ሚካኤል ለገሰ (Page 95)

የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ጅማ አባ ጅፋር ዘንድሮ በበጀት ምክንያት ለተጨዋቾቹ ደሞዝ መክፈል ባለመቻሉ ቅሬታቸውን ለፌዴሬሽኑ ማሳወቃቸው የሚታወስ ሲሆን በዓመቱ አጋማሽ የፈረመው ኦኪኪ አፎላቢም ደሞዝ እንዳልተከፈለው በመግለፅ ከክለቡ ጋር ለመለያየት እንደወሰነ ወኪሉ ገልጿል። የተጫዋቹ ወኪል ኸሪተጅ ሶከር ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ተወካይ የሆነው ሳምሶን ናስሮ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፀው ከሆነ ክለቡ ለደንበኛቸውዝርዝር

በግብፅ አስተናጋጅነት በተከናወነው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በቴክኒክ ጥናት ቡድን ውስጥ ተካተው በሥፍራው የነበሩት አብርሃም መብራቱ (ኢንስትራክተር) ግብፅ ላይ ሲሰሯቸው ስለነበሩ ሥራዎች፣ ስላገኙት ልምድ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዛሬ በጁፒተር ሆቴል በነበረ መግለጫ ገለፃ አድርገዋል። አሰልጣኙ በተመደቡበት የአሌክሳንድሪያ ግዛት የነበሩ ቡድኖችን አቋም ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር ሲተነትኑ እንደነበረ ያስረዱ ሲሆን በተለይ የቡድኖቹንዝርዝር

በአር ሲ በርካን እና ዛማሌክ መካከል የተደረገውን የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ የመራው በዓምላክ ተሰማ በወቅቱ የሞሮኮ ሮያል እግርኳስ ፌደሬሽን እና የካፍ ሁለተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት ፋውዚ ሌካ ጥቃት እንደተሰነዘረበት ይታወሳል። በዓምላክ ጨዋታውን በመራበት መንገድ ደስተኛ ያልነበሩት የዓመቱ “የካፍ ይድነቃቸው ተሰማ ሽልማት” አሸናፊ እና የኤሲ በርካን የክብር ፕሬዝዳንት ፋውዚ ሌካ በዓምላክዝርዝር

በፈረንሳይ አስተናጋጅነት በተከናወነው የ2019 የሴቶች የዓለም ዋንጫ ላይ በዋና ዳኝነት የተሳተፈችው ሊዲያ ታፈሰ እንዲሁም ዓርብ በተጠናቀቀው የ2019 የካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በዋና እና በረዳት ዳኝነት የተሳተፉት በዓምላክ ተሰማ እና ተመስገን ሳሙኤል ስለነበራቸው ቆይታ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫው ከተገኙት ሦስቱ ዳኞች በተጨማሪም የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ በቦታው ተገኝተውዝርዝር

የ2020 የቻን ውድድር ላይ ለመሳተፍ የማጣሪያ ጨዋታውን ለማድረግ በዝግጅት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጂቡቲው ጋር ላለበት የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅቱን በአዳማ እያደረገ ይገኛል። ይህንን አስመልክቶም ዛሬ ከሰዓት በጁፒተር ሆቴል መግለጫ ተሰጥቷል። የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ (ኢንስትራክተር) እና የቡድኑ አምበል አስቻለው ታመነ በሰጡት የ45 ደቂቃ መግለጫ ወቅታዊ የቡድኑ ዜናዎችዝርዝር

የ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ መደረግ ሲጀምሩ ባህር ዳር ላይ ባህር ዳር ከተማ በሜዳው ከወላይታ ድቻ ጋር ነጥብ ተጋርቷል። እምብዛም ደጋፊዎች ባልተገኙበት ጨዋታ ባለሜዳዎቹ ባህር ዳሮች በአንፃራዊነት ተጭነው ሲጫወቱ ድቻዎች ደግሞ ወደ ራሳቸው የግብ ክልል ተጠግተው በመከላከል ጨዋታቸውን አከናውነዋል። ባለሜዳዎቹ በ27 ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ከተጠቀሙበት 11 ተጫዋቾች አምስትዝርዝር

ፋሲል ከነማ እና ባህር ዳር ከተማ ራሳቸውን በፋይናንስ ለማጠናከር እና በዘለቄታዊነት የገንዘብ እጥረታቸውን ለመቅረፍ የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ። ይጀመራል ተብሎ ከታሰበበት ሰዓት አንድ ሰዓት ዘግይቶ የተጀመረው ዝግጅት በርካታ ሃሳቦች የተነሱበት ሲሆን ስለ ስምምነቱ ዝርዝር ጉዳይ ተብራርቶበታል። በባህር ዳር ናኪ ሆቴል በተደረገው ዝግጅት የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ሙሉቀን ዓየሁ፣ የጎንደር ከተማዝርዝር

በባህር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም የተከናወነው የባህር ዳር ከተማ እና የወልዋሎ ዓ/ዩኒቨርስቲ ጨዋታ 0-0 ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች የሚከተለውን ብለዋል። “ውጤቱ የሚያስከፋ አይደለም።” ሚሊዮን ታዬ (ምክትል አሰልጣኝ) – ባህር ዳር ከተማ ስለ ጨዋታው ጨዋታው የደረጃ ለውጥ ስለሚያመጣ ሁለታችንም በጥንቃቄ ነበር ያከናወነው። ወልዋሎዎች በጣም የተደራጀ ቡድን ነው ያላቸው። ያንን ለመለየት 15ዝርዝር

በ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ባህር ዳር ላይ የተገናኙት ባህር ዳር ከተማ እና ወልዋሎ ዓ/ዩኒቨርስቲ ጨዋታቸውን 0-0 አጠናቀዋል። ባለሜዳዎቹ ባህር ዳር ከተማዎች በ25ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ወደ መቐሌ አምርተው በደደቢት 5-2 ከተሸነፉበት ጨዋታ ሰባት ተጨዋቾችን በጉዳት እና በቅጣት ምክንያት ቀይረው ወደ ሜዳ ገብተዋል። በዚህም ሃሪስተን ሄሱ፣ አሌክስ አሙዙ፣ሄኖክ አቻምየለህ፣ ሚካኤልዝርዝር

በባህር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም የተደረገው የባህር ዳር ከተማ እና የድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ 2-1 በባለሜዳዎቹ አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች የሚከተለውን ብለዋል። “ተጫዋቾቼ የሚከፈለውን መስዋትነት ከፍለዋል፣ በዚህም አሸንፈን ወጥተናል።” ጳውሎስ ጌታቸው (ባህር ዳር ከተማ) ስለ ጨዋታው በአጠቃላይ ተጫዋቾቼ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ከፍለዋል። ምክንያቱም ብዙ ነጥቦችን ጥለን ስለመጣን የዛሬው ጨዋታ እጅግ ያስፈልገንዝርዝር