ሰበታ ከተማ (Page 21)

ከሰምንት ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ሊጉ የተመለሰው ሰበታ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ መቅጠሩን ለጊዜው ይፋ ለማድረግ ቢዘገይም በዝውውር መስኮቱ አስራ ስምንት ተጫዋቾችን ለማስፈረም በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ከአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ጋር መለያየቱ እርግጥ መሆኑን ተከትሎ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ቀጣዩ አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም ከጫፍ ቢደርስም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሒደቱ ተጨናግፏል። ይህም ሳይሳካዝርዝር

ሰበታ ከተማ ከአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ጋር ሳይስማማ ሲቀር አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም ክለቡን በቅርቡ እንደሚረከቡ ይጠበቃል። ከስምንት ዓመታት በኋላ በአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና መሪነት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደገው ሰበታ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር የሁለት ወራት ኮንትራት ቢቀረውም ሁለቱ አካላት መስማማት አለመቻላቸውን አሰልጣኝ ክፍሌ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል፡፡ “ዛሬ ጠዋት ጠርተው አናግረውኝ ነበር።ዝርዝር

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የመጨረሻ (22ኛ ሳምንት) ሦስት ጨዋታዎች እሁድ ተካሂደው የየምድቡ አሸናፊዎች ዋንጫቸውን ሲረከቡ ቀሪዎቹ ጨዋታዎች ቅዳሜ ይደረጋሉ ተብሏል። በምድብ ሀ ወልዲያን የገጠመው ሰበታ ከተማ 2-1 አሸንፏል። ለምድብ ሀ አሸናፊዎቹ ናትናኤል ጋንቹላ እና ብሩክ ሀዱሽ ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ ተስፋዬ ነጋሽ የወልዲያ ብቸኛ ጎል ባለቤት ነው። ሌሎች የምድብ ሀ ጨዋታዎች ቅዳሜ ሰኔዝርዝር

የከፍተኛ ሊጉ በተመሳሳይ ቀን ሦስቱንም ክለቦች ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲሸኝ ሰበታ ከተማም ከ8 ዓመታት በኋላ ወደ ዋናው ሊግ ተመልሷል። በየዓመቱ ወጣ ገባ አቋም እያሳየ የነበረው ሰበታ ከተማ ዘንድሮ በወጥ አቋም ለስኬት እንዲበቃ ካስቻሉ የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው አምበሉ ጌቱ ኃይለማርያም ነው። ወጣቱ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ከቡድን ስኬቱ በተጨማሪ በኢትዮጵያዝርዝር

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ የሚገኘው ሰበታ ከተማ ከተከታዩ ለገጣፎ ለገዳዲ ጋር በዕለት እሁድ ከሜዳው ውጪ ባደረገው ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት ተለያይቶ አንድ ጨዋታ እየቀረው አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ ወደ 2012 ፕሪምየር ሊግ ማደጉን ማረጋገጡ ይታወሳል። ይህን ቡድን በአጭር ጊዜ ውስጥ በመረከብ ለውጤት ያበቁት አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ስለ ቡድናቸውዝርዝር

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ 21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሙሉ እሁድ ተከናውነው ሰበታ ከተማ ወደ ፕሪምየር ሊግ ያደገበትን፣ አውስኮድ ወደ አንደኛ ሊግ የወረደበትን ውጤት አስመዝግበዋል። ለገጣፎ ላይ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በለገጣፎ ለገዳዲ እና ሰበታ ከተማ መካከል ተከናውኖ 1-1 ተጠናቋል። ሰበታ ከተማም አንድ ጨዋታ እየቀረው ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደጉን አረጋግጧል። የሁለቱም ከተማ ከንቲባዎችዝርዝር