Soccer Ethiopia

Archives

በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዚህ ሳምንት

ጣልያን ትውልደ ኢትዮጵያዊው የአታላንታ ንብረት የሆነው እና በዓመቱ መጀመርያ ላይ ወደ ሴሪ ሲ ክለብ ሞኖፖሊ 1966 ያመራው አማካዩ ኢዮብ ዛምባታሮ ክለቡ በቪርቱስ ፍራንሳቪላ በተሸነፈበት ጨዋታ በሃያ ስምንተኛው ደቂቃ ለአዲሱ ክለቡ የመጀመርያ ግቡን ማስቆጠር ችሏል። በጨዋታው ባለሜዳዎቹ ሞኖፖሊዎች በኢዮብ ጎል መምራት ቢችሉም እንግዶቹ አከታትለው ባስቆጠሯቸው ግቦች ሦስት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸንፈው ወጥተዋል። ወደ ክለቡ ከተቀላቀለ ጀምሮ […]

ምዓም አናብስት ድጋፍ አደረጉ

የመቐለ 70 እንደርታ ተጫዋቾች እና የአሰልጣኞች ቡድን አባላት ለገበሬዎች ድጋፍ አድርገዋል። ለቀጣይ ውድድር ዓመት በዝግጅት ላይ የሚገኙት መቐለዎች በዓድዋ ወረዳ ጣቢያ ደብረ-ገነት ለሚገኙ አርሶአደሮች የንዋይ እና የጉልበት ድጋፍ አድርገዋል። ይህ በክለቡ ተጫዋቾች እና የአሰልጣኞች ቡድን የተደረገው ድጋፍ ሰማንያ ሺሕ የሚያወጣ የማጭድ ድጋፍ ያጠቃለለ ሲሆን የክለቡ አባላትም በገበሬዎቹ ማሳ ተገኝተው በርካታ ሥራዎች እንደሰሩ ክለቡ አሳውቋል። ከጊዜ […]

የሰማንያዎቹ… | ሁለገቡ የአንድ ክለብ ተጫዋች ሳምሶን አየለ

አስራ አራት ዓመታትን በአንድ ክለብ ብቻ የተጫወተው የሰማንያዎቹ ኮከብ ሳምሶን አየለ የእግር ኳስ ህይወት። ትውልድ እና ዕድገቱ በመዲናችን አዲስ አባበ በተለምዶው የድሮ ቄራ በሚባለው ሰፈር ነው። የእግርኳስ ህይወቱን በተወለደበት ሰፈር ጀምሮ ገና የመጀመርያ ደረጃ ትምህርቱን ሳያገባድድ በትልቅ ደረጃ መጫወት ጀምሯል። በወቅቱ ከዕድሜው ጋር የማይመጣጠን ብስለት እንደነበረውም ይነገርለታል። ገና በለጋነት ዕድሜው በአምበልነት የመራቸው ጨዋታዎች እና ከአንጋፋቹ […]

ሚካኤል ደስታ ወደ ስሑል ሽረ አምርቷል

ላለፉት ሦስት የውድድር ዓመታት መቐለ 70 እንደርታን በአምበልነት የመራው ሚካኤል ደስታ ከክለቡ ጋር ተለያይቶ ለስሑል ሽረ ፊርማውን አኑሯል። የእግርኳስ ሕይወቱን በመቐለ ጀምሮ ወደ ጣልያን በማምራት በሃገሪቱ የታዳጊ ቡድኖች ቆይታ አድርጎ በድጋሚ ወደ መቐለ ተመልሶ በትራንስ ኢትዮጵያ የክለብ እግርኳስ የጀመረው “ጣልያኑ” ለሰባት ዓመታት በትራንስ ቆይታ ካደረገ በኋላ በ2000 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መድን አቅንቷል። በመድን ለአንድ የውድድር […]

ኒጀሮች የአቋም መለክያ ጨዋታ አደረጉ

ቀጣይ የኢትዮጵያ ተጋጣሚ ኒጀር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ስታደርግ ከቀናት በኃላም ሁለት ጨዋታዎች ለማድረግ ቀጠሮ ይዛለች። በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በደርሶ መልስ ኢትዮጵያን የምትገጥመው ኒጀር በትናንትናው ዕለት ያደረገችው የአቋም መለክያ ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቃለች። በሜዳቸው ማሊን ያስተናገዱት ኒጀሮች በጨዋታው ሰሰላሳ አራተኛው ደቂቃ ባሳኩ ባስቆጠራት ግብ በተጋጣሚያቸውን ቢመሩም ብዙም ሳይቆዩ ከአስር ደቂቃ በኃላ በዳሬንኩም አማካኝነት ባስቆጠሯት ግብ አቻ […]

