አፍሪካ

ሦስተኛ ደረጃን ለመያዝ የተደረገው የደቡብ ሱዳን እና ኬንያ ጨዋታ ደቡብ ሱዳንን አንድ ለምንም አሸናፊ አድርጎ ተጠናቋል። ዝግ ያለ እንቅስቃሴ የታየበት የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ ደቂቃዎች የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የግብ ማግባት ሙከራ ለማስተናገድ አስራ አንድ ደቂቃዎች ወስደውበት ነበር። በተጠቀሰው ደቂቃም ኳስ በእጅ በመነካቱ ደቡብ ሱዳን ከጥሩ ቦታ የቅጣት ምት አግኝታ በዶሚኒክ ኮርኔሊዮዝርዝር

ቅዳሜ በሚጀምረው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ አስራ ሰባት ዳኞች ከተለያዩ ሀገራት ጥሪ ሲቀርብላቸው ሁለቱ ከኢትዮጵያ ሆነዋል፡፡ የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ሐምሌ 10 በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በሚደረጉ ሁለት መርሀግብሮች በይፋ ይጀመራል፡፡ በሶስት ምድቦች ተከፍሎ በዘጠኝ ሀገራት መካከል የሚደረገውን ይህን ጨዋታ ከተለያዩ ሀገራት በተመረጡ ዘጠኝ ዋና እና ስምንትዝርዝር

ለትክክለኛ መረጃዎች እምብዛም ክፍት ያልሆነው ሴካፋ በሀገራችን የሚጀመረው ውድድር እሁድ እንደሆነ ይፋ ቢያደርግም ውድድሩ ቀድሞ በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ ሰምተናል። በባህር ዳር ከተማ የሚካሄደው 41ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከሰኔ 26 ጀምሮ እንደሚካሄድ ከወራት በፊት ቢገለፅም “አንዳንድ ተሳታፊ ሀገራት በሌላ ውድድር ላይ መሳተፋቸውን ተከትሎ” የመጀመሪያው ቀን ወደ ሐምሌ 10ዝርዝር

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመቀጠል የሴካፋ ውድድር ወደሚደረግበት ባህር ዳር ከተማ ያቀናችው ሁለተኛ ሀገር ኬንያ ሆናለች። በአሠልጣኝ ስታንሊ ኦኩምቢ የሚመራው የኬንያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለሴካፋ ውድድር ኢትዮጵያ መድረሱ ታውቋል። በምድብ ሦስት ከደቡብ ሱዳን እና ጂቡቲ ጋር የተደለደለው ብሔራዊ ቡድኑም በትናንትናው ዕለት የመጨረሻ ልምምዱን በሀገሩ ከሰራ በኋላ ረፋድ ላይ ወደዝርዝር

በሀገራችን የሚካሄደው የሴካፋ ውድድር ሙሉ መርሐ-ግብርን እንደሚከተለው አዘጋጅተነዋል። 41ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከሦስት ቀናት በኋላ በባህር ዳር ከተማ መደረግ ይጀምራል። በውድድሩ ላይ ስምንት የቀጠናው እና አንድ ተጋባዥ ሀገር ተሳታፊ እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን የእጣ ማውጣት መርሐ-ግብሩም በበይነ መረብ አማካኝነት በትናንትናው ዕለት ተከናውኗል። በዚህም ዘጠኙ ብሔራዊ ቡድኖች በሦስት ምድብዝርዝር

ቅዳሜ ሐምሌ 10 እንደሚጀመር ሲነገር የነበረው የሴካፋ ውድድር በአንድ ቀን መገፋቱ ታውቋል። ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ጊዜ የምታስተናግደው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከሰኔ 26 ጀምሮ እንደሚካሄድ ቀድሞ ቢገለፅም የተሳታፊ ሀገራት በሌላ ውድድር ላይ መሳተፍ የመጀመሪያው ቀኑ ለሁለት ሳምንት እንዲገፋ አድርጎታል። በዚህም ውድድሩ ከሐምሌ 10 ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገልጾ ነበር። አሁን ሴካፋዝርዝር

በዛሬው ዕለት የምድብ ድልድሉ የወጣው የሴካፋ ውድድር የምድብ ጨዋታዎች የቀን እና ሰዓት መርሐ-ግበር ታውቋል። ዘጠኝ ሀገራትን በሦሰት ምድብ ከፋፍሎ የሚደረገው የሴካፋ ውድድር ከሐምሌ 10 ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ መደረግ ይጀምራል። የምድብ ድልድሉ እኩለ ቀን አካባቢ የወጣ ሲሆን አሁን ደግሞ የምድብ ጨዋታዎች ቀን እና ሰዓት ታውቋል። በዚህም መሠረት የውድድሩ የመክፈቻ መርሐ-ግብርዝርዝር

ትናንት በአዲስ አበባ የነበራቸውን ዝግጅት ጨርሰው ወደ ባህር ዳር የተጓዙት የኢትዮጵያ ከ 23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አባላት ዛሬ ልምምድ አከናውነዋል። በአቫንቲ ሆቴል መቀመጫውን ያደረገው ብሔራዊ ቡድኑ ከቀኑ 9 ሰዓት በቀዝቃዛማ የአየር ሁኔታ ላይ ልምምዱን የሰራ ሲሆን ቀለል ያለ ልምምድ እንዲሁም ከሁለት ተከፍለው በግማሽ ሜዳ ጨዋታ በማድረግ አከናውነዋል። በዛሬው ልምምድዝርዝር

ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ የሚደረገው የሴካፋ ውድድር የእጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ዛሬ ከሰዓት ይከናወናል። 41ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በ23 ዓመት በታች ቡድኖች መካከል ከሐምሌ 10 ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ ይደረጋል። ምንም እንኳን በውድድሩ የሚሳተፉ የቀጠናው ብሔራዊ ቡድኖች ቀስ በቀስ ራሳቸውን እያገለሉ ቢመጡም ባሉት ሀገራት የእጣ ማውጣት መርሐ-ግብሩ በዛሬው ዕለትዝርዝር

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ወንድ እና ሴት የካፍ ኢንስትራክተሮች ለአምስት ቀን ቆይታ ከነገ ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ ሊከትሙ ነው። የአፍሪካ እግርኳስ የበላይ አካል የሆነው ካፍ የአባል ሀገራቱን የአሠልጣኞች ስልጠና ደረጃ ከፍ ለማድረግ ከወራቶች በፊት እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ክፍልም ካፍ በሰጠው መመሪያ መሠረት በሀገራችን ከሚገኙ የካፍ ኢንስትራክተሮች ጋር በመሆንዝርዝር