Soccer Ethiopia

Archives

ምዓም አናብስት ጋናዊውን ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማሙ

ባለፉት ሦስት የውድድር ዓመታት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከታዩ ጥሩ የውጭ ግብ ጠባቂዎች አንዱ የሆነው ጋናዊው ዳንኤል አጃይ ወደ መቐለ 70 እንደርታ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል። በ2009 ከጋና ጋር የዓለም ወጣቶች ቻምፒዮን የሆነው አጃይ ሲምባን ለቆ ጅማ አባ ጅፋርን ከተቀላቀለ በኃላ በመጀመርያ ዓመት የክለቡ ቆይታው ቡድኑ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ድርሻ ከነበራቸው ተጫዋቾች አንዱ የነበረ ሲሆን የዓመቱ ምርጥ […]

ስሑል ሽረ አማካይ አስፈረመ

ተስፈኛው አማካይ ቃልአብ ጋሻው ወደ ስሑል ሽረ አምርቷል። በዝውውር መስኮቱ ዘግይተው በመግባት በርካታ ተጫዋቾች ወደ ስብስባቸው የቀላቀሉት ስሑል ሽረዎች አሁን ደግሞ ባለፈው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ሻሸመኔ ከተማ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው አማካዩ ቃልአብ ጋሻውን አስፈርመዋል። ከሼር ኢትዮጵያ ታዳጊ ቡድን የተገኘው እና ለባቱ ከተማ፣ ቡራዩ ከተማ እንዲሁም ባለፈው የውድድር ዓመት በሻሸመኔ ከተማ ቆይታ የነበረው ይህ ተጫዋች […]

አሰልጣኝ ብርሃኑ ባዩ የት ይገኛል?

በቅርብ ጊዜያት ከዕይታ የራቁ የእግርኳስ ሰዎችን በምናቀርብበት አምዳችን በኤሌክትሪክ ከተጫዋችነት እስከ አሰልጣኝነት ለረዥም ዓመታት አገልግሎ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከአሰልጣኝነት የራቀው ብርሀኑ ባዩ የት ይገኛል? ስንል ጠይቀናል። የእግርኳስ ሕይወቱን በ1979 በጭማድ ( ጭነት ማመላለሻ ድርጅት) ጀምሮ በክለቡ አንድ ዓመት ከቆየ በኃላ በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው አማካኝነት ወደ መብራት ኃይል ተዘዋውሮ ከእግርኳስ እስከ ተገለለበት ጊዜ ድረስ በቀዩ ቤት […]

መቐለ 70 እንደርታ ተከላካይ አስፈረመ

በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ የሆኑት መቐለ 70 እንደርታዎች ግዙፉን ማሊያዊ ተከላካይ አስፈርመዋል። በዚህ ክረምት ከበርካታ ተከላካዮች ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ የኋላ ክፍላቸውን በአዲስ መልኩ እንደሚያዋቅሩ የሚጠበቁት መቐለዎች በቦታው ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት ማሊያዊው ተከላካይ አዳማ ሲሶኮን ምርጫቸው አድርገዋል። በ2010 ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በመጀመርያ ዓመት ቆይታው ከጅማ አባጅፋር ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳው ይህ ተከላካይ ባለፈው ዓመት ከባህር ዳር […]

ወልዋሎዎች ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በዝውውሩ ንቁ ተሳትፎ አድርገው ስድስት ተጫዋቾች ያስፈረሙት ወልዋሎዎች ለተጫዋቾቻቸው ጥሪ አድርገዋል። ክለቡ ተጫዋቾቹ እንዲሰበሰቡ ጥሪ ያደረገ ሲሆን የኮቪድ 19 ምርመራ ከተደረገላው በኋላ ጥቅምት 17 ዝግጅት እንደሚጀምሩ ታውቋል። ባለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት በወልዋሎ ስታዲየም እድሳት ምክንያት በመቐለ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ያካሄዱት ቢጫዎቹ ዘንድሮ ግን በከተማቸው ዓዲግራት ዝግጅት የሚጀምሩ ይሆናል። እስካሁን ድረስ ዓወት ገብረሚካኤል፣ […]

