ቴዎድሮስ ታከለ (Page 163)

በ28ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የደቡብ ደርቢ ይርጋለም ላይ የተገናኙት ሲዳማ ቡና እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታቸውን ያለግብ አጠናቀዋል። አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የተከታተሉት ይህ ጨዋታ ሲዳማ ቡና የደበዘዘው የዋንጫ ተስፋን ለማለም እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ካለበት የመውረድ ስጋት ከመላቀቅ አንፃር ብርቱ ትግል ያደረጉበት ነበር። በጨዋታውም  እንዳለ ከበደ ፣ዝርዝር

በ27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ላይ ወልድያን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ 2-1 በማሸነፍ ከተከታታይ ሶስት ሽንፈት በኋላ ወደ ድል መመለስ ችሏል፡፡ ጨዋታው በርካታ ቁጥር ባለው ተመልካች ታጅቦ የተካሄደ ሲሆን በተለይም ከወልድያ በአዲስ አበባ አድርገው ሀዋሳ የገቡት እጅግ ረጅም እና አድካሚ ጉዞ ማድረጋቸው ሳይበግራቸው ቡድናቸውን ሲያበረታቱ ውለዋል፡፡ በጨዋታው ሙሉ ክፍለጊዜ ባለሜዳውዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኝ የነበረው ወላይታ ድቻ ለቀጠናው እጅግ ቀርቦ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክን አስተናግዶ 1-0 በማሸነፍ ላለመውረድ በሚያደርገው ፉክክር ላይ ወሳኝ የሆነ 3 ነጥብ መሰብሰብ ችሏል፡፡ ከጨዋታው መጀመር በፊት የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ በስታድየሙ በመዞር የታደሙትን ተመልካቾች ሲያበረታቱ እና ለድጋፍ ሲያነሳሱ ተስተውሏል፡፡ዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት አርባምንጭ ላይ መከላከያን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረ ግብ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል አርባምንጭ ከተማ ከተማ ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ ለጨዋታው ትኩረት የሰጠ በሚመስል መልኩ በሙሉው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የተሻለ መንቀሳቀስ ችለዋል፡፡ በመጀመሪያው 15 ደቂቃዎች ላይ አዞዎቹ በእንግዳው ቡድን ላይ እጅግ በርካታ የግብዝርዝር

በ24ኛው ሳምንት የኢትየጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሶዶ ላይ ሀዋሳ ከተማን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ 1-0 በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠናው የወጣበትን ድል አስመዝግቧል፡፡ ቶማስ ስምረቱን በጉዳት ሳይዙ የገቡት ወላይታ ድቻዎች በ4-4-2 አሰላለፍ ወደ ሜዳ ሲገቡ መላኩ ወልዴ ፣ መሳይ ጳውሎስ እና መሀመድ ሲይላን በጉዳት ያጡት ሀዋሳ ከተማዎች በበኩላቸው በ4-2-3-1 አሰላለፍ ገብተዋል፡፡ ሶሆሆ ሜንሳህም የተጣለበትዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት የወንድማማቾች ደርቢ በሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና መካከል ተካሂዶ በተመጣጣኝ ፉክክር እና የድንጋይ እሩምታ ታጅቦ በሀዋሳ ከተማ 3-2 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ከሌላው ጊዜ በተለየ ከቀትር ጀምሮ የስታድየሙ ወንበሮች በደጋፊዎቻቸው ተሞልቶ እጅግ ማራኪ በሆነ ዝማሬ ታጅቦ በተጀመረው ጨዋታ በመጀመርያዎቹ  15 ደቂቃዎች ፋተታ የማይሰጥ እንቅስቃሴ ያደረገው ሀዋሳ ከተማዝርዝር

  የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ዛሬ ሲካሄዱ የሊጉ ቻምፒዮንነት እና ላለመውረድ የሚደረጉት ፉክክሮች ይበልጥ አጓጊ መልክ የሚይዙባቸው ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡   ወላይታ ድቻ 1-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ሶዶ ያቀናው የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወላይታ ድቻ ጋር ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዳነ ግርማ ጎል 1-0 በመምራትዝርዝር

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ዛሬም ቀጥሎ ሲውል ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ፋሲል ከተማን አስተናግዶ 2-0 በማሸነፍ በድንቅ መሻሻሉ ቀጥሏል፡፡ በዛሬው ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ ስታድየም ከሌላው ጊዜ በተለየ እጅግ አስደናቂ የሆነ የደጋፊ ድባብ የታየ ሲሆን ስታድየሙም በተመልካች ተሞልቶ ነበር፡፡ ረጅም ኪሎሜትር አቋርጠው የመጡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፋሲል ከተማ ደጋፊዎችም በስፍራው መገኘትዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 15ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች ትላንት እና ዛሬ ሲካሄዱ ሀዋሳ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በ09:00 ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲን የገጠመው ሀዋሳ ከተማ 4-2 በማሸነፍ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን መከተሉን ቀጥሏል፡፡ ሀዋሳ በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴን ማድርግ የቻለ ሲሆን ሮማን ጌታቸው አክርርራ የመታችው ኳስ በቅድስት ማርያሟ ተከላካይዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ከተካሄዱ ጨዋታዎች መካከል ከሜዳው ውጪ ማሸነፍ የቻለው ሀዋሳ ከተማ ብቻ ነው፡፡ ሀዋሳ ከተማ ትላንት መከላከያን 3-0 ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለት ግብ አስቆጥሮ ጃኮ አራፋት ላስቆጠረው አንድ ግብ ጣጣውን ጨርሶ ያቀበለው ጋዲሳ መብራቴ ድንቅ እንቅስቃሴ አሳይቷል፡፡ ጋዲሳ መብራቴ ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት በጨዋታው ልዩነት ፈጣሪ በመሆኑ መደሰቱንዝርዝር