Soccer Ethiopia

አዳማ ከተማ

አዳማ ከተማ የሁለት ተጫዋቾች ውል ለማራዘም ተስማማ

ሱሌይማን መሐመድ እና በላይ ዓባይነህ ከአዳማ ከተማ ጋር ለመቀጠል ተስማምተዋል። የቀድሞው የባንኮች እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመስመር ተከላካይ ሱሌይማን መሐመድ በአዳማ ለረዥም ዓመታት የቆየ ሲሆን ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ ከተመለሰ ወዲህ በአምበልነት እያገለገለ ይገኛል። የአንጋፋው ተጫዋች ውል ለማራዘም መስማማትም ቡድኑን በወጣቶች ለመገንባት ላሰቡት አዳማዎች በልምድ ረገድ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ሁለተኛው ውሉን ያራዘመው ባለፈው ዓመት […]

አዳማ ከተማ እና ውዝፍ ዕዳው

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከነበረው ጥንካሬ በተለያዩ ከሜዳ ውጭ በሚያጋጥሙት ፈተናዎች እየተንገዳገደ የሚገኘው አዳማ ከተማ ያልተከፈለ ውዝፍ ዕዳ ተገኘበት። አዳማ ከተማ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ እግርኳስ ውስጥ ጠንካራ ቡድን በመስራት፣ ውጤታማ ቡድን በመሆን እና ተተኪ ተጫዋቾችን በየዘመኑ በማፍራት የሚታወቅ ክለብ መሆኑ ይታወቃል። ታዲያ ይህ ጠንካራ ቡድን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በፋይናስ እጥረት ምክንያት የተለያዩ ፈተናዎች እያጋጠሙት እንደሆነ […]

አዳማ ከተማ የሁለት ተጫዋቾች ውል ለማራዘም ተስማማ

ሚካኤል ጆርጅ እና ዱላ ሙላቱ ከአዳማ ከተማ ጋር ለመቀጠል ተስማሙ። ከዚ ቀደም በሙገር ሲሚንቶ፣ ሲዳማ ቡና፣ ደደቢት እና አውሥኮድ የተጫወተው ግዙፉ አጥቂ ሚካኤል ጆርጅ ባለፈው ዓመት በድጋሚ ወደ አዳማ ከተመለሰ በኃላ ተቀይሮ እየገባ ቡድኑ ማገልገሉ ይታወሳል። የቀድሞው የነቀምቴ ከተማ፣ ሀዲያ ሆሳዕና እና መቐለ 70 እንደርታ ፈጣን የመስመር አጥቂ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በአዳማ ከተማ ያሳለፈ ሲሆን […]

አዳማ ከተማ ሦስት ተጫዋቾች ለማስፈረም ተስማማ

አዳማ ከተማዎች ሁለት ተከላካዮች እና አንድ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ሲስማሙ የአንድ ተጫዋች ውልም ለማራዘም ተስማምተዋል። ወደ ቡድኑ የተቀላቀሉ ተጫዋቾችም ቶክ ጀምስ፣ ይበልጣል አዳሙ እና ቶማስ ወዳጆ ሲሆኑ ዳንኤል ተሾመ ውል ያራዘመ ተጫዋች ነው። የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ወልድያ እና መቐለ የሆነው የመሃል ተከላካዩ ቶክ ጀምስ በካፋ ቡና ሲጫወት የቆየ ሲሆን ወደ ፕሪምየር […]

አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾች ለማስፈረም ተስማማ

አዳማ ከተማዎች ሁለት የመስመር ተከላካዮች ለማስፈረም በመስማማት ወደ ዝውውሩ ገብተዋል። በዝውውር መስኮቱ በርካታ ተጫዋቾች ከማጣት ውጭ የተጫዋቾች ውል ሳያራዝሙ እና አዳዲስ ተጫዋቾች ሳያዘዋውሩ የቆዩት አዳማ ከተማዎች አንሷር መሐመድ-ሰዒድ እና አንዋር መሐመድ-ሰዒድ የተባሉ ተጫዋቾችን ለማስፈረም በማስማማት ነው ወደ ገበያው የገቡት። የእግርኳስ ሕይወቱን በኮምቦልቻ የጀመረው አንሷር የግራ ተከላካይ ሲሆን ከዚ በፊትም በወልድያ ከተማ ቆይታ አድርጓል። በዚህ ዓመትም […]

