ባህር ዳር ከተማ

ከቀናት በፊት በሶከር ኢትዮጵያ ባህር ዳርን ለመቀላቀል መስማማቱን ዘግበን የነበረው ቡርኪናፋሶዋዊው ተጫዋች የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅሏል። በአሠልጣኝ አብርሃም መብራቱ የሚመራው ባህር ዳር ከተማ ቡርኪናፋሶዋዊው የአጥቂ አማካይ አብዱልከሪም ንኪማን ለማስፈረም መስማማቱን ከቀናት በፊት ዘግበን እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ተጫዋቹም በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ በመምጣት ዝውውሩን ማገባደዱ ይፋ ሆኗል። በ2009 እና 2010 በቅዱስ ጊዮርጊስ በመጫወትዝርዝር

አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱን የሾሙት ባህር ዳር ከተማዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት 33 ነጥቦችን በመያዝ 7ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ባህር ዳር ከተማ በ2014 የሊጉ ውድድር ተጠናክሮ ለመቅረብ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። በቅድሚያ ከአሠልጣኝ አብርሃም መብራቱን ጋር በመስማማት በይፋ ወደ እንቅስቃሴ የገባው ክለቡም ከዛ ፊቱን ወደ ተጫዋቾች ዝውውርዝርዝር

ለሁለት ዓመታት በባህር ዳር ከተማ የተጫወተው የአማካይ መስመር ተጫዋቹ የአንድ ዓመት ውል ቢኖረውም ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል። በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ያደገው እና አንድ ዓመት በቡድኑ ተጫውቶ ያሳለፈው ሳምሶን 2006 ላይ አሳዳጊ ክለቡን ለቆ ወደ ደደቢት ማምራቱ ይታወሳል። በደደቢት ጥሩ ጊዜያት በማሳለፍ በ2010 ወደ ኢትዮጵያ ቡና ያመራው ተጨዋቹም ለሁለት ዓመታት በቡናማዎችዝርዝር

አጥቂው ኦሴ ማውሊ በይፋ የባህር ዳር ከተማ ተጫዋች ሆኗል፡፡ ከቀናት በፊት ወደ ባህር ዳር ለማምራት ከስምምነት ደርሶ የነበረው እሴ ማውሊ ዛሬ አመሻሽ ዝውውሩን ማጠናቀቁ ይፋ ተደርጓል። ጋናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ከኢትዮጵያ እግር ኳስ የተዋወቀው በ2011 መቐለ 70 እንደርታ በመጫወት ሲሆን በመቀጠል ለፋሲል ከነማም ግልጋሎት ሰጥቷል፡፡ ወደ ሀገሩ ተመልሶ እስከ ዓመቱዝርዝር

ከሳምንታት በፊት አብርሃም መብራቱን አሠልጣኝ አድርጎ መሾሙ የተገለፀው ባህር ዳር ከተማ በይፋ ከአሠልጣኙ ጋር ተፈራርሟል። ይጀመራል ተብሎ ከተነገረው አንድ ሰዓት ዘግይቶ መካሄድ የጀመረው የፊርማ ሥነ-ስርዓቱ እና ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ እና የክለቡ ፕሬዝዳንት ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፣ የክለቡ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብርሃም አሰፋ፣ የክለቡ ሥራ-አስኪያጅዝርዝር

አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱን ዋና አሠልጣኝ አድርገው የሾሙት የጣና ሞገዶቹ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረውን አዳነ ግርማን በምክትል አሠልጣኝነት ለማምጣት ንግግር ጀምረዋል። በአሁኑ ሰዓት ከአሠልጣኝ አብርሃም መብራቱ ጋር የሁለት ዓመት ውል እየተፈራረሙ የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች የምክትል አሠልጣኝ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በአዲሱ ዋና አሠልጣኝ አብርሃም በተሰጠው ማብራሪያም ከእርሳቸው ጋርዝርዝር

👉“ኩን አጉዌሮን በጣም ነበር የማደንቀው” 👉”… ስደት መጥፎ ነገር ነው።” 👉”ስለኢትዮጵያ ያለኝ አመለካለት ጥሩ ነው። ህዝቡም በጣም ደስ የሚል ነው” የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከቀናት በፊት በታንዛኒያ አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወቃል። ምንም እንኳን በውድድሩ ላይ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አመርቂ ውጤት ባያመጣምዝርዝር

አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱን የሾሙት ባህር ዳር ከተማዎች ነገ ከሰዓት በይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ከአሠልጣኙ ጋር ስምምነት ይፈፅማሉ። በተጠናቀቀው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሰባተኛ ደረጃን ይዘው የጨረሱት ባህር ዳር ከተማዎች ከአሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር በስምምነት ከተለያዩ በኋላ በቀጣይ ዓመት ተጠናክሮ ለመቅረብ ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ። በዋናነት በሰበታ ከተማ የውድድር ዓመቱን የቋጩትን አሠልጣኝ አብርሃምዝርዝር

የአንድ ዓመት ውል የሚቀረው ግብ ጠባቂው ፅዮን መርዕድ በስምምነት ከባህር ዳር ከተማ ጋር መለያየቱ እርግጥ ሆኗል። በአርባምንጭ ከተማ የተወለደው የግብ ዘቡ ፅዮን መርዕድ በትውልድ ከተማው ክለብ ባሳየው ምርጥ ብቃት 2012 ላይ ወደ ባህር ዳር ከተማ ማቅናቱ ይታወቃል። በኮቪድ-19 ምክንያት የተሰረዘውን እና የዘንድሮውን የውድድር ዘመን ያጠናቀቀው ተጫዋቹም የአንድ ዓመት ውል ከባህርዝርዝር

በዘንድሮ የውድድር ዘመን ከሰበታ ከተማ ጋር ያሳለፉት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የጣና ሞገዶቹን ለማሰልጠን ተስማምተዋል። በፋሲል ከነማ አሸናፊነት በተጠናቀቀው የዘንድሮ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ሰበታ ከተማን እያሰለጠኑ የነበሩት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ለአንድ ዓመት የፈረሙት ኮንትራት ከቀናት በኋላ ይጠናቀቃል። የአሠልጣኙ ኮንትራት መጠናቀቂያ መባቻ ላይ መገኘቱን ተከትሎ በርካታ ክለቦች አሠልጣኙን ለማግኘት ፍላጎትዝርዝር