የሴቶች ገፅ | ኢንስትራክተር ሕይወት አረፋይነ ከትናንት እስከ ዛሬ…

ለብዙዎች አርዓያ መሆን የሚችለው የአሰልጣኝ ህይወት አረፋይነ የእግርኳስ ጉዞ ፣ የህይወት ተሞክሮ እና የወደፊት ህልም በሴቶች ገፅ መሰናዷችን እንዲህ ተቃኝቷል። በሴቶች እግር ኳስ ለበርካታ ዓመታት ከቆዩት አንዷ ናት። ዕድሜዋ ከአስራዎቹ ሳይሻገር በ1993 በከተማ ደረጃ እግርኳስን መጫወት ከጀመረች አንስቶ መቐለ 70 እንደርታን በፕሪምየር ሊግ ደረጃ እስካሰለጠነችበት የመጨረሻው የውድድር ዓመት ድረስ ድፍን ሃያ ዓመታትን በስፖርቱ ውስጥ ቆይታለች። […]

ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ኤሌክትሪክ አራት ተጫዋቾች አስፈረመ

የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የሆኑት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች የአራት ተጫዋቾች ዝውውር አጠናቀዋል። ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት ከአዳማ ከተማ ጋር ቆይታ በማድረግ ክለቡ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ድርሻ ከነበራቸው ተጫዋቾች የሆነችው እፀገነት ማረፍያዋ በሊጉ የተሻሉ ተፎካካሪ ለመሆን በጥረት ላይ ላሉት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ሆኗል። ከዚ በፊት በደደቢት፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዳማ ከተማ የተጫወተችው አማካይዋ ከሦስት የተለያዩ ክለቦች የፕሪምየር […]

ወልቂጤ አንድ ተጫዋች ወደ ዋናው ቡድን አሳደገ

በዝውውር መስኮቱ የነባር ተጫዋቾች ውል በማደስ እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማዘዋወር የቆዩት ሠራተኞቹ አሁን ደግሞ ተስፋ የተጣለበት የአማካይ ተጫዋቹ ቴዎድሮስ ብርሃኑን ወደ ዋናው ቡድን አሳድገዋል። በአመዛኙ የባለፈው ዓመት ስብስባቸው ይዘው ወደ ውድድር ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁት እና አምስት ተጫዋቾች ያስፈረሙት ሠራተኞቹ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውም ጀምረዋል። © ሶከር ኢትዮጵያ 👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

አዲሱ የኒጀር አሰልጣኝ ለኢትዮጵያው ጨዋታ ስብስባቸውን ይፋ አደረጉ

የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ኒጀር ስብስቧን ይፋ አድርጋለች። በአፍሪካ ዋንጫ የሞድቦ ማጣርያ የመጀመርያዎቹ ሁለት ጨዋታዎቿን በአይቮሪኮስት እና ማዳጋስካር የተሸነፈችው ኒጀር የምድቡ ቀጣዮ ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎችን ኖቬምበር 13 በሜዳዋ፤ ኖቬምበር 17 ደግሞ በባህር ዳር ከኢትዮጵያ ጋር ትጫወታለች። ለነዚህ ጨዋታዎች ስብስቧን ይፋ ያደረገችው ኒጀር አብዛኞቹ ተጫዋቾች ከሃገር ውስጥ ሊግ የተመረጡት ሲሆን በዴንማርኩ HB Køge የሚጫወተውን አማካዩ አደባዮር ዛካሪን […]

አሰልጣኝ ሕይወት አረፋይነ ከጨዋታ በፊት የምታደርገው ነገር ምንድነው ?

“በገድ ወይም በአጉል እምነት የማምን ሰው አይደለሁም” አሰልጣኝ ሕይወት አረፋይነ በእግርኳስ ዙርያ የሚሰሙ አጉል እምነቶች ወይም እንደ ጥሩ ዕድል ምልክት ተቆጥረው የሚደረጉ ተግባራት በርካታ ናቸው። ምንም እንኳ በሃገራችን እግርኳስ በይፋ የሚሰሙ መሰል ተግባራት እምብዛም ባይሆኑም ተመሳሳይ ነገሮች እንደማይጠፉ ለመገመት አይከብድም። በዓለም አቀፍ እግርኳስ የሚሰሙ ተመሳሳይ ተግባራትም ጥቂት የሚባሉ አይደሉም። ከነዚህ ውስጥ አይቮሪኮስታዊው የቀድሞ የአርሰናል ተከላካይ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top