Soccer Ethiopia

Archives

ዜና እረፍት| የቀድሞ የዎላይታ ድቻ አምበል ህይወቱ አለፈ

ከዚህ ቀደም ዎላይታ ድቻን በአምበልነት የመራውና የወቅቱ የሶዶ ከተማ አምበል ፈጠነ ተስፋማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የተጫዋቹ ህልፈተ ሕይወት የተሰማው ዛሬ ወደ 5 ሰዓት ገደማ ሲሆን በድንገት በመኖሪያ ቤቱ አርፎ ተገኝቷል። የእግርኳስ ህይወቱን በሶዶ የፕሮጀክቶች ሥልጠና ውስጥ የጀመረው ፈጠነ ተስፈማርያም በ2002 ዎላይታ ድቻ ሲቋቋም በአምበልነት የመራ ሲሆን ድቻ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ትልቁን አስተዋፅኦ አበርክቷል። […]

የወላይታ ድቻ ቡድን አባላት ድጋፍ ሲያደርጉ አሰልጣኞች እና የቀድሞ ተጫዋቾች ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ አከነውነዋል

የኮሮናን ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረገው ድጋፍ የቀጠለ ሲሆን የወላይታ ድቻ የቡድን አባላት የገንዘብ ድጋፍ አበርክተዋል። አሰልጣኞች እና የቀድሞ ተጫዋቾችም የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ አከናውነዋል። ወላይታ ድቻዎች ከተጫዋቾች፣ የክለቡ አመራሮች እና አሰልጣኞች እንዲሁም በቡድኑ ውስጥ የሚገኙ ሠራተኞች የተሰበሰበ አንድ መቶ ሺህ ብር ለዞኑ የኮሮና ቫይረሰ መከላከል ግብር ኃይል አስረክበዋል። ቡድኑም በቀጣይ በርካታ የገንዘብና ቁሳቁስ […]

የአሰልጣኞች አስተያየት | ወላይታ ድቻ 1-1 ፋሲል ከነማ

ከ7ኛ ሳምንት የሊጉ የዛሬ ጨዋታዎች መካከል ሶዶ ላይ ወላይታ ድቻ እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ከተጋሩ በኋላ የቡድኖቹ አሰልጣኞች ተከታዮቹን አስተያየቶች ሰጥተዋል። 👉 ” ዛሬ ቡድኔ በሁሉም ነገር የተሟላ ነበር” ገብረክርስቶስ ቢራራ (ወላይታ ድቻ) ስለጨዋታው እንዳያችሁት ዘጠና ደቂቃ አልቆ ፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቶብናል፤ ኳሱ እጁን በመነካቱ ዳኛው የራሱን ውሳኔ ወስኗል። ዛሬ ቡድኔ በሁሉም ነገር የተሟላ ነበር። […]

ሪፖርት | ፋሲል ከነማ በመጨረሻ ደቂቃ ጎል ከወላይታ ድቻ ጋር ነጥብ ተጋርቷል

በ7ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሶዶ ላይ ፋሲል ከነማን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ ባለቀ ሰዓት በተቆጠረበት የፍፁም ቅጣት ምት ግብ በ1-1 ውጤት ጨዋታውን ሲያጠናቅቅ የዐፄዎቹ አንድ ነጥብ ይዘው መመለስ ችለዋል። ወላይታ ድቻ ከሜዳው ውጪ በ6ኛው ሳምንት የሊግ መርሐግብር በሰበታ ከነማ ሽንፈት ካሰተናገደበት ስብስብ ውስጥ የሁለት ተጫዋቾችን ለውጥ በማድረግ ይግረማቸው ተስፋዬን በእዮብ ዓለማየሁ እና እንድሪስ ሰዒድን […]

የአሰልጣኞች አስተያየት | ወላይታ ድቻ 0-1 ወልቂጤ ከተማ

ወደ ሶዶ ያመራው ወልቂጤ ከተማ ባለሜዳው ወላይታ ድቻን ገጥሞ 1-0 ካሸነፈ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። “ለዛሬው ውጤታችን ሜዳው ትልቁን አስተዋጾ አድርጎልናል” ደግአረገ ይግዛው (ወልቂጤ ከተማ) ስለጨዋታው ጨዋታው እንዳያችሁት ከባድ ፉክክር ነበረው። እኛ ወደዚህ ስንመጣ የተቻለንን ነገር ተጠቅመን ውጤት ለማግኘት ነበር። ነገር ግን ወላይታ ድቻ ሊጉ ላይ ካሉት ጠንካራ ቡድኖች መካከል ነው፤ ልምድ ያላቸው […]

