ቴዎድሮስ ታከለ (Page 167)

የኢትዮጵያ ከ17 አመት የ2010 የውድድር ዘመን ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምሯል። በሁለት ምድብ ተከፍሎ የሚደረገው እና በድምሩ 14 ክለቦችን የሚያሳትፈው ውድድር ከየምድቡ አንድ አንድ ጨዋታ ተደርጎበታል።  ምድብ ሀ ሀዋሳ ከተማ 3-2 አዳማ ከተማ እጅግ ጠንካራ ፉክክር በተስተናገደበት እና ሁለቱም ክለቦች ማራኪ እንቅስቃሴን ባደረጉበት ጨዋታ የአምናው ቻምፒዮን ሀዋሳ ከተማ በሜዳው አዳማዝርዝር

ኢትዮጵያ ቡና በዝውውር መስኮቱ ሁለተኛ የውጪ ተጫዋች ዝውውሩን በማጠናቀቅ ሴኔጋላዊው ባፕቲስቴ ፋዬን በእጁ አስገብቷል። ለኢትዮጵያ ቡና የዘንድሮው ደካማ የሊግ ጉዞ ውሰጥ ከሚጠቀሱ ዋነኛ ክፍተቶች መካከል የአጥቂ ክፍሉ ይጠቀሳል። ይህንን ስፍራ ለማጠናከር ዩጋንዳዊው ቦባን ዚሪንቱሳን ያስፈረመው ክለቡ ሴኔጋላዊው ባብቲስቴ ፋዬን በአንድ አመት ውል ማስፈረም ችሏል። ቡና የተጫዋቹን ፊርማ ባለፈው ሳምንት (የዝውውርዝርዝር

ኢትዮጵያ ቡና ዩጋንዳዊው የአጥቂ መስመር ተጫዋች ቦባን ዚሪንቱዛን ማስፈረሙ ታውቋል። በውድድር አመቱ መልካም ያልሆነ ውጤት እያስመዘገበ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ጠባብ የሆነው የማጥቃት አማራጩን ለማስፋት ዚሩንቱዛን በአንድ አመት ኮንትራት ማስፈረም ችሏል። ክለቡ ተጫዋቹን የውጪ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከመጠናቀቁ በፊት ማስፈረሙ የታወቀ ሲሆን ያለፉትን 3 ቀናት በክለቡ ልምምድ ሲሰራ ቆይቷል። በተለያዩ የአጥቂዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ – 1ኛ ዲቪዝዮን ስድስተኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ አንድ ሲጠናቀቅ ወደ ይርጋለም ያቀናው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን 3-0 አሸንፏል። በጨዋታው የመጀመርያዎቹ 15 ደቂቃዎች ሲዳማ ቡናዎች የተሻለ እንቅስቃሴ ማሳየት ቢችሉም ቀስ በቀስ የበላይ መሆን የቻሉት ንግድ ባንኮች በ20ኛው ደቂቃ ከታሪኳ ደቢሶ የተሻማውን ቅጣት ምት ረሂማ ዘርጋው በግንባሯዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ኢትዮ ኤሌክትሪክን አስተናግዶ ያለ ግብ በአቻ ውጤት አጠናቋል፡፡ ባለሜዳዎቹ ሀዋሳ ከተማዎች ሳምንት ይርጋለም ላይ በሲዳማ ቡና ከተሸነፉበት ጨዋታ የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ጉዳት አስተናግዶ የነበረውን አዲስአለም ተስፋዬን በኄኖክ ድልቢ የተኩ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲሱ አሰልጣኛቸው አሸናፊ በቀለ እየተመሩ ጨዋታዉን ያደረጉት ኢትዮ ኤሌክትሪኮችም ከአዳማዝርዝር

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዝዮን 6ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምረዋል። ጌዲኦ ዲላ ከሜዳው ውጪ ድል ያስመዘግብ ድሬዳዋ እና አዳማ ነጥብ ተጋርተዋል። ሀዋሳ ከተማ 0-1 ጌዲኦ ዲላ 09:00 ሰአት ላይ በሀዋሳ ከተማ ስታድየም በተደረገው በዚህ ጨዋታ እንግዶቹ  የእነረቅስቃሴ የበላይነት የነበራቸው ሲሆን አነጋጋሪ የዳኝነት ውሳኔዎች እና ውዝግቦች የጨዋታው አካልዝርዝር

አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ከተቀላቀለበት 2004 ወዲህ አስከፊውን አጀማመር ዘንድሮ አድርጓል። ከ10 ሳምንታት በኋላም በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ተቀምጧል። ክለቡ በተለይ ያለፉትን ሶስት አመታት የፋይናንስ እና አስተዳደራዊ ችግሮች በተደጋጋሚ እየተከሰተበት የመዝለቁ ውጤት ዘንድሮ እየታየ ይመስላል።  በተጫዋቾች እና በዙርያው የሚገኙ ግለሰቦች ላይ ቅሬታን ከማሳደሩ በተጨማሪም በደጋፊው ዘንድ የማያቋርጥ ተቃውሞ እያስተናገደዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ሲዳማ ቡና ትላንት በሜዳው ሀዋሳ ከተማን አስተናግዶ 1-0 አሸንፏል። ሙሉ የጨዋታው ክፍለጊዜ ተጠናቆ አዲስ ግደይ ላይ በተሰራ ጥፋት በተሰጠው የፍፁም ቅጣት ራሱ አዲስ መትቶ የሀዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ ሶሆሆ ሜንሳ መልሶበት የተሻማውን የማዕዘን ምት አዲስ በግንባሩ በመግጨት ሲዳማን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አስጨብጧል። አዲስ ከጨዋታው በኋላዝርዝር

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ዛሬ በአዲስ አበባ እና የክልል ከተሞች በተደረጉ አምስት ጨዋታዎች ሲቀጥል ይርጋለም ላይ በሲዳማ ደርቢ ሀዋሳ ከተማን ያስተናገደው  ሲዳማ ቡና በአዲስ ግደይ የጭማሪ ደቂቃ ግብ በማሸነፍ ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል። የሲዳማ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታ በአከባቢው መጠሪያ  ሩዱዋ ወይም የወንድማማቾች ደርቢ እየተባለ ቢጠራም የሁለቱዝርዝር

አርባምንጭ ከተማ ለ8 ሳምንታት ክለቡን የመሩት አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ከአሰልጣኝነት ካሰናበተ በኃላ ወልዲያን በገጠመበት የ9ኛ ሳምንት ጨዋታ በምክትል አሰልጣኙ በረከት ደሙ እየተመራ ወደ ሜዳ መግባቱ ይታወሳል፡፡  ትላንት ምሽት የክለቡ ቦርድ ባደረገው ረጅም ሰአት የፈጀ ውይይት ከቀረቡት ሰባት አሰልጣኞች መካከል የሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ እዮብ ማለን በዋና አሰልጣኝነት ሾሟል ፡፡  አርባምንጭ ከተማዝርዝር