ቴዎድሮስ ታከለ (Page 162)

የወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለብ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ደጋፊ ካላቸው ክለቦች መሀከል አንዱ ነው። ክለቡ ከተመሰረተበት 2001 ጀምሮ በሶዶ እና ቦዲቲ ከተማ ባሉት ስታድየሞች የሊግ ጨዋታዎቹን ሲያከናውን ቆይቷል። አሁን ላይ ክለቡ የሶዶ ስታድየምን በቋሚነት እየተገለገለበት ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣው የደጋፊው ቁጥር ከስታድየሙ የመያዝ አቅም ጋር የተመጣጠነ ባለመሆኑዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት የዛሬ ብቸኛ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ሶዶ ላይ መሪው ደደቢትን አስተናግዶ በአምረላ ደልታታ ብቸኛ ግብ በማሸነፍ ሁለተኛውን ዙር በድል ጀምሯል፡፡ ከማለዳው ሁለት ሰአት ጀምሮ ወደ ስታድየሙ መትመም የጀመረው የከተማዋ ነዋሪ ረጃጅም ሰልፎችን በመስራት ሰባት ሰዐት ከመሆኑ በፊት ስታድየሙን ሞልቶታል። እድሉን ያላገኘው ቀሪ ደጋፊም በዛፎች ፣ ዳገቶችዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት በሜዳው ሀዋሳ ከተማ ስታድየም ጅማ አባ ጅፋርን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ 1-0 በማሸነፍ ሁለተኛው የውድድር ዘመን አጋማሽን በድል አሟሽቷል፡፡ እንደተለመደው በኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ታጅቦ በተጀመረው ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ በኩል ዳንኤል ደርቤን ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኃላ በመጀመርያ አሰላለፍ ውስጥ ሲካተት ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር በዝግጅትዝርዝር

የፕሪምየር ሊጉ ክለብ አዳማ ከተማ በቅርቡ ከሀዋሳ ከተማ ጋር የተለያየው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ፍርዳወቅ ሲሳይን ማስፈረም ችሏል። በሀዋሳ ከተማ የመደበኛ ተሰላፊነት እድልን ማግኘት ያልቻለው ፍርዳወቅ በአንደኛው ዙር የመጨረሻ ጨዋታዎች ላይ መጫወት ቢችልም በተጠበቀው ልክ ክለቡን ማገልገል አልቻለም በሚል ምክንያት ቀሪ የ6 ወራት ኮንትራት እያለው በስምምነት አፍርሶ ከሀዋሳ ከተማ ጋር መለዬየቱዝርዝር

ዛማሌክን በመለያ ምቶች አሸንፎ ወደ ሁለተኛው ዙር ያለፈውና ትላንት በካይሮ በወጣው የእጣ ማውጣት ስነስርዓት ከታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ ጋር የተደለደለው ወላይታ ድቻ ትላንት ከሀዋሳ ወደ ሶዶ ሲያመራ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ አቀባበል ያደረገለት ሲሆን ምሸት ላይ ደግሞ ለቡድኑ አባላት የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡  በትላንቱ ዝግጅት ላይ የወላይታ ዞን አስተዳደር በአስተዳዳሪው አቶ አስራትዝርዝር

በያዝነው አመት በርካታ የአስተዳደራዊ እና የአሰልጣኝ ቡድን አባላት ለውጥ ያደረገው አርባምንጭ ከተማ አሁኝ ደግሞ ነባር ተጫዋቾችን ከክለቡ እያሰናበተ ሌሎች አዳዲስ ተጨዋቾችን ከከፍተኛ ሊግ እና አንደኛ ሊግ ክለቦች እያስፈረመ እና በሙከራ ላይ እያየ ይገኛል። በዚህም ሂደት ውስጥ ክለቡ በቡድኑ ውስጥ ደካማ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው ካላቸው ሶስት ተጨዋቾች ጋር  በስምምነት መለያየቱ ተሰምቷል።ዝርዝር

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ዛማሌክን በደርሶ መልስ ጫወታ ከውድድሩ ውጭ ያደረገው ወላይታ ዲቻ ወደ ሀዋሳ ሲደረስ በበርካታ ህዝብ ታጅቦ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ ዛሬ ማለዳ ጠዋት ወደ አዲስ አበባ ሲገባ አቀባበል የተደረገለት ክለቡ 9:00 ገደማ ሀዋሳ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ አንስቶ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ተቀብሎታል። በበርካታ መኪኖች ፣ ሞተር ሳይክሎችዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮው የውድድር ዘመን በሊጉ ወጣ ገባ አቋም እያሳየ የሚገኘው ሀዋሳ ከተማ በፈለግኩት ልክ አላገኘዋቸውም ካላቸው ሁለት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ተለያይቷል። ከክለቡ የተስፋ ቡድን በ2007 ወደ ዋናው ቡድን ያደገው ፍርዳወቅ ሲሳይ በ2008 የውድድር ዘመን ፕሪምየር ሊጉ ላይ 8 ግቦችን አስቆጥሮ የበርካቶች አይን ውስጥ ቢገባም ያለፉትን ሁለት አመታት ግንዝርዝር

ወላይታ ድቻ ለመጀመርያ ጊዜ እየተሳተፈበት በሚገኘው የአፍሪካ መድረክ ብዙዎችን ባስገረመ መልኩ ከአፍሪካ ሃያላን አንዱ የሆነው ዛማሌክን ከውድድር በማስወጣት ወደ ሁለተኛው ዙር አልፏል። በ2001 የተመሰረተው ወላይታ ድቻን ከምስረታው ጀምሮ ሲያሰለጥን የቆየውና ከወራት በፊት ከክለቡ ጋር የተለያየው መሳይ ተፈሪ ከትላንት ምሽቱ ጨዋታ በኋላ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጠው አስተያየት በውጤቱ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል። ”ዝርዝር

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመርያ ዙር የመልስ ጨዋታ ነገ ዛማሌክን የሚገጥመው ወላይታ ድቻ ትላንት 42 የልዑካን ቡድን አባላትን አካቶ ወደ ስፍራው በማቅናት ኖቫ ሆቴል ማረፊያውን አድርጓል። የጦና ንቦች ትላንት ከሰአት በካይሮ ስታዲየም ሁለተኛ የመለማመጃ ሜዳ ላይ የመጀመርያ ልምምዳቸውን የሰሩ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ጨዋታውን በሚያደርጉበት አል ሰላም ስታድየም በእኛ አቆጣጠር 1 ሰአትዝርዝር