ሪፖርት | ወልቂጤ ከተማ የመጀመርያ የሜዳ ውጪ ድሉን ወላይታ ድቻ ላይ አሳክቷል

በ5ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሶዶ ላይ ወልቂጤ ከነማን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ 1-0 ተሸንፏል። አዲስ አዳጊው ወልቂጤ ከተማም በታሪኩ የመጀመርያ የፕሪምየር ሊግ የሜዳ ውጪ ድል ማስመዝገብ ችሏል። ወላይታ ድቻ ባለፈው ሳምንት ከአዳማ ከተማ ጋር ነጥብ ከተጋራው ስብስብ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ ቸርነት ጉግሳ እና ተስፋዬ አለባቸውን በተመስገን ታምራት እና ፀጋዬ ብርሃኑ ተክቶ ወደ ሜዳ […]

ወላይታ ድቻ በፎርፌ 3 ነጥብ አግኝቷል

በ27ኛው ሳምንት ከተያዙት የኢትዮጽያ ፕሪምየር ሊግ መርሃግብሮች ውስጥ ሶዶ ላይ ሊካሄድ የነበረው የወላይታ ድቻ እና ጅማ አባጅፋር ጨዋታ ጅማዎች ባለመገኘታቸው በደንቡ መሠረት የፎርፌ ውሳኔ ተግባራዊ ሆኗል። ጅማ አባጅፋሮች ከተጫዋች የደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዝ በገጠማቸው ችግር ምክንያት ያሳለፍነውን ሳምንት የቡድኑ ስብስብ ምንም ዓይነት ልምምድ ያላደረጉ ከመሆኑ ጋር ወደ ሶዶ ሳያመሩ ቀርተዋል። በመሆኑም የዕለቱን መርሀግብር የሚዳኙት ዳኞች […]

ሪፖርት | ወላይታ ድቻ እና ስሑል ሽረ ነጥብ ተጋርተዋል

ከፕሪምየር ሊጉ የ16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መካከል የወራጅነት ስጋት ላይ የሚገኙት ወላይታ ድቻ እና ስሑል ሽረ ሶዶ ላይ 1-1 በሆነ ወጤት ተለያይተዋል። በሁለተኛው ዙር የአሰልጣኝ ለውጥ በማድረግ እና በርከት ያሉ ተጫዋቾችን በማዘዋወር ወደ ውድድር የተመለሱት ሁለቱ ቡድኖች የሚያደርጉት ጨዋታ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት እንደመደረጉ ተጠባቂ ሆኖ ነበር። የዕለቱ ጨዋታ ከመጀመሩ አስቀድሞ የወላይታ ድቻ የደጋፊዎች ማህበር ደጋፊዎችን በማስተባበር ባሳለፍነው […]

የአሰልጣኞች አስተያየት | ወላይታ ድቻ 1-1 ባህር ዳር ከተማ 

ሶዶ ላይ የተከናወነው የወላይታ ድቻ እና ባህርዳር ከተማ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። “በውጤቱ ደስተኛ ነኝ” ጳውሎስ ጌታቸው – ባህር ዳር ከተማ ስለ ጨዋታው  ” በጠቃላይ ጨዋታው እጅግ በጣም ውጥረት የበዛበት እና እልህ አስጨራሽ የነበረ ነበር። ምክንያቱም እነሱም ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት እኛም ወደ መሪዎች ለመጠጋት የምንፈልገው ስለነበር ጠንካራ ነበር። ከእረፍት በፊት ተበልጠናል […]

ሪፖርት | ወላይታ ድቻ እና ባህር ዳር ከተማ አቻ ተለያይተዋል

በ13ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ ዛሬ ሶዶ ላይ ወላይታ ድቻ ባህር ዳር ከተማን ያስተናገደበት ጨዋታ በ1-1 ውጤት ተፈፅሟል። ወላይታ ድቻዎች በ12ኛው ሳምንት ጅማ ላይ 2-0 ከተሽነፉበት ጨዋታ ውብሸት ክፍሌን ከቅጣት በተመለሰው እሸቱ መና ብቻ በመለወጥ ወደ ሜዳ ሲገቡ እንግዳው ባህር ዳር ከተማ ከፋሲል ከነማ ጋር አቻ ከተለያየበት አሰላለፍ ውስጥ በተመሳሳይ የአንድ  ተጫዋች ለውጥ በማድረግ  ማራኪ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top