ሚካኤል ለገሰ (Page 92)

በሚካኤል ለገሰ ከሁለት ቀናት በፊት ቢሾፍቱ ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በተባበር የተጫዋቾች የደሞዝ ጉዳይ ላይ ውይይት በማድረግ ከፍተኛው የክፍያ መጠንን መገደቡ ይታወሳል።በዚህ መሰረት የተጫዋቾች የደሞዝ ጣሪያ 50ሺ ብር እንዲሆን ተወስኗል።  ከዚህ ቀደም የጉዳዩ አሳሳቢነት ማለትም የተጫዋቾች ክፍያ በየጊዜው እያሻቀበ መምጣት በግልፅ የሚታይ እንደመሆኑ ውሳኔው መነጋገርያ መሆኑዝርዝር

በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ ፋሲል ከነማ የታንዛንያው አዛምን በባህር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም አስተናግዶ 1-0 አሸንፏል። በጨዋታው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ፣ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ሙሉቀን አየሁ፣ የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሙሉቀን አዳነ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ጨምሮ በርካታ ደጋፊዎችዝርዝር

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ፋሲል ከነማ ከታንዛንያው አዛም ጋር የሚያደርገው ጨዋታ የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት እንደሚያገኝ ታውቋል። ሃዋሳ ከተማን በመለያ ምት በማሸነፍ ወደ አህጉራዊ ውድድሮች በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ያመሩት ፋሲል ከነማዎች እሁድ ከታንዛኒያው ክለብ አዛም ጋር የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በባህር ዳር ዓለምአቀፍ ስታዲየም የሚደረገው ይህ ጨዋታም በአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት (አማራዝርዝር

በዓመቱ መጨረሻ ከአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ጋር የተለያዩት የጣናው ሞገዶቹ ዛሬ በይፋ ፋሲል ተካልኝን አሰልጣኝ አድርገው ማስፈረማቸውን አስታውቀዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ፋሲል ተካልኝ ወደ ክለቡ እንደሚመጣ መነገሩ የሚታወስ ሲሆን አሰልጣኙ በብሄራዊ ቡድን ግዳጅ ላይ በመገኘቱ ይፋዊ ስምምነት ሳይደረግ ቆይቷል። አሰልጣኙን ማጣት ያልፈለጉት ባህር ዳሮች ቀደም ብለው ድሬዳዋ ድረስ በማቅናት ቅድመ ስምምነት ማድረጋቸውምዝርዝር

ባህር ዳር ከተማዎች ከአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ጋር ከተለያዩ በኋላ ፊታቸውን ወደ ፋሲል ተካልኝ አዙረዋል። ከአምስት ወራት በፊት አዲስ አመራር የሾመው ቡድኑ በ2012 ፕሪምየር ሊግ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ የመጀመሪያ ስራውን የአሰልጣኝ ቅጥር አድርጓል። ቡድኑ በመጀመሪያ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን ለማምጣት አስቦ ሲንቀሳቀስ የነበረ ቢሆንም ከአሰልጣኙ ጋር ሳይስማሙ ቀርተው ድርድሩ ተቋርጧል። በመቀጠልም ፊታቸውንዝርዝር

የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ጅማ አባ ጅፋር ዘንድሮ በበጀት ምክንያት ለተጨዋቾቹ ደሞዝ መክፈል ባለመቻሉ ቅሬታቸውን ለፌዴሬሽኑ ማሳወቃቸው የሚታወስ ሲሆን በዓመቱ አጋማሽ የፈረመው ኦኪኪ አፎላቢም ደሞዝ እንዳልተከፈለው በመግለፅ ከክለቡ ጋር ለመለያየት እንደወሰነ ወኪሉ ገልጿል። የተጫዋቹ ወኪል ኸሪተጅ ሶከር ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ተወካይ የሆነው ሳምሶን ናስሮ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፀው ከሆነ ክለቡ ለደንበኛቸውዝርዝር

በግብፅ አስተናጋጅነት በተከናወነው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በቴክኒክ ጥናት ቡድን ውስጥ ተካተው በሥፍራው የነበሩት አብርሃም መብራቱ (ኢንስትራክተር) ግብፅ ላይ ሲሰሯቸው ስለነበሩ ሥራዎች፣ ስላገኙት ልምድ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዛሬ በጁፒተር ሆቴል በነበረ መግለጫ ገለፃ አድርገዋል። አሰልጣኙ በተመደቡበት የአሌክሳንድሪያ ግዛት የነበሩ ቡድኖችን አቋም ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር ሲተነትኑ እንደነበረ ያስረዱ ሲሆን በተለይ የቡድኖቹንዝርዝር

በአር ሲ በርካን እና ዛማሌክ መካከል የተደረገውን የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ የመራው በዓምላክ ተሰማ በወቅቱ የሞሮኮ ሮያል እግርኳስ ፌደሬሽን እና የካፍ ሁለተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት ፋውዚ ሌካ ጥቃት እንደተሰነዘረበት ይታወሳል። በዓምላክ ጨዋታውን በመራበት መንገድ ደስተኛ ያልነበሩት የዓመቱ “የካፍ ይድነቃቸው ተሰማ ሽልማት” አሸናፊ እና የኤሲ በርካን የክብር ፕሬዝዳንት ፋውዚ ሌካ በዓምላክዝርዝር

በፈረንሳይ አስተናጋጅነት በተከናወነው የ2019 የሴቶች የዓለም ዋንጫ ላይ በዋና ዳኝነት የተሳተፈችው ሊዲያ ታፈሰ እንዲሁም ዓርብ በተጠናቀቀው የ2019 የካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በዋና እና በረዳት ዳኝነት የተሳተፉት በዓምላክ ተሰማ እና ተመስገን ሳሙኤል ስለነበራቸው ቆይታ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫው ከተገኙት ሦስቱ ዳኞች በተጨማሪም የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ በቦታው ተገኝተውዝርዝር

የ2020 የቻን ውድድር ላይ ለመሳተፍ የማጣሪያ ጨዋታውን ለማድረግ በዝግጅት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጂቡቲው ጋር ላለበት የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅቱን በአዳማ እያደረገ ይገኛል። ይህንን አስመልክቶም ዛሬ ከሰዓት በጁፒተር ሆቴል መግለጫ ተሰጥቷል። የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ (ኢንስትራክተር) እና የቡድኑ አምበል አስቻለው ታመነ በሰጡት የ45 ደቂቃ መግለጫ ወቅታዊ የቡድኑ ዜናዎችዝርዝር