ቴዎድሮስ ታከለ (Page 2)

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ታደለ መንገሻ የአዳማ ከተማ አምስተኛ ፈራሚ ተጫዋች ሆኗል። በዝውውር ገበያው የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው አዳማ ከተማ ታደለ መንገሻን አምስተኛ ፈራሚው አድርጓል፡፡ በቴክኒክ ችሎታቸው ከሚጠቀሱት መሀል አንዱ የሆነው የቀድሞው የደደቢት፣ ኢትዮጵያ መድን፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አርባምንጭ ከተማ አማካይ ታደለ ከሁለት ዓመት በፊት ዳግም ወደ ቀድሞ ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስዝርዝር

በዝውውር ገበያው እየተሳተፈ የሚገኘው ሀዋሳ ከተማ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል፡፡ ሀዋሳ ከተማን በድምሩ ለአራት ዓመታት በግብ ጠባቂነት ያገለገለው ቶጓዊው ሶሆሆ ሜንሳ ከክለቡ ጋር በመለያየቱ ጋናዊው ግብ ጠባቂ መሐመድ ሙንታሪ በአንድ ዓመት ውል በቦታው ተተክቷል፡፡ ከዚህ ቀደም ለሀገሩ ክለቦች ሚዴአማ፣ አሻንቲ ኮቶኮ እንዲሁም ለዛምቢያው ሉሳካ ዳይናሞስ የተጫወተው እና ለጋና ከ23ዝርዝር

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ መሪነት ወደ ዝውውሩ የገባው አዳማ ከተማ አዲሱ ተስፋዬ እና ዮናስ ገረመውን አስፈርሟል፡፡ ሦስተኛ አዲስ የክለቡ ፈራሚ በመሆን አዳማ የደረሰው ተከላካዩ አዲሱ ተስፋዬ ነው፡፡ የቀድሞው የስልጤ ወራቤ፣ ወላይታ ድቻ እና መከላከያ ተጫዋች ጦሩን ከለቀቀ በኃላ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በሰበታ ከተማ ቆይታን ያደረገ ሲሆን ውሉም በክለቡ መጠናቀቁን ተከትሎዝርዝር

ኢትዮጵያ ቡና የተከላካይ መስመር ተጫዋችን በሦስት ዓመት ውል አስፈረመ፡፡ አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና በዛሬው ዕለት የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ነስረዲን ኃይሉን በሦስት ዓመት ውል ማስፈረሙን አስታውቋል፡፡ የቀድሞ የለገጣፎ እና መከላከያ ተጫዋች በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በመከላከያ ውል እያለው ከተለያየ በኋላ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቶ ጥሩ የውድድር ዓመትን ካሳለፈዝርዝር

አዲስ አሰልጣኝ ከቀጠረ በኃላ ወደ ዝውውሩ በመግባት ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው ሰበታ ከተማ አሁን የተከላካዩን ውል አራዝሟል። በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ለመመራት በቅርብ ይፋ ያደረጉት ሰበታዎች ከከፍተኛ ሊግ ጀምሮ ቡድኑን ፕሪሚየር ሊግ እስከገባበት ጊዜ አንስቶ አሁንም ድረስ እያገለገለ የሚገኘው ጌቱ ኃይለማርያምን ውል ለሁለት ተጨማሪ ዓመት አራዝመዋል፡፡ ሰበታ ከተማ ከከፍተኛ ሊግ ሲያድግ በአምበልነትዝርዝር

ሁለቱ ረጅም የምስረታ ዕድሜ ያላቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኮረንቲያስ ክለብ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት እንደፈፀሙ ክለቡ ይፋ አድርጓል፡፡ ክለቡ በተለያዩ ሀገራት ከሚገኙ ክለቦች ጋር የልምምድ ልውውጥ እና በጋራ የመስራት ዕቅድ የነበረው ሲሆን ይሄንንም ዕቅዱን በዛሬው ዕለት ከብራዚሉ ኮረንትያስ ክለብ ጋር አድርጓል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብነት ገብረመስቀል እና የክለቡዝርዝር

በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር በመግባት የነቃ ተሳትፎን እያደረጉ የሚገኙት ሰበታ ከተማዎች ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን በሁለት ዓመት ውል በእጃቸው አስገብተዋል። አራተኛ ፈራሚ ሆኖ ሰበታ የደረሰው ሳሙኤል ሳሊሶ ነው፡ በመከላከያ ጥሩ ጊዜያትን ካሳለፈ በኃላ 2011 መስከረም ወር ላይ ወደ መቐለ 70 እንደርታ አምርቶ ከክለቡ ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ በመጀመሪያ አመቱ ያሳካው ተጫዋቹዝርዝር

ሰበታ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን በሦስት ዓመት ውል አስፈርሟል። የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ መሐመድ አበራ የቀድሞ አሰልጣኙን ተከትሎ ወደ ሰበታ ከተማ አምርቷል፡፡ ከሀላባ ከተማ ፕሮጀክት ከተገኘ በኃላ ወደ መከላከያ ተስፋ ቡድን በማምራት መቀላቀል የቻለው ወጣቱ ተጫዋች በ2012 የወቅቱ የመከላከያ አሰልጣኝ የነበሩት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ወደ ዋናው ቡድን አሳድገውት በክለቡ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴንዝርዝር

በቃሉ ገነነ ሀዋሳ ከተማን የተቀላቀለ ሁለተኛ አዲስ ፈራሚ ተጫዋች ሆኗል፡፡ በአሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ እየተመራ ወደ ዝውውር ገበያው ጎራ ያለው ሀዋሳ ከተማ ከቀናቶች በፊት ተከላካዩ ፀጋሰው ድማሙን ከሀድያ ሆሳዕና ያስፈረመ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ሁለተኛ ፈራሚ በማድረግ አማካዩ በቃሉ ገነነን በሁለት ዓመት የውል ዕድሜ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡ የቀድሞው የወልቂጤ ከተማ እናዝርዝር

አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን በትናንትናው ዕለት በይፋ የቀጠረው ሰበታ ከተማ የአጥቂው መስመር ተጫዋቹን የመጀመሪያው ፈራሚ አድርጓል፡፡ አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱን ለባህር ዳር ከተማ አሳልፎ ከሰጠ በኃላ የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ በማውጣት ሲያወዳድር የነበረው ሰበታ ከተማ በትናንትናው ዕለት ከተወዳደሩት አስር አሰልጣኞች መካከል ዘላለም ሽፈራውን በቦታው ምርጫው ማድረጉን ዘግበን ነበር፡፡ ክለቡም የአሰልጣኙን ቅጥር ከፈፀመ በኃላዝርዝር