አዳማ ከተማ

አዳማ ከተማ ተከላካይ አስፈረመ

ትዕግስቱ አበራ አዳማ ከተማን ተቀላቅሏል፡፡ አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሞ የነበረው ክለቡ በዛሬው ዕለት የመሐል እና የመስመር ተከላካይ የሆነው ትዕግስቱ አበራን በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል፡፡ ከዚህ ቀደም በሙገር ሲሚንቶ፣ ሀላባ ከተማ፣ ሀምበሪቾ እና ኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች የነበረው ተከላካዩ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከከፍተኛ ሊጉ እስከ ተሰረዘው የውድድር አመት ድረስ በሀዲያ ሆሳዕና ቆይታን ካደረገ በኋላ ለ2013 የውድድር ዓመት […]

አዳማ ከተማ ሦስት ተጫዋቾችን አስፈረመ

በበርካታ አዳዲስ ተጫዋቾች እየተዋቀረ የሚገኘው አዳማ ከተማ ሦስት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡ በአሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል እና ረዳቶቹ የሚመራው አዳማ ከተማ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ከበርካታ ተጫዋቾች ጋር ቅድመ ስምምነት የፈፀመ ቢሆንም ከዝውውሩ መከፈት ወዲህ ግን ወሳኝ ያላቸውን ተጫዋቾች በማስፈረም እንዲሁም ደግሞ ስምምነት ፈፅመው የነበሩትን በሙከራ ሲመለከት ቆይቶ ወደ ልምምድ ከገባ ሳምንታት አልፈውታል፡፡ የነባር ተጫዋቾችን ኮንትራት […]

​ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አዳማ ከተማ አዲስ ተጫዋች ሲያስፈርም የአማካይዋን ውል አራዘመ

አዳማ ከተማ ሁለገቧን ተጫዋች ሄለን ሰይፉን ሲያስፈርም የአማካይዋ ፋሲካ መስፍንን ውልም አድሷል፡፡ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪው አዳማ ከተማ ከወራት በፊት የአሰልጣኝ ሳሙኤል አበራን ውል ካራዘመ በኃላ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ የቀላቀለ ሲሆን አሁን ደግሞ አንጋፋዋን የአማካይ እና የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቿን ሄለን ሰይፉን አስፈርሟል፡፡ በአዲስ አበባ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ ስትጫወት የነበረችው […]

አዳማ ከተማ ቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በዚህ ሳምንት ይጀምራል

አዳማ ከተማዎች 2013 የውድድር ዓመት ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል፡፡ ካለፉት ዓመታት በተለየ መልኩ ከከፍተኛ ሊጉ እንዲሁም ጥቂት ተጫዋቾችን ከፕሪምየር ሊጉ ያስፈረመው አዳማ ከተማ ከፈረሙ ተጫዋቾች ባሻገር አብዛኛዎቹን በሙከራ ከተመለከተ በኃላ የመጨረሻ ፈራሚዎቹን ከሰሞኑ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል እና ረዳቶቹ የሚመሩት አዳማ ከተማዎች ለ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በዛሬው ዕለት ለተጫዋቾቹ ጥሪ አቅርቦ ሁሉም […]

አዳማ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ ሾሟል

አዳማ ከተማ ተጨማሪ ረዳት አሰልጣኝ ወደ ክለቡ አምጥቷል፡፡ ለ2013 የውድድር ዓመት የቀድሞው ረዳት አሰልጣኙን አስቻለው ኃይለሚካኤልን በይፋ የሾመው አዳማ ከተማ ከአሰልጣኙ ደጉ ዱባሞ ሌላ ረዳት አሰልጣኝ በቡድኑ ውስጥ ጨምሯል፡፡ አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ ደግሞ ለቦታው ተመራጭ ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ክለቦች በርከት ያሉ ጊዜያቶችን ያሳለፉት አሰልጣኙ ቡራዩ ከተማን ከለቀቁ በኃላ ሻሸመኔ ከተማን ይዘው ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ […]

“የተሰጠኝን ትልቅ ኃላፊነት ለመወጣት እሠራለው” የአዳማ ከተማ አሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል

