ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ብቅ ብሎ በአጭር ጊዜ ተፎካካሪ የሆነው ፋሲል ከነማ ዘንድሮም ዋንጫ ማንሳትን እያለመ የሚጀምረውን የውድድር ዓመት እንደሚከተለው ቃኝተነዋል። ጎንደር ከተማ ላይ መቀመጫውን ያደረገው ፋሲል ከነማ ዘንድሮ 55ኛ የምስረታ በዓሉን እያከበረ ይገኛል። ይህ በዓል ደግሞ አይረሴ ሆኖ በደማቁ እንዲከበር የሊጉን ዋንጫ ማንሳት አማራጭ የሌለው ትልም ይመስላል። እርግጥ ቡድኑRead More →

ነብሮቹ በስብስባቸው ላይ ለውጦችን በማድረግ በአዲሱ የውድድር ዘመን ወጥ አቋም ለማሳየት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል ፤ እኛም በተከታዩ ፅሁፋችን የቡድኑን ዝግጅት ዳሰናል። በ2014 የውድድር ዘመን እጅግ የተቀዛቀዘ አጀማመርን በማድረግ ከመጀመሪያዎቹ ስድስት ጨዋታዎች ሦስት ነጥቦችን ብቻ አግኝተው የነበሩት ነብሮቹ ከዚህ አስከፊ አጀማመር መልስ ምንም እንኳን በወጥነት ውጤቶችን ለማስመዝገብ ቢቸገሩም ዓመቱን ከወራጅ ቀጠና በጥቂቱRead More →

ኢትዮጵያ ቡና ራሱን በአዲስ መልክ አደራጅቶ ለሊጉ ፍልሚያ ያዘጋጀበትን መንገድ በቀጣዩ ፅሁፋችን ተመልክተነዋል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከጀመረ አንስቶ በተሳታፊነት ከቆዩ ሁለት ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ኢትዮጵያ ቡና 25ኛ የውድድር ዓመቱን ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል። አንድ ጊዜ ቻምፒዮን መሆን የቻሉት ቡናዎች ያለፈው ዓመት ጉዟቸው እንዳሰቡት ስኬታማ አልነበረም። የመጀመሪያ ድሉን ለማሳካት አምስት ሳምንታትRead More →

ከሦስት የውድድር ዘመናት በኋላ ዓምና ዳግም የሊጉን ዘውድ የደፉት ፈረሰኞቹ በተረጋጋ የቡድን ስብስብ ዘንድሮም የተሻሉ ሆነው ስለመቅረብ ያልማሉ ፤ ሶከር ኢትዮጵያም በተከታዩ ዳሰሳ ለአዲሱ የውድድር ዘመን ስላደረጉት ዝግጅት ልታስቃኛችሁ ወዳለች። በ2014 የውድድር ዘመን በ30 የጨዋታ ሳምንታት በአንዱ ብቻ ሽንፈትን በማስተናገድ በድምሩ 65 ነጥቦች በማሳካት ከሦስት የውድድር ዘመናት ቆይታ በኋላ አስራRead More →

የሁለት ጊዜ የሊጉ ሻምፒዮን ሀዋሳ ከተማ ለሦስታ የተዘጋጀበትን የ2015 የውድድር ዓመት ዳሰሳ እንደሚከተለው አጠናክረናል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአዲስ መልክ 1990 ላይ ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫው ወደ ክልል እንዲወጣ ያደረገው እና ከመዲናይቱ ክለቦች ውጪ 2 ጊዜ ሻምፒዮን መሆን የቻለው ሀዋሳ ከተማ በየዓመቱ በሊጉ ከምናያቸው ሁለት ክለቦች (አንደኛው ኢትዮጵያ ቡና ነው)Read More →

ለገጣፎ ለገዳዲ የታሪኩን የመጀመሪያ የፕሪምየር ሊግ ተሳትፎ ለማድረግ ከወትሮው የአዲስ አዳጊዎች መንገድ የተለየ አቅጣጫን መርጧል። ወደ ሀገሪቱ ከፍተኛ የሊግ ዕርከን ለማደግ ከፍ ያለ ፉክክር በሚደረግበት የከፍተኛ ሊግ ውድድር ከ2009 ጀምሮ ሲፋለም የቆየው ለገጣፎ ለገዳዲ በተለይም በ2011 እና በኮቪድ ምክንያት በተቋረጠው ቀጣዩ የውድድር ዓመት ሊጉን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሶ ሳይሳካለት ቀርቶ ነበር።Read More →

ያለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት ለአዳማ ከተማዎች እምብዛም ለማስታወስ የሚፈልጓቸው እንዳልነበሩ መናገር ይቻላል ፤ ዘንድሮ ይህን ሂደት ለመቀልበስ በቀድሞው ኮከባቸው እየተመሩ ውድድሩን በተስፋ ይጀምራሉ። እኛም ዝግጅታቸው ምን ይመስላል ስንል ተከታዩን ፅሁፍ አሰናድተናል። በ2014 የውድድር ዘመን አዳማ ከተማዎች ከተወሰኑ ጨዋታዎች በስተቀር በአመዛኙ ጨዋታዎች ከተጋጣሚዎቻቸው በተሻለ መንቀሳቀስ ቢችሉም ከጨዋታዎች ሙሉ ሦስት ነጥብ ይዘውRead More →

ከአሠልጣኝ ጀምሮ ስብስባቸውን በአዲስ መልክ ያዋቀሩት ሠራተኞቹ በዘንድሮ ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንደ ቅፅል ስማቸው በርትተው ጠንካራ ፉክክር ለማድረግ ተዘጋጅተዋል። 2012 ላይ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የሊግ እርከንን የተቀላቀለው ወልቂጤ ከተማ የመጀመሪያ የሊጉ ተሳትፎ በኮቪድ-19 ምክንያት እንዲሰረዝ ከተደረገ በኋላ 2013 ላይ ወደ መጣበት ከፍተኛ ሊግ የመውረድ እጣ ፈንታ አጋጥሞትRead More →

በ1980ዎቹ አጋማሽ ከሀገር አልፎ በአህጉራዊ ውድድሮች የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚ የነበረው ቡድን ከ1990ዎቹ መጨረሻ አንስቶ የነበረው ገናናነት ታሪክ ሆኖ አሁን ላይ ሊጉን ከስምንት ዓመታት ጥበቃ በኋላ ዳግም ተቀላቅሏል ፤ እኛም በዚህኛው ፅሁፋችን መድን ራሱን ለፕሪሚየር ሊግ ህይወት እያዘጋጀበት ስላለው መንገድ ተከታዩን ዳሰሳ አሰናድተናል። በኢትዮጵያ እግርኳስ በቀደመው ዘመን በገናናነታቸው ከሚጠቀሱ ክለቦች አንዱRead More →

መቻል የቀድሞው መጠሪያውን በመመለስ እና ‘አዲስ ቡድን’ በመገንባት በብርቱ ለመፎካከር ተዘጋጅቷል። ከሁለት ዓመታት የከፍተኛ ሊግ ቆይታ በኋላ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደገው የአምናው መከላከያ በሊጉ የሚያከርመውን ውጤት አስመዝግቦ ለዘንድሮ ውድድር በታሪካዊ ስያሜው ‘መቻል’ ተሰኝቶ መጥቷል። ዓምና ሊጉን በሁለት ተከታታይ ድሎች ጀምሮ ኮስታራ ተፎካካሪ ይመስል የነበረው መቻል በሂደት ወደ ሰንጠረዡ የታችኛው ክፍልRead More →