ድሬዳዋ ከተማ (Page 2)

የአሰልጣኝ ብዙአየው ጀምበሩን ውል ያደሰው እና አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ከአንድ ቀን በፊት ያስፈረመው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮኑ ድሬዳዋ ከተማ በዛሬው ዕለት ደግሞ ተጨማሪ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአንድ ነባር ተጫዋችን ውልም አድሷል፡፡ ተከላካይዋ ፀሐይ ኢፋሞ ወደ ቀድሞው ክለቧ ድሬዳዋ ከተማ ከአራት ዓመታት በኃላ በድጋሚ የሚመልሳትን ዝውውር አጠናቃለች፡፡ የቀድሞዋዝርዝር

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ መጣባቸው ሙሉ በፋሲል ከነማ ካሳደጉት አሠልጣኝ ጋር ዳግም የተገናኘበትን ዝውውር አጠናቋል፡፡ በዛሬው ዕለት መሳይ ጳውሎስ እና ማማዱ ሲዲቤን ወደ ስብስቡ የቀላቀለው ድሬዳዋ ከተማ መጣባቸው ሙሉን የክለቡ አምስተኛ ፈራሚ አድርጎ በሁለት ዓመት ውል ወደ ቡድኑ ማምጣቱ ታውቋል፡፡ መጣባቸው ከፋሲል ከነማ የወጣት ቡድን በወቅቱ የክለቡ አሠልጣኝ በነበሩት ዘማርያም ወልደጊዮርጊስዝርዝር

በዛሬው ዕለት መሳይ ጳውሎስን ያስፈረመው ድሬዳዋ ከተማ ማሊያዊውን አጥቂ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል። የአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን ውል ካደሰ በኃላ ጋዲሳ መብራቴ፣ እንየው ካሣሁን እና ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ መሳይ ጳውሎስን ያስፈረመው ድሬዳዋ ከተማ ማሊያዊው አጥቂ ማማዱ ሲዲቤን በሁለት ዓመት ውል አስፈርሟል። በ2011 ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኃላ በጅማ አባጅፋር በመጫወት ከሀገራችን እግር ኳስዝርዝር

አዲስ ጎጆ-ወጪ የሆነው ተጫዋች በዛሬው ዕለት ከባለቤቱ ጋር የፎቶ ፕሮግራም ሲያከናውን ወደ ሌላ የሊጉ ክለብ ያመራበትን ዝውውርም አጠናቋል። በአሠልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ የሚመሩት ድሬዳዋ ከተማዎች በስጋት ካሳለፉት የዘንድሮ የውድድር ዓመት በቀጣይ በተሻለ መልኩ ተጠናክረው ለመምጣት እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ። ሁለቱን የመሐል ተከላካዮች ወደ ሰበታ (በረከት ሳሙኤል) እና ሀዲያ (ፍሬዘር ካሳ) የሸኘው ክለቡምዝርዝር

ድሬዳዋ ከተማ የአሰልጣኝ ብዙዓየሁ ጀምበሩን ውል ሲያራዝም ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችንም አስፈርሟል። በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ጥሩ የውድድር ዘመን ካሳለፉ ክለቦች አንዱ ድሬዳዋ ከተማ ነው፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለክለቡ ቦርድ ከአንድ እስከ አምስተኛ ለማጠናቀቅ ቃል ገብታ የነበረችው አሰልጣኝ ብዙዓየሁ ጀምበሩ በቃሏ መሠረት አምስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ውሏ ለተጨማሪ ሁለትዝርዝር

ከሰሞኑ የአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን ውል አስቀድሞ ማደስ የቻለው ድሬዳዋ ከተማ በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር ገበያው በመግባት ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡ ጋዲሳ መብራቴ የመጀመሪያው የክለቡ ፈራሚ ሆኗል፡፡ በደደቢት የእግር ኳስ ህይወቱን ከጀመረ በኃላ ለኒያላ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ያለፉትን አራት ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ያሳለፈው አማካዩ ወደ ምስራቁ ክለብ አምርቷል፡፡ ሌላኛው ፈራሚዝርዝር

ድሬዳዋ ከተማን በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ተረክበው ሲያሰለጥኑ የነበሩት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ውላቸውን አድሰዋል። በ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አስቸጋሪ የውድድር ዓመትን ካሳለፉ ክለቦች መካከል አንዱ የነበረው ድሬዳዋ ዓመቱን በአሰልጣኝ ፍሰሐ ጥዑመልሳን እየተመራ መጀመር ቢችልም በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ላይ በውጤት መጥፋት ምክንያት ከአሰልጣኙ ጋር ከተለያየ በኃላ የቀድሞው የአዳማ፣ ፋሲል ከነማ፣ ወልድያ፣ዝርዝር

ከዕለቱ የመጀመሪያው ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኞች ተከታዮቹን አስተያየቶች ለሱፐር ስፖርት ሰጥተዋል። አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት – ሀዋሳ ከተማ በወጣት ተጫዋቾች እንቅስቃሴ ደስተኛ ስለመሆናቸው እጅግ በጣም ! በዓመቱ ወጣቶችን ስለመጠቀማቸው ወጣቶች ላይ በመስራት ብዙ ልዩነቶች ይፈጠራሉ። ለአንድ ዓመት ብቻ ዕቅድ ይዘህ የምትነሳ ከሆነ ይከብዳል። ለሦስት አራት ዓመት አብረህ ብትሰራ የተሳካ ጊዜ ይኖርሀል።ዝርዝር

ሀዋሳ እና ድሬዳዋ ከተማን ያገናኘው የረፋዱ ጨዋታ ሦስት ግቦች ተስተናግደውበት ሀዋሳ ከተማን አሸናፊ አድርጓል። የሀዋሳ ከተማው ዋና አሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ቡድናቸው ከፋሲል ከነማ ጋር ነጥብ ከተጋራው ስብስብ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። በዚህም ዳግም ተፈራ፣ ምኞት ደበበ እና ተባረክ ሔፋሞን በማሳረፍ ምንተስኖት ጊምቦ፣ ብሩክ በየነ እና አዲስዓለም ተስፋዬ ቋሚ አድርገዋል። ባለፈውዝርዝር

የመጨረሻው ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎችን እንደሚከተለው አጠናቅረናል። በሀዋሳ ከተማ በኩል ከፋሲል ነጥብ ከተጋራው ስብስብ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ በዳግም ተፈራ፣ ምኞት ደበበ እና ተባረክ ሔፋሞ ምትክ ምንተስኖት ጊምቦ፣ ብሩክ በየነ እና አዲስዓለም ተስፋዬ የሚጫወቱ ይሆናል። አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምኅረትም የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፉ ደረጃቸው እንደሚሻሻል በመግለፅ አሽንፈው እንደሚወጡ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንትዝርዝር