ሚካኤል ለገሰ (Page 90)

ዛሬ ከሰዓት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በገዛው አዲስ ህንፃ ላይ ኢትዮ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ምስረታን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጥቷል። ጋዜጣዊ መግለጫውን ለመስጠት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት እና የሊግ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አወል አብዱራሂም (ኮሎኔል)፣ የውድድር እና ስነ-ስርዓት ኮሚቱ ሰብሳቢው አቶ ጌታቸው የማነብርሃን (ኢንስፔክተር)፣ የሕግ ባለሙያ አቶ ኃይሉዝርዝር

የኢትዮጵያን ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን በአሁኑ ሰዓት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል እያደረገ ባለው ስብሰባ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ላይ ክስ ሊመሰርት እንደሆነ ገልጿል። ከደቂቃዎች በፊት በጀመረው በዚህ ስብሰባ የአሶሴሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ፣ የአሶሴሽኑ ፀሃፊ አቶ ሳምሶን እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል። በቦታው ከተገኙ የየክለቦች አምበሎች ጋር እየተደረገ ባለው ውይይትምዝርዝር

የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌደሬሽን በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የሲቲ ካፕ ውድድር ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ እንደሚከናወን ይጠበቃል። ፌደሬሽኑ ውድድሩን ለማከናወን ያሰበበት ጊዜም ታውቋል። በየዓመቱ የሚከናወነው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ (ሲቲ ካፕ) ውድድር ዘንድሮ ከመስከረም 23 – ጥቅምት 9 እንደሚደረግ የፌደሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ዮናስ ሃጎስ (ጋዜጠኛ) ለሶከር ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።ዝርዝር

ኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ከሰዓት በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ከአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ጋር በይፋ የቅጥር ስምምነት ተፈራርሟል። ለሁለት ሰዓታት በቆየው ጋዜጣዊ መግለጫ የክለቡ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ፣ የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ስንታየሁ በቀለ ፣ የክለቡ ደጋፊዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ክፍሌ አማረ እና አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል። በቦታው በዋናነት ክለቡዝርዝር

ለ2022 የኳታር ዓለም ዋንጫ ለማለፍ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን በሜዳው ከሌሶቶ ጋር ያከናወነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 0-0 ተለያይቷል። በግሩም የደጋፊ ድባብ ታጅቦ በባህር ዳር ስታዲየም የተከናወነው ጨዋታው ምንም የተሻለ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ሳይስተዋልበት ተጠናቋል። በ4-3-3 የተጨዋች አደራደር ቅርፅ ወደ ሜዳ የገቡት ዋሊያዎቹ ኳስን በመቆጣጠር ረገድ የተሻለ ቢመስሉም የጠራ የግብ ማግባት እድሎችንዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በቶኪዮ ለሚዘጋጀው የ2020 የኦሊምፒክ ውድድር ለማለፍ የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ነገ ያከናውናሉ። በ2020 ጃፓን ቶኪዮ ላይ ለሚደረገው የኦሊምፒክ ውድድር ለመሳተፍ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እያደረጉ የሚገኙት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የመልስ ጨዋታቸውን ለማድረግ ካሜሩን ገብተዋል። ከሳምንት በፊት ባህር ዳር ላይ የተጫወቱት ሉሲዎቹ በተቀዛቀዘ የጨዋታ እንቅስቃሴ 1-1 መለያየታቸውዝርዝር

ዘግየት ብለው ወደ ተጨዋቾች ዝውውር የገቡት ኢትዮጵያ ቡናዎች አምስተኛ ተጨዋቻቸውን ለማስፈረም ተስማምተዋል። ከጣና ሞገዶቹ ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ወንድሜነህ ደረጄ ከሱሉልታ ከተማ ወደ ባህር ዳር ከተማ በ2009 የተዘዋወረ ሲሆን ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ ወሳኝ ግልጋሎት አበርክቷል። ባሳለፍነው የውድድር ዓመትም በቋሚነት ከአቤል ውዱ ጋር ጠንካራ ጥምረት ፈጥሮ ዓመቱን ሲቋጭዝርዝር

የጣና ሞገዶቹ ዘግይተው ወደ ዝውውር እንቅስቃሴ በመግባት ተጫዋቾች በማስፈረም ላይ ሲገኙ በዛሬው ዕለትም አፈወርቅ ኃይሉን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል። ታታሪው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች በወልዋሎ መልካም ጊዜያትን ያሳለፈ ሲሆን በተለይም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ እና ዋናው ብሔራዊ ቡድን ጥሪ እንዲደርሰው ያስቻለ እንቅስቃሴ ማድረግ ችሏል። ባህር ዳር ከተማዎች በ1 ዓመት ኮንትራት ካስፈረመውዝርዝር

በተከታታይ ቀናት አንድ አንድ ተጨዋች እያስፈረሙ የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች የቀድሞ ተጨዋቻቸውን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል። ሳሙኤል ተስፋዬን እና ኤፍሬም ዓለሙን (መጠርያ ስሙን ወደ ፍፁም ዓለሙ ቀይሯል) በማስፈረም ወደ ዝውውር ገበያው የገቡት ባህር ዳር ከተማዎች ዛሬ ከሰዓት ሚኪያስ ግርማን ማስፈረማቸው ታውቋል። ከዚህ ቀደም ለአደድ ዓመት ከግማሽ በባህር ዳር መጫወት የቻለው ሚኪያስዝርዝር

ሳሙኤል ተስፋዬን ከቅዱስ ጊዮርጊስ በማስፈረም ወደ ዝውውር መስኮቱ የገቡት ባህር ዳር ከተማዎች ሁለተኛ ተጨዋቻቸውን ማግኘታቸውን አስታውቀዋል። አዲስ የቴክኒክ ክፍል በማዋቀር የዝውውር ገበያውን ዘግይተው የተቀላቀሉት ባህር ዳሮች አሰልጣኛቸው ፋሲል ተካልኝ ያመነባቸውን ተጨዋቾች ወደ ቡድናቸው እየቀላቀሉ ይገኛሉ። ዛሬ ማምሻውንም የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ከሆነው ፋሲል ከነማ ኤፍሬም ዓለሙን በእጃቸው ማስገባታቸውን አስታውቀዋል። በዘንድሮ የውድድርዝርዝር