በMLS ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው ማረን ኃይለስላሴ እና ቤተ እስራኤላዊው ስንታየው ሳላሊች ግብ አስቆጥረዋል። 👉 ማረን ኃይለስላሴ በምርጥ ብቃት ይገኛል በጥር ወር በውሰት ውል የአሜሪካው ቺካጎ ፋየር ተቀላቅሎ ምርጥ ብቃት በማሳየት የሚገኘው ማረን ኃይለስላሴ ቡድኑ ከአትላንታ ዩናይትድ ጋር አቻ በተለያየበት ጨዋታ አንድ ጎል ስያስቆጥር ጆርጅዮ ኮትስያስ ባለቀ ሰዓት ላስቆጠራት ወሳኝRead More →

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የተመደበበትን ጨዋታ አጠናቆ በመመለስ ላይ የነበረው አርቢትር የመኪና አደጋ አጋጥሞታል። በከፍተኛ ሊግ የምድብ ሀ ውድድር በአሰላ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በዛሬው ዕለትም የ19ኛ ሳምንት ሦስት ጨዋታዎች ተካሂደው ተጠናቀዋል። በጠዋቱ የመጀመርያ ጨዋታ ወሎ ኮምቦልቻን ከቤንች ማጂ ቡና ያገናኘውን መርሐግብር ከሌሎች የውድድር ዳኞች ጋር በመሆን በረዳት ዳኝነት ያጫወተው ኢንተርናሽናል ዳኛRead More →

ኢትዮጵያውያን ዓለምአቀፍ ዳኞች ነገ ታንዛኒያ ላይ የሚደረገውን የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ እንዲመሩ ተመርጠዋል። የ2022/23 የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎች መደረግ ከጀመሩ ሦስት ወራት ተቆጥሯል። የአራተኛ ዙር የምድብ ጨዋታዎች መደረግ የጀመሩ ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ ሁለት ክለቦችን በያዘው ምድብ ሦስት ስር ተደልድለው የሚገኙትን የዩጋንዳው ቫይፐርስ እና የታንዛኒያው ሲምባ ክለብRead More →

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ እና ላይቤሪያ የሚያደርጉት ፍልሚያ በሀገራችን ዳኞች ይመራል። አይቮሪኮስት ለምታስተናግደው የ2023 አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የአህጉራችን ብሔራዊ ቡድኖች የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ። በምድን አስራ አንድ ከሞሮኮ እና ዚምባቢዌ ጋር የተደለደሉት ደቡብ አፍሪካ እና ለይቤሪያ ዚምባቢዌ ከውድድሩ ውጭ መሆኗን ተከትሎ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ለሦስትRead More →

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከሰተው ግጭት ውድመት ያጋጠመው የወልዲያ ስታዲየም ወቅታዊ ሁኔታ ምን ይመስላል ስንል ቀጣዩን ጽሁፍ አሰናድተናል። ለግንባታ 1 ቢሊዮን ብር የፈሰሰበት እና የወልዲያ ከተማ ተወላጅ በሆኑት ሼህ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አላሙዲን የተገነባው የወልዲያ ስታዲየም ቀሪዎቹ የሆቴል ፣ ውሃ ዋና ፣ ሁለገብ ሥፍራው ( መረብ ኳስ ፣ እጅ ኳስን እናRead More →

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስፖርት ሳይንስ እና ሳይኮሎጂ መምህር የሆነው ሳሙኤል ስለሺ በግብ ጠባቂዎች ሥልጠና ዙሪያ የላከልን ፅሁፍ እንደሚከተለው ይነበባል። በሳሙኤል ስለሺ “ፋሲል” ሲባል አብዛኛው የስፖርት ብሎም የእግር ኳስ ቤተሰብ ወደ አዕምሮው የሚመጣው ጃኖ ለባሹ ፋሲል ከነማ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይሄ ስም ከፋሲል ከነማ በተለየ መልኩ ሰሞኑን በተደጋጋሚ እየተነሳRead More →

በሱዳን አስተናጋጅነት በሚደረገው የሴካፋ ከ20 ዓመት ዋንጫ ጨዋታ ላይ በዳኝነት ግልጋሎት ለመስጠት ሁለት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ወደ ስፍራው አምርተዋል፡፡ በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግርኳስ ተቋም በሆነው (ሴካፋ) አዘጋጅነት ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ በሱዳን አስተናጋጅነት ካርቱም ላይ ይከናወናል፡፡ ሰባት ሀገራትን በተሳታፊነት የሚያቅፈው ውድድሩ ቀደም ብሎ ከተቀመጠለት ቀን በአንድ ሳምንት ተራዝሞ የፊታችን ዕርብRead More →

12 ቀናት የቀሩት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና ሥራ አስፈፃሚዎች ምርጫን የተመለከተ መግለጫ ተሰጥቷል። ዛሬ ከሰዓት በእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት የተሰጠው መግለጫ ነሐሴ 22 በጎንደር ከተማ የሚደረገውን ምርጫ የተመለከተ ነበር። በመግለጫው ላይ የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሦስት አባላት እንዲሁም የምርጫው ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሁለት አባላት ተገኝተው በእስካሁኑ የሥራ ሂደታቸው ላይ የመጡበትንRead More →

ኢትዮጵያዊቷ አርቢትር ሊዲያ ታፈሰ በእንስቶች የአፍሪካ ዋንጫ ነገ ምሽት የሚከናወነውን ወሳኝ ጨዋታ እንድትመራ ተመርጣለች። የ2022 የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። አስራ ሁለት ሀገራት በሦስት ምድብ ተከፋፍለው የሚያደርጉት ፍልሚያ ከዛሬ ጀምሮ የምድብ የመጨረሻ መርሐ-ግብሮች የሚደረጉበት ሲሆን በምድብ ሁለት በካሜሩን እና ታንዛኒያ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ አልቢትርRead More →

ከ15 ቀናት በኋላ የሚጀምረው የእንስቶች የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በአርቢትርነት እንዲሳተፉ ከተመረጡ ዳኞች መካከል ሊዲያ ታፈሰ ተካታለች። ከሰኔ 25 ጀምሮ ለሦስት ሳምንታት በሞሮኮ የሚከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በ12 ብሔራዊ ቡድኖች መካከል እንደሚደረግ ይታወቃል። በራባት እና ካዛብላንካ በሚከናወነው ውድድር ላይ በአርቢትርነት የሚሳተፉ ዳኞችን ደግሞ የአፍሪካ እግር ኳስ የበላይ አካል የሆነው ካፍRead More →