ቆይታ ከተስፈኛው ታዳጊ ዱሬሳ ሹቢሳ ጋር…

በዛሬው የተስፈኞች አምዳችን ላይ ከፈጣኑ ሁለገብ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ዱሬሳ ሹቢሳ ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርገናል ። ሻሸመኔ ካፈራቻቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ታዳጊው ዱሬሳ ሹቤሳ በሻሸመኔ በሚገኝ ፕሮጀክት ነው የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው። በመላው ኦሮሚያ ውድድር ላይ በአሰላ ፉድ ኮምፕሌክስ መመረጥ የቻለው ዱሬሳ ጥሩ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ ወደ አዳማ ከተማ በማምራት እጅግ ስኬታማ የነበረ ቤሔራዊ […]

የአዳማ ከተማ አመራሮች አዳዲስ ውሳኔዎችን አሳለፉ

በዘንድሮ ዓመት በተለያዩ ምክንያቶች የተቀዛቀዘ የውድድር ጊዜ ያሳለፈው አዳማ ከተማ ለቀጣይ ዓመት ራሱን ለማዘጋጀት ወደ እንቅስቃሴ ሊገባ ነው። አዲስ የተሾሙት የክለቡ ፕሬዝደንት አቶ ገመቹ በተገኙበት የክለቡ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በትናንትናው ዕለት በክለቡ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ሰፊ ውይይት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል። ክለቡ አዲስ አሰልጣኝ ለጊዜው እንደማይቀጥር እና በምክትል አሰልጣኞቹ አማካኝነት ቡድኑ እንዲመራ ወስነዋል። ከዚህ […]

የሴቶች ገፅ | ቆይታ ከኮከቧ ሴናፍ ዋቁማ ጋር…

በዛሬው የሴቶች ገፅ አምዳችን የአዳማ ከተማ እና የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ኮከብ ሴናፍ ዋቁማን እንግዳ አድርገናታል። ነቀምት ላይ ተወልዳ ያደገችው ሴናፍ ከልጅነቷ ጀምሮ የኳስ ፍቅር እንዳደረባት ትናገራለች። በተለይ ተወልዳ ባደገችበት እና እስከ 8 ክፍል ድረስ በተማረችበት ነቀምት ከተማ ከወንዶች ጋር ኳስን አዘውትራ ትጫወት ነበር። ከዛም የ2ኛ ደረጃ ትምህርቷን እና የእግርኳስ ፍቅሯን ለመቀጠል ወደ አሰላ አመራች። […]

“የዘመኑ ከዋክብት ገጽ” ከከነዓን ማርክነህ ጋር..

ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ካሉት ድንቅ አማካዮች አንዱ ነው። ጥሩ የኳስ ክህሎት፣ ግዙፍ ተክለ ሰውነት እና ቀልጣፋ የሆነው ይህ አማካይ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ በሊጉ በትልቅ ደረጃ ከሚጠቀሱት አማካዮች አንዱ ለመሆን በቅቷል። የእግርኳስ ሕይወቱን በአዳማ ከተማ ተስፋ ቡድን ጀምሮ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና አዲስ አበባ ከተማ የተጫወተው ከነዓን ከ2010 ጀምሮ ወደ አሳዳጊ ክለቡ አዳማ ከተማ ተመልሶ በመጫወት […]

አሳዛኙ የዕዳጋ ሐሙስ አደጋ – ትውስታ በሲሳይ አብርሀም አንደበት

በአሳዛኝ አጋጣሚ የተደመደመው የአዳማ ከተማ የደስታ ቀን በ 2003 ካጋጠሙት እና የማይረሱ አጋጣሚዎች አንዱ የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በትግራይ ዕዳጋ ሐሙስ በምትባል ከተማ ያጋጠመው አስደንጋጭ የመኪና አደጋ አንዱ ነው። ታኅሣሥ 24 ቀን 2003 በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት አዳማ ከተማ ትራንስ ኢትዮጵያን ለመግጠም ወደ ዓዲግራት አምርቶ ጨዋታውንም 2-0 አሸንፎ በመመለስ ላይ እያለ ያጋጠመው ይህ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top