ሚካኤል ለገሰ (Page 2)

መስከረም 26 እና 30 ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የሚያደርገው የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በፊት ለተጫዋቾች ጥሪ አስተላልፏል። ኳታር ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በየአህጉራቱ የሚገኙ ብሔራዊ ቡድኖች የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል። በአህጉራችን አፍሪካም ብሔራዊ ቡድኖች በምድብ ተከፋፍለው የማጣሪያ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ። በዚሁ የማጣሪያ ጨዋታዎች በምድብዝርዝር

ከቀናት በፊት በሶከር ኢትዮጵያ ባህር ዳርን ለመቀላቀል መስማማቱን ዘግበን የነበረው ቡርኪናፋሶዋዊው ተጫዋች የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅሏል። በአሠልጣኝ አብርሃም መብራቱ የሚመራው ባህር ዳር ከተማ ቡርኪናፋሶዋዊው የአጥቂ አማካይ አብዱልከሪም ንኪማን ለማስፈረም መስማማቱን ከቀናት በፊት ዘግበን እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ተጫዋቹም በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ በመምጣት ዝውውሩን ማገባደዱ ይፋ ሆኗል። በ2009 እና 2010 በቅዱስ ጊዮርጊስ በመጫወትዝርዝር

👉”በሜዳችን ያደረግነው ጨዋታ ላይ ያገኘነው ውጤት አርኪ አይደለም” 👉”በዚህ የቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ላይ ሁላችንም ትኩረታችን አንድ ነገር ላይ ነው። እሱም…” 👉”ለማሸነፍ እና ሙሉ ነጥብ ለማግኘት ጉጉት ላይ ነን። እንዳልኩት እናደርገዋለን ፤ በቡድኔ ላይም ዕምነት አለኝ” 👉”ሦስት ነጥብ ብቻ ብለን ለማሸነፍ ነው ወደ ሱዳን የሄድነው እንጂ ሀገር ለመጎብኘት አይደለም” የ2013 የኢትዮጵያዝርዝር

ለመጀመሪያ ጊዜ ከመስከረም 16 ጀምሮ የሚካሄደው ውድድር ጎፈሬ የሲዳማ ዋንጫ በሚል ስያሜ እንደሚካሄድ በዛሬው ዕለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል። ከተቋቋመ ገና አንድ ዓመቱን ያስቆጠረው የሲዳማ እግርኳስ ፌዴሬሽን በስሩ የሚከናወን የመጀመሪያውን የቅድመ ውድድር ዝግጅት ፍልሚያ ከመስከረም 16 ጀምሮ እንደሚያደርግ መግለፁ ይታወቃል። በሀዋሳ ከተማ በሚካሄደው ውድድር ላይም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች እንደሚሳተፉዝርዝር

ከፊቱ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ተከታታይ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ያሉበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ በቀጣይ ሳምንት ዝግጅቱን ይጀምራል። በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኳታር ለምታስተናግደው የ2022 ዓለም ዋንጫ ለማለፍ በምድብ ሰባት ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባቡዌ ጋር ተደልድሎ የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል። ብሔራዊ ቡድኑምዝርዝር

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን የምስል ባለ መብት ዲ ኤስ ቲቪ ለአስራ አንድ ቀናት የሚቆይ ሥልጠና ለሊጉ አሠልጣኞች ሊሰጥ መሆኑ ታውቋል። ከ2013 ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ዓመታት የሊጉን የምስል መብት ዳጎስ ባለ ገንዘብ የገዛው ዲ ኤስ ቲቪ የፕሪምየር ሊጉን ገፅታ ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል። ከሳምንታት በፊት ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበርዝርዝር

የአዲስ አበባ ስታዲየምን በባለቤትነት የሚመራው የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ለስታዲየሙ እየተደረገ ያለውን እድሳት በተመለከተ ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰጥቷል። በብቸኝነት ዘለግ ላሉ ዓመታት ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ጨዋታዎችን ሲያስተናግድ የነበረው የአዲስ አበባ ስታዲየም በካፍ እና ፊፋ የተቀመጠውን መመዘኛ ባለማሟላቱ ከጨዋታዎች መታገዱ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ ስታዲየሙን ለጨዋታዎች ለማብቃት የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ጨረታ በማውጣት በሁለትዝርዝር

የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን የፊታችን እሁድ ከአል ሂላል ጋር የሚያደርገዋል ፋሲል ከነማ ነገ ወደ ስፍራው ጉዞውን ያደርጋል። በአሠልጣኝ ሥዩም ከበደ እየተመሩ የሊጉን ዋንጫ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍ አድርገው ያነሱት ፋሲል ከነማዎች በአህጉራዊው ትልቁ የክለቦች የውድድር መድረክ ለመሳተፍ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል። ክለቡም በመጀመሪያ ዙር የማጣሪያዝርዝር

ከመስከረም 15-30 ድረስ የሚካሄደው የመዲናው የዋንጫ ውድድር ላይ የሚካፈሉ ክለቦች ዛሬ የደንብ ውይይት ሲያደርጉ የእጣ ማውጣት መርሐ-ግብሩም በነገው ዕለት የሚከናወን ይሆናል። ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ የሚከናወነው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር ከመስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚደረግ መገለፁ ይታወሳል። ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ አዲስ አበባ ከተማ፣ መከላከያ፣ዝርዝር

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡናን በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚገጥመው የዩጋንዳው ክለብ ዩ አር ኤ ነገ ማለዳ ኢትዮጵያ ይገባል። በካፍ ሥር የሚደረገው እና የአህጉሪቱ ሁለተኛው ትልቁ የክለቦች ፍልሚያ በሆነው የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ኢትዮጵያ ቡና የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል። ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻምዝርዝር