ምርጦች

በስድስት ዘርፎች የስፖርት ዞን የዓመቱ የዕዉቅና ፕሮግራም አሰጣጥ አስመልክቶ ዛሬ በቤዝ ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል። ያለፉትን ስድስት ዓመታት በሀገር ውስጥ እግርኳስ ላይ ትኩረቱን በማድረግ በፋና ኤፌም 98.1 ከሰኞ እስከ አርብ በጋዜጠኛ ሰዒድ ኪያር እና ጋዜጠኛ መኳንንት በርሄ ዋና አዘጋጅነት ተሰናድቶ የሚቀርበው ስፖርት ዞን በእግርኳሱ ዘርፍ ኮከቦችን ለመሸለም ከወራትዝርዝር

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎችን በመንተራስ ሶከር ኢትዮጵያ ይህንን የምርጦች ቡድን ሰርታለች። አሰላለፍ: 4-3-3 ግብ ጠባቂ ተክለማርያም ሻንቆ – ኢትዮጵያ ቡና በመጨረሻው ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ከታዩ የግብ ዘቦች መካከል በአንፃራዊነት የተሻሉ ዕድሎችን ሲያመክን የታየው ተክለማርያም ሻንቆ ነው። እርግጥ ተጫዋቹ በ12ኛው ደቂቃ የፈፀመው የኳስ ቅብብል ስህተት ዋጋ ሊያስከፍለው የነበረዝርዝር

የዘንድሮ የውድድር ዘመን ኮከብ አሠልጣኝ ተብለው የተመረጡት አሠልጣኝ ሥዩም ከበደ የተሰማቸውን ስሜት አጋርተዋል። የፋሲል ከነማው ዋና አሠልጣኝ ሥዩም ከበደ ቡድናቸውን ሻምፒዮን በማድረጋቸውም ከአሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው የዋንጫ እና 2 መቶ ሺ ብር ሽልማት ተቀብለዋል። አሠልጣኙም ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ ተከታዩን አጭር ሀሳብ ሲናገሩ ተደምጧል። ” በቅድሚያ ፈጣሪዬን አመሠግናለሁ። ይሄንንም ከፍተኛ ክብር በቅርቡዝርዝር

የዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋች የሆነው አቡበከር ናስር የዋንጫ እና የገንዘብ ሽልማቱን ተረክቧል። 29 ግቦችን ያስቆጠረው አቡበከር ናስር የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆኑ የዋንጫ እና የ2 መቶ ሺ ብር ሽልማቱን ከክብር እንግዳው ዮርዳኖስ ዓባይ ተቀብሏል። ተጫዋቹም ሽልማቱን ከተረከበ በኋላ ተከታዩን ሀሳብ በመድረኩ ተናግሯል። “በቅድሚያ ፈጣሪዬን አመሠግናለሁ። ዓመቱዝርዝር

በ25ኛው ሳምንት በተካሄዱት ስድስት ጨዋታዎች ላይ በመመርኮዝ ተከታዮቹን ምርጥ አስራ አንድ መርጠናል። አሰላለፍ: 3-5-2 ግብ ጠባቂ ሚኬል ሳማኬ – ፋሲል ከነማ የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ክለብ የግብ ዘብ የሆነው ሚኬል ሳማኬ ከሁለት ጨዋታ እረፍት በኋላ በተሰለፈበት በዚህኛው የጨዋታ ሳምንት ድንቅ ጊዜ አሳልፏል። ቡድኑ ፋሲል ከነማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር አንድ ለአንድ ሲለያይምዝርዝር

በሃያ አራተኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ በመመርኮዝ የሳምንቱን ምርጦች በዚህ መልኩ አሰናድተናል። አሰላለፍ: 3-4-3 ግብ ጠባቂ ሴኩምባ ካማራ (አዳማ ከተማ) ምንም እንኳን ባሳለፍነው የጨዋታ ሳምንት አዳማ ከተማ በሰበታ ከተማ ቢረታም ጊኒያዊው የግብ ዘብ ሴኩምባ ካማራ ያሳየው ብቃት መልካም ነበር። በተለይ ተጫዋቹ ቅልጥፍና፣ ጊዜ አጠባበቅ እና ጨዋታን ማንበብዝርዝር

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን በመመርኮዝ ይህንን የምርጦች ቡድን ሰርተናል። አሰላለፍ: 3-2-3-2 አቡበከር ኑሪ (ጅማ አባ ጅፋር) ወጣቱ ግብ ጠባቂ ቡድኑ ከወላይታ ድቻ ነጥብ በተጋራበት ጨዋታ ጠንካራ ሙከራዎችን በማዳን ጥሩ ቀን አሳልፏል። በተለይ በመጀመርያው አጋማሽ የድቻዎችን በርካታ ተሻጋሪ ኳሶች በጥሩ ሁኔታ ከመቆጣጠር በተጨማሪ ሁለት አደገኛ ሙከራዎችን ማዳን የቻለዝርዝር

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ ምርጥ አቋማቸውን ያሳዩ ተጫዋቾችን እንዲህ መርጠናል። አሰላለፍ 4-3-3 ግብ ጠባቂ ይድነቃቸው ኪዳኔ – ፋሲል ከነማ ፋሲል ከነማ የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱን ካረጋገጠ በኋላ ባደረገው የዚህ ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታው ይድነቃቸው የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ የመሰለፍ ዕድል አግኝቷል። በጨዋታው የቡድኑን እንቅስቃሴ በእግሩ ቅብብሎችን በመከወን ከማገዙ እናዝርዝር

በድሬዳዋ የውድድር ምዕራፍ የመጨረሻ የጨዋታ ሳምንት ላይ ጎላ ብለው የታዩ ተጫዋቾችን እንደሚከተለው አሰናድተናል። አሰላለፍ: 3-2-3-2 ግብ ጠባቂ – ፋሲል ገብረሚካኤል (ሰበታ ከተማ) የምንተስኖት አሎን ወደ ተጠባባቂ ወንበር መውረድ ተከትሎ የቋሚነት ዕድል ያገኘው ፋሲል በ21ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ-ግብር ያሳየው ብቃት ለቀጣዮቹ ጨዋታዎችም በግቦቹ መካከል ቆሞ እንደሚዘልቅ የጠቆሙ ናቸው። ቀልጣፋው የግብ ዘብዝርዝር

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 20ኛ ሳምንት በተደረጉት ጨዋታዎች ላይ ጥሩ ብቃት አሳይተዋል ያልናቸውን ተጫዋቾች እና አሰልጣኝ በማካተት ተከታዩን ምርጥ ቡድን መርጠናል። አሰላለፍ 3-3-3 ግብ ጠባቂ ፍሬው ጌታሁን – ድሬዳዋ ከተማ ድሬዳዋ ከተማ ከቅርብ ተፎካካሪው ሲዳማ ቡና ጋር ያደረገውን ጨዋታ በድል እንዲወጣ የግብ ጠባቂው ሚና ከፍተኛ ነበር። በተለይም በሁለተኛው አጋማሽ ያዳናቸውዝርዝር