ቴዎድሮስ ታከለ (Page 3)

አርባምንጭ ከተማ ከከፍተኛ ሊግ የተከላካይ አማካይ አስፈረመ፡፡ አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ተካፋዩ አርባምንጭ ከተማ በትላንትናው ዕለት ኬኒያዊውን የመሀል ተከላካይ ኦቼንግን የክለቡ ስድስተኛ ፈራሚ አድርጎ አስፈርሞ የነበረው አርባምንጭ ከተማ ሰባተኛ አዲስ ፈራሚው በማድረግ አቡበከር ሻሚልን በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል፡፡ ከኢትዮጵያ ቡና የተስፋ ቡድን የተገኘው ይህ የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋች በመቀጠል በአዲስ አበባዝርዝር

አዞዎቹ በባህር ዳር ተዘጋጅቶ በነበረው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ለኬንያ ብሔራዊ ቡድን ሲጫወት የነበረውን ተከላካይ አስፈርመዋል፡፡ ከሦስት አመታት በኋላ በድጋሚ የከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ አሸናፊ በመሆን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ዳግም የተመለሰው አርባምንጭ ከተማ ለቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በከተማው አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን በማቀፍ መስራት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ አምስትዝርዝር

የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በከተማው እየሠራ የሚገኘው አዳማ ከተማ የሁለት ተጫዋቾችን ውል ለተጨማሪ ዓመት አድሷል፡፡ ለ2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በአዲሱ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እየተመራ አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን በጥምረት በማቀፍ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በክለቡ መቀመጫ በሆነች አዳማ እየከወነ የሚገኘው አዳማ ከተማ የመስመር ተከላካዩ ሚሊዮን ሰለሞን እና አጥቂው አብዲሳ ጀማልን ውልዝርዝር

ከትናንት በስቲያ አስራ አንድ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ የቀላቀለው አዲስ አበባ ከተማ አሁን ደግሞ የሰባት ነባር ተጫዋቾችን ውል ሲያራዝም ሦስት ታዳጊዎችን ከ20 ዓመት ቡድኑ አሳድጓል፡፡ ሮቤል ግርማ ውሉን አራዝሟል፡፡ ይህ የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ፣ ሲዳማ ቡና እና ጅማ አባቡና የመሀል እና የግራ መስመር ተከላካይ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን አዲስ አበባ ከተማንዝርዝር

አዲሱ የሀዋሳ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ በከተማዋ ለሚገኙ አምስት የታዳጊ ፕሮጀክቶች በርከት ያሉ የኳስ ስጦታዎችን በዛሬው ዕለት አበርክቷል፡፡ የቀድሞው የሲዳማ ቡና እና አዳማ ከተማ እንዲሁም በቅርቡ የሀዋሳ ከተማ ዋና አሰልጣኝ በመሆን በሁለት ዓመት ውል የተሾሙት አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ በሀዋሳ ከተማ በታዳጊ እግርኳስ ላይ ሲለፉ ለነበሩ አምስት ፕሮጀክቶች በርከት ያሉዝርዝር

በሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌድሬሽን አስተናጋጅነት የሲዳማ ዋንጫ ውድድር በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች መካከል በሀዋሳ ከተማ ሊደረግ ነው፡፡ ከተቋቋመ አንደኛ ዓመቱን እየተሻገረ የሚገኘው የሲዳማ ክልል እግርኳስ ፌዴሬሽን በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ የውስጥ እና ሀገር አቀፉ የሆኑ ውድድሮችን በማዘጋጀት አመርቂ ሥራዎችን እየፈፀመ የሚገኝ ሲሆን አሁን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የሲዳማ ዋንጫዝርዝር

ዛሬ ረፋድ አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ከፕሪምየር ሊጉ ወደ ስብስቡ የቀላቀለው አዲስ አበባ ከተማ አሁን ደግሞ ተጨማሪ ስድስት ተጫዋቾችን ከከፍተኛ ሊጉ አስፈርሟል፡፡ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ቢኒያም ጌታቸው አዲሱ የክለቡ ፈራሚ ተጫዋች ሆኗል፡፡ እግር ኳስን በሀምበሪቾ ዱራሜ የጀመረው ይህ የፊት መስመር ተጫዋች ወደ ስልጤ ወራቤ እና አክሱም ከተማ በማምራት ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆንዝርዝር

የከፍተኛ ሊጉ የምድብ ለ ተወዳዳሪው ሀላባ ከተማ የቀድሞው አሰልጣኙን በድጋሚ ሾሟል፡፡ የ2013 የውድድር አመትን በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ስር ታቅፎ ሲወዳደር የነበረው ሀላባ ከተማ በ33 ነጥቦች አራተኛ ደረጃን በመያዝ በአሰልጣኝ ደረጀ በላይ መሪነት ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ለቀጣዩ የ2014 የውድድር ዘመን በድጋሚ ተጠናክሮ ለመቅረብ ያሰበው ክለቡ የቀድሞው አሰልጣኙ አላምረው መስቀሌን በአንድ ዓመት ውልዝርዝር

በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ አስፈርሞ የነበረው አዲስ አበባ ከተማ ተጨማሪ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡ ከከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ አሸናፊ በመሆን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደግ የቻለው አዲስ አበባ ከተማ የነባር ተጫዋቾችን ውል ካራዘመ በኋላ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በከፊል ማረፊያውን በወወክማ በማድረግ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ዝግጅት ከጀመሩ ቀናቶች የሞሉት ክለቡ ከደቂቃዎችዝርዝር

አዲሱ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊው ክለብ አርባምንጭ ከተማ ተጨማሪ ረዳት አሰልጣኝ ሲሾም የነባሮቹን ውል አድሷል፡፡ በአርባምንጭ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ከጀመሩ ሰንበትበት ያሉት አዞዎቹ አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን በጥምረት በማቀፍ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ በዚህም በ2010 የአርባምንጭ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ የነበረው ማቲዮስ ለማን በድጋሚ በረዳት አሰልጣኝነት ሾሟል፡፡ በከፍተኛ ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ በሆነውዝርዝር