ሚካኤል ለገሰ (Page 91)

 ዜና | 04-01-2009  በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን አዘጋጅነት ለ11ኛ ጊዜ የሚካሄደው የአዲስ አበባ ዋንጫ(city cup) መስከረም 28 እንደሚጀመር ታውቋል፡፡ ስምንት ክለቦችን የሚያሳትፈው ይህ ውድድር ለሁለት ሳምንታት በአዲስ አበባ ስታድየም እንደሚከናወን ከፌደሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ለውድድሩ በቶሎ አለመጀመር እንደ ምክንያት የቀረበው የአዲስ አበባ ስታድየም እድሳት ላይ በመሆኑ እና የኢትዮጵያ ፕሪምየርዝርዝር

በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው የሴቶች የሴካፋ ውድድር ከመስከረም1 እስከ መስከረም 14 ይደረጋል። ከሚሳተፉት ሰባት ቡድኖች መካከል በምድብ ሁለት የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በድሬዳዋ ከተማ ከነሀሴ 13 ጀምሮ በትሪያንግል ሆቴል ከትሞ ዝግጅቱን ሲያከናውን ቆይቶ ከትላንት በስትያ አዲስ አበባ የገባ ሲሆን ትላንት በአበበ ቢቂላ ስታድየም ሊያደርጉት የነበረውን ልምምድ በዝናብ ምክንያትዝርዝር

አራተኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና የምዘና ውድድር ከነሃሴ 18-29 በሃዋሳ ከተማ ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ በ13 የስፖርት አይነቶች ሲካሄድ በቆየው በዚህ ውድድር በእግርኳስ በሴቶች 7 ፣ በወንዶች ደግሞ 9 ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ተሳታፊ ሆነዋል። በወንዶች ቤኒሻንጉል ፣ በሴቶች ደቡብ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ትላንት በተከናወነው የሴቶች የፍጻሜ ጨዋታ ደቡብዝርዝር

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ2017ቱ የጋቦን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ዛሬ ሃዋሳ ኢንተርናሽናል ስታድየም ከሲሸልስ ጋር አድርጎ በድል አጠናቋል። የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ የሆኑት አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ ከጨዋታው በኃላ አስተያየታቸውን ሰተዋል። ስለ ጨዋታው “ዛሬ ካሰብነው ነገር አንጻር 100% እቅዳችንን አሳክተናል ማለት ባይቻልም ማሸነፍ ስለሆነ ዋነኛ ግባችን በማሸነፋችን ደስተኞች ነኝ፡፡ ነገር ግንዝርዝር

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ራሱን ከእግርኳስ ተጫዋችቸነት ያገለለው ሙሉጌታ ምህረትን በክብር ለመሸኘት የመሸኛ ጨዋታዎች እንደሚዘጋጁ ዛሬ በሃዋሳ ሴንትራል ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ተደርጓል። የሽኝት ጨዋታው አዘጋጅ ኮሚቴ አባል ከሆኑት መካከል አቶ ሲሳይ አድርሴ ስለ ዝግጅቱ ሲናገሩ “ዋና አላማችን በእግር ኳስ ያገለገሉንን ባለውለታዎቻችንን ለማመስገን እና እንደዚህ አይነት ዝግጅቶችን በሃገራችን ለማስለመድ ነው።ዝርዝር

በሁለት ምድቦች ተከፍሎ በ32 ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የቆየው የ2008  የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ ከቀኑ 7፡00 በተደረገው የደረጃ ጨዋታ ወልድያ ከ አዲስ አበባ ከተማ መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1-1 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል፡፡ ኃይሌ እሸቱ አዲስ አበባ ከተማን ቀዳሚ ሲያደርግ ያሬድ ሀሰን ወልድያን አቻዝርዝር

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከጣልያኑ ግዙፍ የትጥቅ አምራች ኤሪያ ጋር የትጥቅ አቅርቦት ውል ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱ ከ1 ወር በፊት ቢፈፀምም ይፋ የተደረገው ዛሬ ነው፡፡  ኤሪያ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድኖች እንደየደረጃቸው የትጥቅ አቅርቦት ለ4 ዓመት ለማቅረብ ሲስማማ ውሉ ግን በሁለቱ ወገኖች ስምምነት በየአመቱ እንደሚታደስ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 በጣሊያን ባህል ማዕከል በተሰጠዝርዝር

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2008 የውድድር ዘመን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያለፉትን ክለቦች ለይቷል፡፡ ወልድያም ከ2 ሳምንት በፊት ወደ ሊጉ ማደጉን አረጋግጧል፡፡ ለቡድኑ ስኬታማነት ቁልፍ ሚና ከተወጡት መካከል አንጋፋው የቡድኑ አምበል ዮሃንስ ኃይሉ እና ግብ አዳኙ እዮብ ወልደማርያም ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ያደረጉትን ቆይታ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ “የስኬታችን ምስጢር አንድነታችን ነው” ዮሃንስ ኃይሉ ስለዝርዝር

በ2007 ከፕሪሚየር ሊጉ የወረደው ወልድያ በአዲስ መልክ በተዋቀረው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የዘንድሮ የውድድር ዘመን 3 ጨዋታ እየቀረው በአመቱ ወደ ፕሪሚየር ሊግ መመለሱን አረጋግጧል፡፡ ወልድያ ወደ ሊጉ ለመመለስ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን ከማሰባሰቡ በተጨማሪ የቀድሞው የመከላከያ እና ደደቢት አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ትልቁን ሚና ተጫውተዋል፡፡ በመጀመርያ የወልድያ የውድድር ዘመናቸው ክለቡን ወደ ፕሪሚየር ሊጉዝርዝር

የ2008 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሊጠናቀቅ ተቃርቧል፡፡ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የተላቀሉት አራት ክለቦች ከወዲሁ የተለዩ ሲሆን ከነዚህም መካከል በምድብ ለ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ ከ2 ሳምንት በፊት ወደ ሊጉ ማደጉን አረጋግጧል፡፡ ክለቡ በሚከተለው በኳስ ቁጥጥር ላይ ያመዘነ እንቅስቃሴ ላይ ውበት እንዲላበስ ቁልፍ ሚና እየተወጣ የሚገኘው ባለ ክህሎቱ አማካይ ሙሃጅርዝርዝር