት ጸሃዬ ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡ የመጀመሪያ ዙር የቡድናችሁን እንቅስቃሴ እንዴት ተመለከትከው? ” የመጀመሪያው ዙርዝርዝር

ወላይታ ድቻ በአንደኛው ዙር የመጨረሻ ጨዋታዎች ያስመዘገበውን ውጤት ተከትሎ በደረጃ ሰንጠረዡ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ 1ኛውን ዙር አጠናቋል፡፡ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በቡድናቸው የአንደኛ ዙር አቋም እና ስለ ሁለተኛው ዙር ለዳዊት ጸሃዬ የነገሩትን በዚህ መልኩ አቅርበነዋል፡፡ የመጀመሪያ ዙር የቡድኑ ጉዞ “ሊጉን ሁለት ጨዋታዎችን በሜዳችን በማሸነፍ በጥሩ ሁኔታ ነበር የጀመርነው፡፡ ነገርግን በ4ኛውዝርዝር

አዳማ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አንደኛው ዙርን 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ አጠናቋል፡፡ ባለፉት አመታት ከነበረው ተፎካካሪነት አንጻር ደረጃው መንሸራተት ቢያሳይም ከመሪዎቹ ያለው ርቀት ጥቂት ነው፡፡ ዳዊት ጸሀዬ በአዳማ ከተማ አንደኛ ዙር እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከቡድኑ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር ያደረገውን ቆይታ እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፡፡ የአዳማ ከተማን በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያውዝርዝር

ብርሃኑ ባዩ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስለ ጨዋታው ” በመጀመሪያው አጋማሽ እኛ የተሻልን ነበርን፡፡ በዚህም እኛ ብዙ ወደ ጎል የቀረቡ እድሎችን አምክነናል ፤ እነዛን እድሎች አስቆጥረን ቢሆን ኖሮ ወደ መጨረሻ ላይ እንደታየው ጫና ውስጥ ላንገባ እንችል ነበር፡፡” ስለ በሀይሉ ተሻገር ሚና ” ጥሩ ነው በሃይሉ በዛሬው ጨዋታ በዳዊት አለመኖር ምክንያት ተጠቅመዋልዝርዝር

አስራት ኃይሌ – መከላከያ ስለ ጨዋታው ” በዛሬው ጨዋታ ላይ ቡድኔ ጥሩ አልነበረም ፤ በአጠቃላይ እንቅስቃሴያችን አሳማኝ አልነበረም፡፡ በዛሬው ጨዋታ ላይ እንዳሳየነው እንቅስቃሴ ከሆነ መሸነፍ ይገባን ነበር፡፡ ሁሉም ቦታዎች ላይ እርማቶች አድርገን ነበር ጨዋታውን የጀመርነው፡፡ ነገር ግን ልጆቼ ለውጤቱ ጎጉተው ይሆን አላውቅም የነገርኳቸውን ነገር የመዘንጋት ነገር ይታይ ነበር፡፡ ዞሮ ዞሮዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃግብር ደደቢት እና መከላከያን ያገናኘው ጨዋታ ያለግብ በአቻ ውጤ ተጠናቋል፡፡ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ እጅግ የተቀዛቀዘ እና የሚጠቀሱ የግብ ሙከራዎች ያልታየበት ነበር፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽ ደደቢቶች ይዘው በገቡት የ3-5-2 የጨዋታ ቅርፅ የነበራቸውን የመሀል ሜዳ የቁጥር ብልጫ መጠቀም አልቻሉም፡፡ በአንጻሩ በዝርግ 4-4-2 ወደ ጨዋታው የገቡት መከላከያዎች በራሳቸው የሜዳዝርዝር

አለማየሁ አባይነህ – ሲዳማ ቡና ስለ ጨዋታው “ጨዋታውን የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ ጨርሰን መውጣት ይገባን ነበር፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻልን ነበርን ፤ በርካታ ግቦችን ማስቆጠር ይገባን ነበር፡፡ ነገር ግን ያንን ማድረግ አልቻልንም፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ልጆቼ ተቀዛቅዘው ነበር ፤ በመልሶ ማጥቃት ነበር ለመጫወት ያሰብነው፡፡ ነገርግን ጥቂት እድሎችን ነበር መፍጠር የቻልነው፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ከመስመርዝርዝር

ጸጋዬ ኪዳነማርያም – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስለ ጨዋታው “ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን ከሜዳ ውጪ ተሸንፈን ነበር የውድድር ዘመኑን የጀመርነው፡፡  ከዛ በኃላ በነበሩን ጨዋታዎች ቡድናችንን አሻሽለን ለመቅረብ ሞክረን ሁለት ጨዋታዎችን በተከታታይ አሸነፈን ነበር፡፡ ከዛ በኃላ ቋሚ ተጫዋቾቻችን በጉዳት እና በግል ችግር የተነሳ ከድሬዳዋው ጨዋታ ጀምሮ እስካሁን አልገቡም ነበር፡፡ ነገርግን በዛሬው ጨዋታ ሁለቱንዝርዝር

በ11ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወደ አዲስ አበባ ያቀናው ሲዳማ ቡና ከተከከታይ ነጥብ መጣሎች በኃላ አዲስ አበባ ከተማን 1-0 በማሸነፍ ዳግም ወደ አሸነፊነት ተመልሷል፡፡ በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃዎች ሁለቱም ቡድኖች በመሀል ሜዳ ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴን ያደረጉ ሲሆን በመጀመርያው አጋማሽ ሲዳማ ቡናዎች ወደፊት ቶሎ ቶሎ በመድረስ በርከት ያሉ የግብ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል፡፡ዝርዝር