ሰበታ ከተማ (Page 2)

የ24ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎችን እንዲህ አሰናድተናል። በሰበታ ከተማ በኩል አብዱልሀፊዝ ትፊቅ፣ ናትናኤል ጋንቹላ፣ ኢብራሂም ከድር እና አዲሱ ተስፋዬ አርፈው ፉአድ ፈረጃ፣ መስዑድ መሐመድ፣ ታደለ መንገሻ እና ቢያድግልኝ ኤልያስ በአሰላለፉ ተካተዋል። ላለመውረድ የነበራቸውን እቅድ በማሳካታቸው ቀጥ እቅዳቸው እስከ አራት ገብቶ ማጠናቀቅ መሆኑን አሰልጣኝ አብርሀም መብሬቱ ገልፀዋል። በአዳማ ከተማ በኩልዝርዝር

ከከሰዓቱ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አሠልጣኞች የድህረ ጨዋታ አስተያየታቸውን ለሱፐር ስፖርት ሰጥተዋል። አብርሃም መብራቱ – ሰበታ ከተማ በመጨረሻ ደቂቃ ግብ አስቆጥረው ስለማሸነፋቸው? እጅግ በጣም ነው ደስ ያለኝ። ከነበረብን የስነ-ልቦና ችግር አንፃር ዛሬ ያገኘነው ውጤት ቀጣይ ለምናደርጋቸው ጨዋታዎች እጅግ የሚያነሳሳን ነው። በአጠቃላይ እንደውም እኔ የዛሬውን ውጤት ወርቃማ ድል ብዬ ነው የምገልፀው። በጨዋታውዝርዝር

በ21ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ ሰበታ ከተማዎች ከመመራት ተነስተው ባህር ዳር ከተማን ከረቱበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኃላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ለሱፐር ስፖርት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አብርሃም መብራቱ – ሰበታ ከተማ በእረፍት ሰአት ወደ መልበሻ ክፍል እያሰበ ስለገባው ጉዳይ “ወደ መልበሻ ክፍል ስገባ በሁለተኛው አጋማሽ የግድ አጨዋወታችንን መቀየር እንዳለብን እናዝርዝር

የ21ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመክፈቻ መርሐ-ግብር የሆነው የባህር ዳር እና ሰበታ ከተማ ጨዋታ ጥሩ ፉክክር፣ አነጋጋሪ ውሳኔዎች እንዲሁም በድምሩ 51 ጥፋቶች ታይተውበት ሰበታ ከተማን ባለድል አድርጓል። ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ዋና አሰልጣኙ ፋሲል ተካልኝን በሜዳ ላይ ያገኘው ባህር ዳር ከተማ በሀዋሳ ከተማ ከተሸነፈበት ስብስብ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ አድርጎ ጨዋታውንዝርዝር

የ21ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታን የተመለከቱ መረጃዎች እነሆ! ከሁለት ጨዋታ በኋላ ዋና አሰልጣኙ ፋሲል ተካልኝን ያገኘው ባህር ዳር ከተማ በሀዋሳ ከተማ ከተሸነፈው ስብስብ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ አድርጓል። በዚህም በግርማ ዲሳሳ እና በረከት ጥጋቡ ምትክ አፈወርቅ ኃይሉ እና ሳለአምላክ ተገኘ በአሰላለፉ ተካተዋል። በአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በኩል ባለፈው ሳምንትዝርዝር

የ20 ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ የሆነው የሰበታ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታን መረጃዎች እንደሚከተለው አሰናድተናል። (የአሰላለፍ ለውጥ መኖሩ በመገለፁ ይህ የተስተካከለ አሰላለፍ መረጃ መሆኑን እንገልፃለን።) ሰበታ ከተማ ባለፈው ሳምንት ጅማ አባ ጅፋርን ሲያሸንፍ በቀረበበት አሰላለፍ ላይ አራት ለውጦች በማድረግ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል። በዚህም በቢያድግልኝ ኤልያስ፣ አንታምቢ፣ ቃልኪዳን ዘላለም፣ ያሬድ ሀሰንዝርዝር

በ20ኛው ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ ዙሪያ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተናል። አሁን ላይ የከፋ ስጋት የሌለባቸው ሁለቱ ቡድኖች በሰንጠረዡ አጋማሽ አካባቢ ላይ ሆነው ይበልጥ ራሳቸውን የሚያደላድሉባቸውን ነጥቦች ፍለጋ ይገናኛሉ። ድሬዳዋ ላይ የመጀመሪያ ሦስት ነጥባቸውን ጅማ አባ ጅፋርን በመርታት ያሳኩት ሰበታዎች አሸነፊነታቸውን ካስቀጠሉ የነገ ተጋጣሚያቸውንም በነጥብ በልጠው ከፍ ማለት ይችላሉ። የኮቪድ በትር አብዝቶ ያረፈበትዝርዝር

ሰበታ ከተማ ጅማ አባጅፋርን ሲረታ ሁለት ግቦችን ካስቆጠረው ኦሴ ማውሊ ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርገናል። ዛሬ ከተደረጉ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ቀዳሚ የነበረው ጅማ አባ ጅፋርን ከሰበታ ከተማ ያገናኛው ጨዋታ ነበር። በጨዋታው ሰበታ ከተማ በቅድሚያ ግብ ቢቆጠርበትም በጋናዊው አጥቂ ኦሲ ማውሊ ሁለት ግቦች ጨዋታውን አሸንፎ መውጣት ችሏል። በ2011 የውድድር ዓመትዝርዝር

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 19ኛ ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ ሰበታ ከተማ ከመመራት ተነስቶ ጅማ አባጅፋርን ከረታበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኃላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዮን ሀሳብ ለሱፐር ስፖርት ሰጥተዋል። አብርሃም መብራቱ – ሰበታ ከተማ ስለድሉ ትርጉም “ለእኛ የዛሬው ጨዋታ ትርጉም አንድ ደረጃችንን የምናሻሽልበት ነው ፤ ሁለተኛ ደግሞ ከአቻ እና መሸነፍ ወጥተን ወደ አሸናፊነትዝርዝር