ቴዎድሮስ ታከለ

ወላይታ ድቻ የአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ረዳትን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡ አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን በማጣመር የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በመቀመጫ ከተማው ሶዶ እየሰራ የሚገኘው ወላይታ ድቻ በየትኛውም የቅድመ ውድድር ዋንጫ ላይ በበጀት እጥረት የተነሳ እንደማይሳተፍ ሶከር ኢትዮጵያ ያረጋገጠች ሲሆን በቀጣዩ ቀናት በሚገኙ የአቋም መፈተሻ የወዳጅነት ጨዋታዎች ግን ራሱን ለመፈተሽ እቅድ ይዟል፡፡ዝርዝር

አምስት የፕሪምየር ሊግ ክለቦችን ተሳታፊ የሚያደርገው የሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአት በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ሌዊ ሪዞርት ተካሂዷል፡፡ በሲዳማ ክልል እግርኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በጎፈሬ የትጥቅ አምራች ተቋም ስፖንሰር አድራጊነት የ2014 የሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ በሚል ስያሜ በአምስት የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች መካከል በሀዋሳ ከተማ ቀደም ተብሎ ከተያዘለት ቀን በአንድ ወደፊትዝርዝር

ሀድያ ሆሳዕና የመስመር አጥቂውን በአንድ ዓመት ውል ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡ በአዲሱ አሰልጣኙ ሙሉጌታ ምህረት እና ረዳቶቹ መሪነት ከሳምንታቶች በፊት በመቀመጫው ሆሳዕና ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የጀመረው ሀድያ ሆሳዕና በሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ላይ ለመካፈል ከአንድ ቀን በፊት ወደ ሀዋሳ በመምጣት በሴንትራል ሆቴል ማረፊያውን በማድረግ በርከት ያሉ አዳዲስ ፈራሚዎችን ከነባሮቹ ጋር በማቀናጀትዝርዝር

አዲስ አበባ ከተማ ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአስራ ሦስቱን ውል አድሷል፡፡ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ስር በመወዳደር ላይ የሚገኘው አዲስአበባ ከተማ ለቀጣዩ የ2014 የውድድር ዓመት ጊዜያዊ አሰልጣኝ የነበረችው የሺሀረግ ለገሰን በዋና አሰልጣኝነት እንድትቀጥል ሲያደርግ ዘጠኝ ተጫዋቾችን ከተለያዩ ክለቦች ማስፈረም እና በክለቡ የነበሩ አስራ ሦስት ተጫዋቾች ደግሞ ውላቸውን ማደስዝርዝር

የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየሰሩ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች አምስት ወጣቶችን ወደ ዋናው ቡድን ሲያሳድጉ የወጣት ተጫዋቻቸውን ውልም አራዝመዋል፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ታዳጊ ወጣቶችን በማብቃቱ ረገድ ሊጠቀሱ ከሚችሉ ውስን ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ሀዋሳ አምስት ወጣቶችን በአሰልጣኝ እስራኤል ጊነሞ ከሚመራው ከ20 ዓመት በታች የሀዋሳ ቡድን ያሳደገ ሲሆን ብሩክ ዓለማየሁ (አማካይ)፣ አስችሎምዝርዝር

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ልማት እና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ2022 የኢንተርናሽናል ዳኝነት ባጅ የሚወስዱ ዳኞችን ዝርዝር ለፊፋ ልኳል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ልማት እና አስተዳደር ኮሚቴ ከቀናቶች በፊት በ2022 ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን  ሊመሩ ለሚችሉ ዳኞችን ለፊፋ ለማሳወቅ ለነባር ዳኞች የአካል ብቃት ፈተና እንዲሁም ደግሞ ከነባሮቹ በሚወድቁት ምትክ ለአዳዲስ ዳኞች የአካል ብቃትዝርዝር

የሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዝዮን ተሳታፊው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሦስት ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ብርቱ ተፎካካሪው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለ2014 የውድድር ዘመን ቀደም ብሎ የአሰልጣኝ መሠረት ማኔን ኮንትራት በሁለት ዓመት ካደሰ በኋላ ከአንድ ወር በፊት ከተለያዩ ክለቦች ስድስት አዳዲስ ፈራሚዎችን ማስፈረሙ የሚታወስ ሲሆን ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችንዝርዝር

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን የሚወዳደረው አዲስ አበባ ከተማ ጊዜያዊ አሰልጣኝ የነበረችው የሺሀረግ ለገሰን በዋና አሰልጣኝነት አስቀጥሏል። የሺሀረግ ለገሰ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የዋና አሰልጣኟ ሙሉጎጃም እንዳለ ምክትል በመሆን ስታገለግል ከቆየች በኋላ የዋና አሰልጣኟ ስንብትን ተከትሎ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት የመጨረሻዎቹን የሊግ ሳምንታት መምራት ችላ ነበር።  አሁን ደግሞ ለቀጣዩ የ2014 የውድድር ዘመንዝርዝር

አርባምንጭ ከተማ ኬንያዊ አጥቂ በይፋ አስፈረመ፡፡ ከቀናት በፊት ኬንያዊው የመሐል ተከላካይ በርናንድ አቼንግን በይፋ ወደ ክለቡ መቀላቀል የቻለው አርባምንጭ ከተማ በዛሬው ዕለት ሁለተኛው ኬንያዊ ፈራሚ በማድረግ አጥቂው ኤሪክ ካፓይቶን በአንድ ዓመት ውል ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል፡፡ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በባህርዳር ተዘጋጅቶ በነበረው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ከተመለከቷቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱዝርዝር

በሀዋሳ ከተማ ዝግጅት እየሰሩ የሚገኙት ድሬዳዋ ከተማዎች የሙከራ ዕድል ከተሰጧቸው ተጫዋቾች መካከል ሁለቱን አስፈርመዋል፡፡ በሀዋሳ ከተማ ለቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ2014 ዝግጅትን እየሰሩ የሚገኙት ድሬዳዋ ከተማዎች በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው እየቀላቀሉ የሚገኙ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ለሁለት ሳምንታት በሙከራ ሲመለከቷቸው ከነበሩ ከ15 በላይ ከድሬዳዋ እና አካባቢዋ የመጡ ተጫዋቾች መካከል አሰልጣኙዝርዝር