ለ2013 የውድድር ዘመን በቅርቡ ቅድመ ዝግጅቱን የሚጀምረው አዳማ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ እንደሾመ ታውቋል። በ2012 በክረምቱ ወራት ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር የተለያየው አዳማ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ እንደማይሾምና በምክትል አሰልጣኞቹ እየተመራ የዘንድሮውን የውድድር ዓመት እንደሚጀምር መዘገባችን ይታወቃል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የክለቡ ቦርድ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ፊቱን አዙሮ አሰልጣኝ ዻውሎስ ጌታቸው እና አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን የመጨረሻ እጩ ሆነው […]

አዳማ ከተማ በርካታ ተጫዋቾችን በሙከራ ተመልክቶ ሊያስፈርም ነው

የፋይናንስ ችግሮቹን ለመቅረፍ ከሰሞኑ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው አዳማ ከተማ ለማስፈረም የተስማማቸው ተጫዋቾችን ጨምሮ በቅርቡ በሙከራ ጨዋታ መልምሎ ለማስፈረም ተዘጋጅቷል፡፡ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ብርቱ ተፎካካሪ ተብሎ ስማቸው ከፊት ከሚጠሩ ክለቦች መካከል የሆነው አዳማ ከተማ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በተጫዋቾቹ በተደጋጋሚ የደመወዝ አለመከፈል ጋር ተያይዞ ጥያቄ እየተነሳበት የቆየ ሲሆን በዚህ ችግር ውስጥም ሆኖ ሲጓዝ ቆይቶ የእግድ […]

አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማማ

ከአዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾች ጋር በመስማማት ላይ የተጠመዱት አዳማ ከተማዎች ሁለት የቀኝ መስመር ተጫዋቾችን በአንድ ዓመት ውል ለማስፈረም ተስማምተዋል፡፡ አንደኛው ፈራሚ ታፈሰ ሰርካ ነው፡፡ ይህ የቀደሞ የደቡብ ፖሊስ የመስመር ተከላካይ የልጅነት ክለቡን ለቆ ወደ መከላከያ ካመራ በኃላ እስከ 2011 በክለቡ አሳልፏል፡፡ የቀድሞው አሰልጣኙ ገብረመድኅን ኃይሌን ተከትሎ ወደ መቐለ 70 እንደርታ በመጓዝም ዘንድሮ ሊጉ እስከተሰረዘበት ጊዜ […]

የደጋፊዎች ገፅ | የአዳማ ከተማ ደጋፊዎች መኅበር ፕሬዝደንት አቶ ምስክር ሰለሞን

ከምስረታው ጀምሮ ብዙ እግርኳሰኛ ኮከብ ትውልዶችን አፍርቷል፣ በእግርኳሱ ከፍተኛ ስም እና ዝናም ያተረፈ ትልቅ ክለብ ነው። ቡድኑ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ከነበረው ጥንካሬ ባለፈ የክለቡ አስራ ሁለተኛ ተጫዋች በመሆን ውበቶቹ እና ድምቀቶቹ ደጋፊዎቹ መሆናቸው ይታወቃል። ሆኖም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች ደጋፊው ከሜዳ እየሸሸ ይገኛል። እነዚህ ክለቡ እየገጠሙት ያሉትን ተግዳሮቶች ለማለፍ ከክለቡ ሥራ አመራር ቦርድ ጋር […]

አዳማ ከተማዎች ግብጠባቂ ለማስፈረም ተስማሙ

አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም የሚገኙት አዳማ ከተማዎች ግብ ጠባቂው ታሪክ ጌትነትን ለማስፈረም ተስማምተዋል። ቀደም ብለው ሌላው ግብ ጠባቂ ቶማስ ወዳጆን በማስማማት የዳንኤል ተሾመን ውል ያራዘሙት አዳማዎች ላለፉት ዓመታት የቡድኑነ ግብ ከጠበቀው ጃኮ ጋር እንደሚለያዩ የሚጠበቅ ከመሆኑ አንፃር ተጨማሪ ግብ ጠባቂ ሲፈልጉ ቆይተው ታሪክ ጌትነትን ለማስፈረም ማስማማት ችለዋል። በተለያዩ ጊዜያት ከብሄራዊ ቡድን ጥሪ ደርሶት የሀገሩን ማልያ ለብሶ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top