ዳዊት ፀሐዬ (Page 51)

በ9ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ቀን ውሎ የሊጉ ክስተት የሆነው ፋሲል ከተማ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ አዲስ አበባ ከተማን ገጥሞ በቶጎዋዊው ኤዶም ሆሶሮውቪ የመጀመሪያ አጋማሽ 2 ግቦች በመታገዝ በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማን 2-0 መርታት ችሏል፡፡ ይህንን ድል ተከትሎ አፄዎቹ ካደረጓቸው ስምንት ጨዋታዎች 15 ነጥቦችን ሰብስበው ከመሪዎቹዝርዝር

በ8ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ መርሃግብር ታላቁ የሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና በኢኮ ፌቨር ብቸኛ ግብ ፈረሰኞቹን በመርታት የውድድር ዘመኑን ሁለተኛ ሙሉ ሶስት ነጥብ ማስመዝገብ ችሏል፡፡ ለወትሮውም ቢሆን በከፍተኛ የደጋፊዎች ታጅቦ የሚካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ተጠባቂ ጨዋታ ዛሬም እንደወትሮው ከጠዋት 12፡30 ጀምሮ የሁለቱም ቡድኖች ደጋፊዎች ካንቦሎጆ አካባቢ መሳባሰብ ጀምረው ነበር፡፡ ፌዴሬሽኑምዝርዝር

በ7ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ አስተናግዶ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ በ10፡00 ሰአት የጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በዚህ ሳምንት እንደተከናወኑት ሌሎች ጨዋታዎች ሁሉ ከትላንት በስቲያ ንጋት ላይ ከዚህ አለም በሞት ለተለየው ጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጥር የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነበር፡፡ዝርዝር

በ7ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃግብር መከላከያ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ከመመራት ተነስቶ 2-1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ መሪዎቹ ጎራ ለጊዜውም ቢሆን ተቀላቅሏል፡፡ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የተጀመረው በትላንትናው እለት ከዚህ አለም በሞት ለተለየው ጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነበር፡፡ በጨዋታው የመጀመሪያ 10 ደቂቃዎች ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ከመከላከያዎች በተሻለዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሶስት ሳምንታት ምንም ግብ ሳያስተናግድ ተጋጣሚዎቹ መረብ ላይ ስምንት ግቦችን አስቆጥረው በድንቅ ሁኔታ ሊጉን የጀመሩት ፈረሰኞቹ በአራተኛው ሳምንት በፋሲል ከተማ ጎንደር ላይ አስደንጋጭ ሽንፈትን ካስተናገዱ በኃላ በተከታታይ ያደረጓቸውን ሁለት ጨዋታዎችን ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ሊጉን ከመምራት ያገዳቸው ባይኖርም በመጨረሻ ካደረጓቸው ሶስት ጨዋታዎች ማግኘት ከሚገባቸው ዘጠኝ ነጥቦች ሁለቱንዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት በሜዳው አበበ ቢቂላ ስታዲየም ወልዲያ ያስተናገደው አዳማ ከተማ በሲሳይ ቶሊ ብቸኛ ግብ 1-0 በማሸነፍ ነጥቡን ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ እኩል አድርሷል፡፡ ከጨዋታው መጀመር በፊት በቅርቡ ከዚህ አለም በሞት ለተለየውና የአዳማ ተወላጅ ለሆነው ለድምፃዊ ኤርሚያስ አስፋው የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡ ከጨዋታው መጀመር አንስቶ የመሀል ሜዳውን ብልጫዝርዝር

አዳማ ከተማ1-0ወልድያ 6′ ሲሳይ ቶሊ ተጠናቀቀ!! ጨዋታው በአዳማ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ 90+3′ ብሩክ ቃልቦሬ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል 90′ ተጨማሪ አራት ደቂቃ ተጨምሯል 90′ ፋሲካ አስፋው አስከነ ህመሙ ወደ ሜዳ ተመልሶ ገብቷል፡፡ 89′ ፋሲካ አስፋው የትከሻ ጉዳት አጋጥሞት ከሜዳ ወጥቷል፡፡ 73′ ብሩክ ቃልቦሬ የሞከረው ኳስ ለጥቂት የግቡን ቋሚ ታካ ወጥታለች፡፡ዝርዝር

ሁለቱን የአዲስ አበባ ክለቦች ባገናኘው የ5ኛው ሳምንት ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመመራት ተነስቶ አዲስ አበባ ከተማን 2-1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ድል አስመዝግቧል፡፡ በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ኳስን ተቆጣጥረው በመጫወት ለማጥቃት እና ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ በመድረስ ግብ ለማስቆጠርግ ሲጥሩ ተስተውሏል፡፡ በመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች ኢትዮጵያ ንግድዝርዝር

5ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሲጀመር አዲስ አበባ ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አርባምንጭ ከተማን በ09:00 አስተናግዶ ነጥብ ተጋርቷል፡፡ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በሁለቱም አጋማሽ የተመልካችን አይን መያዝ ሳይችል የተጠናቀቀ ሲሆን በሁለቱም ቡድኖች በኩል ቶሎ ቶሎ ኳስ በመነጣጠቅ እና በመሀል ሜዳ የተገደቡ ተደጋጋሚ ቅብብሎች የታየበት ነበር፡፡ በዚሁ አሰልቺ በነበረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታዝርዝር

በ4ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግዶ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ በአዳማው አበበ ቢቂላ የተካሄደውን ጨዋታ ለመከታተል እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሁለቱም ክለቦች ደጋፊዎች ከ7 ሰአት ጀምሮ ወደ ስታዲየም ሲተሙ ተስተውሏል፡፡ ጨዋታውም በበርካታ የግብ ሙከራዎች እንዲሁም ሽኩቻዎች ታጅቦ ተጠናቋል፡፡ ባለሜዳዎቹ አዳማዎች የመጀመሪያውን የግብ ሙከራ ለማድረግ የፈጀባቸውዝርዝር