ድሬዳዋ ከተማ

ከሰሞኑ የአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን ውል አስቀድሞ ማደስ የቻለው ድሬዳዋ ከተማ በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር ገበያው በመግባት ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡ ጋዲሳ መብራቴ የመጀመሪያው የክለቡ ፈራሚ ሆኗል፡፡ በደደቢት የእግር ኳስ ህይወቱን ከጀመረ በኃላ ለኒያላ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ያለፉትን አራት ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ያሳለፈው አማካዩ ወደ ምስራቁ ክለብ አምርቷል፡፡ ሌላኛው ፈራሚዝርዝር

ድሬዳዋ ከተማን በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ተረክበው ሲያሰለጥኑ የነበሩት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ውላቸውን አድሰዋል። በ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አስቸጋሪ የውድድር ዓመትን ካሳለፉ ክለቦች መካከል አንዱ የነበረው ድሬዳዋ ዓመቱን በአሰልጣኝ ፍሰሐ ጥዑመልሳን እየተመራ መጀመር ቢችልም በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ላይ በውጤት መጥፋት ምክንያት ከአሰልጣኙ ጋር ከተለያየ በኃላ የቀድሞው የአዳማ፣ ፋሲል ከነማ፣ ወልድያ፣ዝርዝር

ከዕለቱ የመጀመሪያው ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኞች ተከታዮቹን አስተያየቶች ለሱፐር ስፖርት ሰጥተዋል። አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት – ሀዋሳ ከተማ በወጣት ተጫዋቾች እንቅስቃሴ ደስተኛ ስለመሆናቸው እጅግ በጣም ! በዓመቱ ወጣቶችን ስለመጠቀማቸው ወጣቶች ላይ በመስራት ብዙ ልዩነቶች ይፈጠራሉ። ለአንድ ዓመት ብቻ ዕቅድ ይዘህ የምትነሳ ከሆነ ይከብዳል። ለሦስት አራት ዓመት አብረህ ብትሰራ የተሳካ ጊዜ ይኖርሀል።ዝርዝር

ሀዋሳ እና ድሬዳዋ ከተማን ያገናኘው የረፋዱ ጨዋታ ሦስት ግቦች ተስተናግደውበት ሀዋሳ ከተማን አሸናፊ አድርጓል። የሀዋሳ ከተማው ዋና አሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ቡድናቸው ከፋሲል ከነማ ጋር ነጥብ ከተጋራው ስብስብ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። በዚህም ዳግም ተፈራ፣ ምኞት ደበበ እና ተባረክ ሔፋሞን በማሳረፍ ምንተስኖት ጊምቦ፣ ብሩክ በየነ እና አዲስዓለም ተስፋዬ ቋሚ አድርገዋል። ባለፈውዝርዝር

የመጨረሻው ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎችን እንደሚከተለው አጠናቅረናል። በሀዋሳ ከተማ በኩል ከፋሲል ነጥብ ከተጋራው ስብስብ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ በዳግም ተፈራ፣ ምኞት ደበበ እና ተባረክ ሔፋሞ ምትክ ምንተስኖት ጊምቦ፣ ብሩክ በየነ እና አዲስዓለም ተስፋዬ የሚጫወቱ ይሆናል። አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምኅረትም የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፉ ደረጃቸው እንደሚሻሻል በመግለፅ አሽንፈው እንደሚወጡ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንትዝርዝር

ከሊጉ የመጨረሻ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ላይ የሚከወኑትን ሁለት ጨዋታዎች እንዲህ ዳሰናቸዋል። ሀዋሳ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ ይህ ጨዋታ ለመርሐ ግብር ማሟያ ከሚደረጉ የ 26ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ውስጥ የሚካተት ነው። እርግጥ ነው ሀዋሳ ከተማ የግብ ልዩነቱንም በነገው ጨዋታ ማሻሻል ከቻለ እስከ አምስተኛ ደረጃ ከፍ የማለት ዕድል ያለው ሲሆን ድሬዳዋ ከተማ በበኩሉዝርዝር

የፋሲል ከነማው አሠልጣኝ ሥዩም ከበደ ከቀናት በፊት የወልቂጤ እግርኳስ ክለብ ቡድናቸውን “ከአቅም በታች ተጫውቷል” በሚል ስለከሰሰበት ጉዳይ ሀሳብ ሰጥተዋል። የ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ክለብ ፋሲል ከነማ በቀጣይ ስለሚያከናውናቸው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብሮች ጋር በተያያዘ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተነሱ ሙሉ ሀሳቦችን ከቆይታ በኋላዝርዝር

ያለግብ ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ የቡድኖቹ አሰልጣኞች ለሱፐር ስፖርት ሀሳባቸውን አካፍለዋል። አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ – ሀዲያ ሆሳዕና ካሉሻ አልሀሰንን ቀይረው አስገብተው መልሰው ስለማስወጣታቸው ስም እና ብቃት ይለያያል ። ሜዳ ላይ ምንም ካልሰራልህ ፣ የተሰጠውን ስራ ካልሰራልህ ምንም ልታደርገው አትችልም። ለእኔ ትልቅ ተጫዋች ነው ፤ ግን ትልቅነቱን ሜዳ ላይ ሲያሳይ ነው። በዚህዝርዝር

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሃያ አንደኛ ሳምንት በሁለተኛ ደረጃ ፉክክር እና ባለመውረድ ትንቅንቅ ውስጥ የሚገኙት ሆሳዕና እና ድሬዳዋን ያገናኘው ጨዋታ ያለ ጎል ተጠናቋል። ሀዲያ ሆሳዕና ከፋሲል ነጥብ ከተጋራበት ስብስብ የአምስት ተጫዋች ለውጥ በማድረግ በሱሌይማን ሀሚድ፣ ቴዎድሮስ በቀለ፣ ሄኖክ አርፊጮ፣ ካሉሻ አልሀሰን እና ቢስማርክ አፒያ ምትክ አይዛክ ኢሲንዴ፣ ብሩክ ቀልቦሬ፣ ዱላዝርዝር

በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ላይ ድሬዳዋ እና ሆሳዕና ይዘዋቸው የሚገቡት አሰላለፍ ታውቋል። ሀዲያ ሆሳዕና ከፋሲል ነጥብ ከተጋራበት ስብስብ የአምስት ተጫዋች ለውጥ ያደረገ ሲሆን አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ሱሌይማን ሀሚድ፣ ቴዎድሮስ በቀለ፣ ሄኖክ አርፊጮ፣ ካሉሻ አልሀሰን እና ቢስማርክ አፒያን በማሳረፍ ለአይዛክ ኢሲንዴ፣ ብሩክ ቀልቦሬ፣ ዱላ ሙላቱ፣ ተስፋዬ በቀለ እና ተስፋዬ አለባቸው የመሰለፍ እድልንዝርዝር