ሚካኤል ለገሰ

በነገው ዕለት ከሩዋንዳ አቻው ጋር የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን አመሻሽ ላይ ሰርቷል። ኮስታሪካ ለምታስተናግደው የ2022 የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የአህጉራችን ብሔራዊ ቡድኖች የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በቀጥታ ወደዝርዝር

ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከሰራተኞቹ ጋር ያሳለፈው የመሐል ተከላካይ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል። 2012 ላይ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዋናው የሀገሪቱ የሊግ እርከን ያደገው ወልቂጤ ከተማ ባደገበት ዓመት የመሐል ተከላካዩን ቶማስ ስምረቱ ከኢትዮጵያ ቡና አስፈርሞ እንደነበር ይታወሳል። ተከላካዩ በኮቪድ-19 ምክንያት የተሰረዘውን ግማሽ እና የ2013 የውድድር ዓመትን በክለቡ በመቆየት ግልጋሎት ሲሰጥ ነበር።ዝርዝር

ለ15 ጊዜ የሚደረገውን የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አስመልክቶ ዛሬ ረፋድ መግለጫ ተሰጥቷል። በአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚከናወነው የመዲናው ዋንጫ ዘንድሮ ለ15 ጊዜ እንደሚከናወን ይታወቃል። በስምንት ክለቦች መካከል የሚደረገው የዘንድሮ ውድድርም ከመስከረም 15 ጀምሮ እስከ 30 ድረስ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል። ባሳለፍነው ሳምንት የውድድሩ የምድብ ድልድል የወጣ ቢሆንም ተጋባዡዝርዝር

ከደቡብ አፍሪካ ጋር ለሚደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታ ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ ያቀረቡት አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከፈረሰኞቹ የመረጧቸውን ተጫዋቾች አላገኙም። ኳታር ለምታስተናግደው የ2022 ዓለም ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ 7 ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባቡዌ ጋር እንደተደለደለ ይታወቃል። ብሔራዊ ቡድኑም ሁለት የምድብ ጨዋታዎችን አድርጎ ሦስት ነጥብ በማግኘት የምድቡዝርዝር

ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው የሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ሲጀመር የእጣ ማውጣት መርሐ-ግብሩም ነገ ከሰዓት ይከናወናል። ከተቋቋመ ገና አንድ ዓመት እያስቆጠረ የሚገኘው የሲዳማ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንደ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚቆጠረውን የክልሉ ዋንጫ ፍልሚያ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚያከናውን ይታወቃል። የስፖርት ትጥቅ አምራች ተቋሙ ጎፈሬ’ን የሥያሜ አጋር በማድረግ ከመስከረም 15 ጀምሮ የሚካሄደውዝርዝር

የባህር ዳር ከተማን የሴቶች ቡድን ከታችኛው የሊግ እርከን ወደ ዋናው ሊግ ያሳደገችው አሠልጣኝ ሰርካዲስ እውነቱ በዛሬው ዕለት ውሏን አራዝማለች። ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ ሁለተኛ ዲቪዚዮን የሴቶች ውድድር 41 ነጥቦችን በመሰብሰብ ወደ ዋናው ሊግ ያደገው ባህር ዳር ከተማ የአሠልጣኙን ውል ለማደስ ከሰሞኑን ንግግር ሲያደርግ ነበር። ክለቡም ከምስረታው አንስቶ አሠልጣኝ የነበረችውን ሰርካዲስዝርዝር

ከመስከረም 15 ጀምሮ በሚካሄደው የሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ውድድር ላይ ተካፋይ የሚሆኑ ስድስት ክለቦች በውድድሩ የስያሜ ባለቤት የተሰራላቸውን ልዩ መለያ በነገው ዕለት ይረከባሉ። በስድስት ክለቦች መካከል ከመስከረም 15 ጀምሮ የሚደረገው የሲዳማ ዋንጫ ውድድር ሀገር በቀሉን የትጥቅ አምራች ተቋም ጎፈሬ’ን የስያሜ አጋራ በማድረግ በሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ ይታወቃል። የሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ በሚል የሚካሄደውዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ሊጀምሩ ነው። በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ከፊቱ ጨዋታ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ሊጀምር መሆኑን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል። በዚህም የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ለዩጋንዳው ጨዋታ ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ በካፍዝርዝር

ኮስታሪካ ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል አንዱ የሆነውን መርሐ-ግብር ለመዳኘት አራት እንስት የሀገራችን ዳኞች ወደ ናይሮቢ ሊያመሩ ነው። በቀጣይ ዓመት በኮስታሪካ አስተናጋጅነት በሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የአህጉራችን ብሔራዊ ቡድኖች የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታቸውን ካለንበት ሳምንት አንስቶ ማድረግ ይጀምራሉ። ካሉት መርሐ-ግብሮች መካከል ደግሞዝርዝር

ከሩዋንዳ አቻው ጋር የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከፊቱ ያለበት የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች  የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን እና ከፊቱ ያሉበትን ጨዋታዎች አስመልክቶ ለብዙሃን መገናኛ አባላት መግለጫ ሰጥቷል። ኮስታሪካ ለምታስተናግደው የ2022 ዓለም ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከፊቱ የሚጠብቁት የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታ ከሩዋንዳ ጋር እንደሚጫወትዝርዝር