ሶከር ኢትዮጵያ

ለኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የስፖርት ብራ (ቦዲ ኬር) ድጋፍ በአቶ ዳዊት ጌታቸው እንደተደረገ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በጨዋታ ጊዜ በሚከሰት ግጭት በጡት ላይ የሚገጥም አደጋን ለመከላከል የሚረዳ የጡት መከላከያን በቦስተኔ ነዋሪ በሆኑት አቶ ዳዊት ጌታቸው አማካኝነት በፌዴሬሽኑ አዳራሽ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ አቶ ባሕሩ ጥላሁን፣ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው እና የሉሲዎቹ አምበል ሎዛ አበራ በተገኙበት መበርከቱንም ፌዴሬሽኑ ባሰራጨው መረጃ ገልጿል። አቶ ዳዊትዝርዝር

በዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣርያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥመው የዚምባብዌ ብሔራዊ ቡድን ስብስቡን አሳውቋል። የ2022 የዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ጨዋታዎች ከወሩ መጨረሻ ጀምሮ መከናከናቸውን ይጀምራሉ። ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባብዌ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያም ወደ ኬፕ ኮስት አምርታ ጋናን በመግጠም የምትጀምር ሲሆን ከሦስት ቀናት በኋላ ዚምባብዌን በባህር ዳር ስታዲየም ታከናውናለች። ጳጉሜ 2ዝርዝር

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት አካል የሆኑ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን እንደሚያደርግ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነሐሴ 28 ከጋና (ከሜዳው ውጪ) እንዲሁም ጳጉሜ 2 ከዚምባብዌ (በሜዳው) በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የ2022 የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጉዞውን የሚጀምር ሲሆን ለእነዚህ የማጣርያ ጨዋታዎችም በአዳማ ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ። በቀጣይ ሳምንት ደግሞ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችንዝርዝር

ለካታሩ የ2022 ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመርያ ሁለት ጨዋታዎቿን በዓመቱ መጨረሻ የምታከናውነው ኢትዮጵያ ጨዋታ የምታደርግባቸው ቀናትን አውቃለች። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው በምድብ 7 ከጋና፣ ዚምባብዌ እና ደቡብ አፍሪካ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ የመጀመርያ ጨዋታዋን ነሐሴ 28 ወደ ጋና አምርታ የምታከናውን ሲሆን ቀጣዩን ጨዋታ ጳጉሜ 2 ላይ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ዚምባብዌንዝርዝር

የ2013 የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በሀዋሳ ከተማ ሲደረግ ቆይቶ ዱራሜ ከተማን አሸናፊ በማድረግ ተጠናቋል። (በብሩክ ሀንቻቻ) በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ከሐምሌ 18 ጀምሮ በአርባ ስድስት ክለቦች በ11 ምድብ ተከፍሎ ሲደረግ የቆየው ወደ አንደኛ ሊግ የሚያልፉ ክለቦችን ለመለየት የተደረገው የ2013 የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ ረፋድ በተደረጉ የደረጃ እና የፍፃሜዝርዝር

በዛሬው ዕለት በተደረጉ ሁለት የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ምስራቅ ክፍለከተማ እና ዱራሜ ከተማን ለፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ (በብሩክ ሀንቻቻ) ወደ 2014 የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ውድድር ላይ ለማለፍ ከሐምሌ 18 ጀምሮ በአርባ ስድስት ክለቦች መካከል በአስራ አንድ ምድቦች ተከፍሎ ሲደረግ በቆየው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ቀደም ብሎ አስራ ሁለትዝርዝር

በሁለት ምድብ ተከፍሎ በአስር ክለቦች መካከል ሲደረግ የቆየው የኢትዮጵያ ሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በአራዳ ክፍለ ከተማ አሸናፊነት በዛሬው ዕለት ተጠናቋል፡፡ (በብሩክ ሀንቻቻ) በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ለመጀመሪያ ከሐምሌ 19 ጀምሮ በሁለት ምድብ ተከፍሎ በአስር ክለቦች መካከል ሲደረግ የቆየው የ2013 የኢትዮጵያ ሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በዛሬው ዕለት በተደረጉ ሁለት መርሀግብሮች ፍፃሜውንዝርዝር

በባህርዳር ከተማ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እያለው ለሰበታ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና በቀጣዩ ዓመት ለመጫወት ፊርማውን ያኖረው አጥቂ በብዙሀኑ ዘንድ መነጋገሪያ እየሆነ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾች የዝውውር ገበያው ከተከፈተ በኋላ በርካታ ተጫዋቾች ወደ ተለያዩ ክለቦች እያመሩ ይገኛሉ፡፡ ካለፉት ዓመታት አንፃር ዘንድሮ ይበልጥ ከፍተኛ ገንዘብ ለዝውውር እየተሰጠም እንደሚገኝ ሰምተናል፡፡ ምንምዝርዝር

ሀዲያ ሆሳዕና በተጫዋቾቹ የቀረበበትን ክስ ተከትሎ የተላለፈበት የእግድ ውሳኔን ተግባራዊ ባለማድረጉ የእግድ ውሳኔ እንደተላለፈበት ታውቋል። ለረጅም ጊዜያት በዘለቀው የክለቡ እና ተጫዋቾቹ ውዝግብ መነሻነት የፌዴሬሽኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴ የቀረበለትን ክስ መርምሮ የዛሬ ወር ክለቡ በአስራ አምስት ተጫዋቾች ላይ የወሰነውን የሁለት ዓመት ዕግድ በመሻር በውላቸው መሠረት ክፍያቸውን እንዲፈፅም መወሰኑ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም ክለቡዝርዝር

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባህር ዳር ከተማ የሚካሄደው ከ23 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድርን አስመልክቶ በፌዴሬሽኑ ስር የሚገኘው የሴካፋ ውድድር አዘጋጅ ብሔራዊ ኮሚቴ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። የኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ አበበ ገላጋይ እና የፌዴሬሽኑ ም/ዋና ፀሐፊ እና የኮሚቴው ፀኃፊ የሆኑት አቶ ሰለሞን ገብረሥላሴ በሰጡት መግለጫ ላይ የዝግጀቱ ሁኔታ ማብራርያዝርዝር