አርባምንጭ ከተማ

የከፍተኛ ሊግ የምድብ ሐ ሻምፒዮን በመሆን ወደ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ያደገው አርባምንጭ ከተማ ራሱን በገቢ ለማጠናከር ሁለት መርሐግብሮችን አዘጋጅቷል፡፡ አስቀድሞ የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን ኮንትራት በማደስ በዛሬው ዕለት ደግሞ ሦስት አዳዲስ እንዲሁም አስር ነባር ተጫዋቾችን ያስፈረመው ክለቡ የፋይናንስ አቅሙን ለማጠናከር በያዝነው ወር ሁለት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር እንዳዘጋጀ ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችውዝርዝር

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በአርባምንጭ ከተማ ውላቸውን አራዝመዋል፡፡ አርባምንጭ ከተማ ከሦስት ዓመታት የከፍተኛ ሊግ ቆይታ በኋላ ወደ 2014 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን የምድብ ሐ ውድድርን ሳይሸነፍ በበላይነት አጠናቆ ማረጋገጡ ይታወሳል፡፡ ክለቡ ለከርሞ በፕሪምየር ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን ይችል ዘንድ እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን አስቀድሞ ግን የአሰልጣኙን ኮንትራል ማደስን ቀዳሚው ተግባሩ አድርጓል፡፡ ከ2011ዝርዝር

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከምድብ ሐ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደጉን ላረጋገጠው አርባምንጭ ከተማ ሽልማት ተበረከተለት፡፡ በነቀምት ሲደረግ የነበረው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ሐ ውድድርን አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ ወደ 2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ማለፉን ያረጋገጠው የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ትናንት የደቡብ ክልል መቀመጫ በሆነችው ሀዋሳ ከተማ ሲደርስ በማርሽ ባንድ በታገዘዝርዝር

ትናንት ወሳኝ ጨዋታ ያሸነፈው አርባምንጭ ከተማ የተከታዩን ነጥብ መጣል ተከትሎ ወደ ፕሪምየር ሊግ የማደግ ዕድሉን ከፍ አድርጓል። ትናንት በምድብ ሐ 19ኛ ሳምንት ቀግተኛ ተፎካካሪው ከሆነው ኢትዮጵያ መድን ጋር ጨዋታውን ያደረገው አርባምንጭ ከተማ አላዘር ዝናቡ በመጀመርያ እንዲሁም ፍቃዱ መኮንን በመጨረሻ ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2-1 ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በዚህም ነጥቡን 43 በማድረስዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪው አርባምንጭ ከተማ የአሰልጣኝ ጌታነህ ኃይሉን ውል ሲያራዝም አንጋፋዋን አጥቂ አስፈርሟል፡፡ ከ2011 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ላይ ተወዳዳሪ የሆነው እና አዳዲስ ወጣት ተጫዋቾችን እያፈራ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ ለ2013 የውድድር ዓመት ዝግጅቱን ጀምሯል፡፡ የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ስንታየሁ ንጉሴ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁትዝርዝር

የዘንድሮ ውድድር በኮሮና ምክንያት እንዲሰረዝ ፌዴሬሽኑ ውሳኔ ያሳለፈበት መንገድ ተገቢ አይደለም በማለት አርባምንጭ ከተማ ተቃውሞውን አሰምቷል። በከፍተኛ ሊግ በምድብ ሐ እየመራ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ ለፌዴሬሽኑ በላከው ባለ ሦስት ገፅ ደብዳቤ ውሳኔው የሀገራችንን እግርኳስ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ያላገናዘበ፣ ከአድሏዊ አሰራር ያልፀዳ፣ ባለ ጉዳዮቹን አሳታፊ ያላደረገ፣ ፌዴሬሽኑ ያስቀመጠውን የአሰራር (ደንብ) የጣሰ እናዝርዝር

(መረጃውን የላከልን ክለቡ አርባምንጭ ከተማ ነው) በድንገት ሕይወቱ ያለፈው የአርባምንጭ ከተማው ግብ ጠባቂ ፍሬው ገረመው የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ በትውልድ ከተማው አርባምንጭ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል፡፡ ፍሬው ገረመው ከአባቱ ገረመው መገርሳና ከእናቱ ከወ/ሮ አከላት አማረ በ1985 ዓ.ም በአርባምንጭ ከተማ ድልፋና ቀበሌ ተወለደ። እድሜው ለትምህርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በቀድሞው ሳርማሌ 1ኛ ደረጃዝርዝር

ዛሬ ማለዳ ህይወቱ በድንገት ስላለፈው የአርባምንጭ ከተማ ግብ ጠባቂ ፍሬው ገረመው የክለቡ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ እና አምበሉ ወርቅይታደስ አበበ ለሶከር ኢትዮጵያ እንዲህ ይላሉ… አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ስለ ተጫዋቹ ህመም “አብሮት ወላይታ የሄደ እኛ ቡድን የሚጫወት ልጅ ነበር። ጠዋት ላይ ለኛ ሲነግረን ከቁርጭምጭሚቱ በላይ ከጉልበቱ በታች ትንሽ እንደ እጢ ነገርዝርዝር

የአርባምንጭ ከተማ ግብ ጠባቂ ፍሬው ገረመው በቅፅል ስሙ (ሰጌቶ) ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ተጫዋቹ ከሰሞኑ በጉልበቱ ላይ መጠነኛ ዕጢ ነገር ወጥታበት የነበረ ሲሆን እስከ ትላንት ድረስ ከጓደኞቹ ጋር ሲጫወት ከቆየ በኋላ ጉልበቱ ላይ ያለችውን ዕጢ ለማስወጣት ወደ ህክምና ስፍራ አምርቶ ክትትል በማድረግ ላይ ሳለ ዛሬ ማለዳ ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉንዝርዝር

ቀደም ብለው ምንተስኖት አበራ እና አድማሱ ጌትነትን ያስፈረሙት አዞዎቹ አሁን ደግሞ ሁለት ተጫዋቾች ወደ ቀድሞ ክለባቸው መልሰዋል። ባለፈው የውድድር ዓመት አርባምንጭ ከተማ ለቆ ኢትዮጵያ ቡና በመቀላቀል ከቡድኑ ጋር የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገው የግራ መስመር ተከላካዩ ተካልኝ ደጀኔ በትናንትናው ዕለት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በስምምነት መለያየቱ ሲታወስ ከዚህ ቀደም በደደቢት፣ አርባምንጭ ከተማዝርዝር