ስሑል ሽረ የሁለት ተጫዋቾችን ውል አራዘመ

ስሑል ሽረዎች የሁለት ቁልፍ ተጫዋቾቻቸውን ውል አራዘመዋል። ዲዲዬ ለብሪ ካራዘሙት መካከል ነው። ከሦስት ዓመት በፊት ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ፈርሞ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው እና በእግርኳስ ሕይወቱ ለአስራ ሁለት የተለያዩ ክለቦች ተዘዋውሮ የተጫወተው ፈጣኑ አማካይ ከዚ በፊት ለሴፋክስ፣ ኤስፔራንስ እና አል ሜሪክ ተጫውቷል። ጅማ አባ ጅፋርን ለቆ ወደ ሽረ ካመራ በኋላ ባለፈው የውድድር ዓመት ጥሩ ጊዜ ካሳለፉ የክለቡ […]

ስሑል ሽረዎች ተጫዋች ማስፈረማቸውን ቀጥለዋል

ቀደም ብሎ ወደ አዳማ ከተማ ለማምራት ተስማምቶ የነበረው ታሪክ ጌትነት ወደ ስሑል ሽረ አምርቷል። ከደደቢት የረጅም ጊዜ ቆይታ በኃላ ወደ ወላይታ ድቻ አምርቶ በክለቡ የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገው ታሪክ ባለፈው የውድድር ዓመት በሀድያ ሆሳዕና ቆይታ አድርጓል። ከአቤር ኦቮኖ ጋር እየተፈራረቀ የመሰለፍ ዕድል ያገኘው ይህ ግብጠባቂ ምንተስኖት አሎ እና ወንድወሰን አሸናፊ ላጡት ስሑል ሽረዎች ጥሩ ፊርማ […]

ወልዋሎዎች የሁለት ተጫዋቾች ዝውውር አጠናቀቁ

ባለፈው ሳምንት አራት ተጫዋቾች ያስፈረሙት ቢጫ ለባሾቹ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾች ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል። የመጀመርያው ፈራሚ የመስመር ተከላካዩ ሽመልስ ተገኝ ነው። ከሙገር ወደ መከላከያ በማምራት ለረጅም ዓመታት በጦሩ ቆይታ ያደረገው ሽመልስ ከአንድ ዓመት የከፍተኛ ሊግ ቆይታ በኋላ ወደ ፕሪምየር ሊጉ የሚመልሰውን ዝውውር ሲያደርግ ባለፈው ሳምንት ለቢጫዎቹ ከፈረመው ዓወት ገብረሚካኤል ጋር ለቦታው ቋሚ ተሰላፊነት ይፎካከራል። ሌላው ፈራሚ […]

መስፍን ታፈሰ ነገ ብሔራዊ ቡድኑን ይቀላቀላል

በኢኳቶርያል ጊኒ በሙከራ ላይ የሚገኘው መስፍን ታፈሰ ነገ ብሔራዊ ቡድኑን ይቀላቀላል። ባለፈው ወር ወደ ኢኳቶርያል ጊኒው ቻምፒዮን ፉትሮ ኪንግስ ለሙከራ ያቀናው የሀዋሳ ከተማው አጥቂ መስፍን ታፈሰ ዛሬ ሌሊት ኢትዮጵያ ገብቶ ነገ ጠዋት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የሚያደርግ ሲሆን ውጤቱ ታይቶ ብሔራዊ ቡድኑን ይቀላቀላል ተብሏል። ላለፈው አንድ ወር ከፉትሮ ኪንግስ ጋር ልምምድ ሲሰራ የቆየው መስፍን ቡድኑ ባደረጋቸው […]

አሰልጣኝ ብርሃኔ ገብረእግዚአብሔር የት ይገኛሉ?

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለረጅም ዓመታት ካሰለጠኑ አንጋፋ አሰልጣኞች መካከል ስማቸው ይጠራል። በአሰልጣኝነት ጊዜያቸው ኪራይ ቤቶች፣ ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ድርጅት፣ ኢትዮጵያ መድን፣ መቐለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ እና ወሎ ኮምቦልቻን አሰልጥነዋል። በ2009 ወልዋሎን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያሳለፉበት ድላቸው ትልቁ ነው። በ2010 ከወሎ ኮምቦልቻ ጋር ከተለያዩ በኃላ ከአሰልጣኝነት ርቀው የሚገኙት አሰልጣኙ ከሞያው ስለራቁበት ምክንያት እና አሁን ስለሚገኙበት ሁኔታ አጭር […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top