ሀዋሳ ከተማ (Page 2)

ዐፄዎሉ በታሪክ የመጀመርያ የሊግ ዋንጫቸውን ባነሱበት ዕለት ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ስለተፈጠረው ጉዳይ አምሳሉ ጥላሁን አስተያየቱን ሰጥቷል። ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከመጠናቀቁ ከአንድ ጨዋታ አስቀድሞ ዛሬ የዋንጫ አሰጣጥ ሥነ-ስርዓት በፋሲል ከነማ እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታ ላይ ሲከናወን በአቻ ውጤት ተለያይተው ዐፄዎቹ የድል ዋንጫቸውን ከፍ አድርገው ማንሳታቸው ይታወቃል። በዕለቱ ጨዋታ መጠናቀቂያ ላይዝርዝር

የረፋዱ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ አሰልጣኞች ለሱፐር ስፖርት የሰጡት አስተያየት ይህንን ይመስላል። አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ – ፋሲል ከነማ ስለቻምዮንነት ስሜት ፋሲል ከነማ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ይህን ዋንጫ ሲያገኝ። የተለየ የሚያደርገው ደግሞ ጨዋታዎች በ ዲ ኤስ ቲቪ መታየት ሲጀምሩ መሆኑ ነው። በዚህ ዘመን የመጀመሪያውን ዋንጫ በማግኘቴ እጅግ ነው ደስ ያለኝ። እንዴትዝርዝር

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎች እንደሚከተለው አጠናክረናቸዋል። የግላቸው ያደረጉትን ዋንጫ በዛሬው ዕለት የሚረከቡት ፋሲል ከነማ ከ19 ጨዋታዎች በኋላ ከተሸነፉበት የድሬዳዋው ፍልሚያ ስምንት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም አሠልጣኝ ስዩም ከበደ ይድነቃቸው ኪዳኔ፣ ሳሙኤል ዮሐንስ፣ አምሳሉ ጥላሁን፣ ሰዒድ ሀሰን፣ ሀብታሙ ተከስተ፣ሽመክት ጉግሳ፣ ሱራፌል ዳኛቸው እና ፍቃዱ ዓለሙን በማሳረፍ ሳማኬ ሚኬል፣ ሄኖክ ይትባረክ፣ዝርዝር

ፋሲል ከነማ ቀድሞ የግሉ መሆኑን ያረጋገጠውን ዋንጫ የሚረከብበትን የነገ ረፋድ ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል። በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለው ፋሲል ከነማ በመጨረሻ ጨዋታው በድሬዳዋ ከተማ ከደረሰበትን ሽንፈት ለማገገም፣ አሁንም በጥንካሬው ላይ እንደሚገኝ ለማሳየት እና የዋንጫ ርክክብ መርሐ-ግብሩን በድል ለማሳጀብ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይታሰባል። ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻሉት ሀዋሳዝርዝር

የሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ በአዳማ አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ለሱፐር ስፖርት ሰጥተዋል። ዘርዓይ ሙሉ – አዳማ ከተማ ድሉ የዘገየ ስለመሆኑ እስካሁን የምናደርገው እንቅስቃሴ ጥሩ ነበር። ለጎል እንቀርብ ነበር፤ ድል ያሳካነው ግን ዛሬ ነው። በእንቅስቃሴ ደረጃ የወረደ ቡድን አንመስልም ነበር። በራስ መተማመን ነበር ኳሱን ይዘው ሲጫወቱ የነበረው። ያለው ነገርዝርዝር

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 23ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ መውረዱን ያረጋገጠው አዳማ ከተማ ሀዋሳን አሸኝፏል። አዳማ ከተማ ከድሬዳዋ ነጥብ ከተጋራበት ጨዋታ ላሚን ኩማራ (ቅጣት) ፣ ትዕግስቱ አበራ፣ አሊሲ ጆናታን፣ ኤልያስ ማሞ፣ ሰይፈ ዛኪር እና በላይ ዓባይነህን አሳርፎ ጀሚል ያዕቆብ ፣ ደስታ ጊቻሞ፣ አሚን ነስሩ ፣ ደሳለኝ ደባሽ ፣ ሀብታሙ ወልዴ እናዝርዝር

ከ23ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እነሆ! ከ2013 ፕሪምየር ሊግ መውረዱን ያረጋገጠው አዳማ ከተማ ከድሬዳዋ ነጥብ ከተጋራበት ጨዋታ የስድስት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ ጀሚል ያዕቆብ፣ ደስታ ጊቻሞ፣ አሚን ነስሩ፣ ደሳለኝ ደባሽ፣ ሀብታሙ ወልዴ እና ኤልያስ አህም ወደ አሰላለፉ መጥተዋል። ላሚን ኩማራ (ቅጣት)፣ ትዕግስቱ አበራ፣ አሊሲ ጆናታን፣ ኤልያስ ማሞ፣ ሰይፈ ዛኪርዝርዝር

የ23ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመዝጊያ መርሐ-ግብር የሆነውን የአዳማ እና ሀዋሳን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል። በዛሬው ዕለት ከሊጉ መውረዱን ያረጋገጠው አዳማ ከተማ (ምናልባት የትግራይ ክለቦች በቀጣይ ዓመት ካልተሳተፉ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሊተርፍ ይችላል) የተጣላው ከሚመስለው ድል ጋር ለመታረቅ ብቻ ነገ ወደ ሜዳ ይገባል። ቀስ በቀስ የሁለተኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ በሚደረገው ፉክክርዝርዝር

በነገ ምሽቱ ጨዋታ ዙሪያ የሚያተኩረው ዳሰሳችን ይህንን ይመስላል። በነገው ዕለት የሚከናወነው የሮድዋ ደርቢ ጠንከር ያለ ፉክክርን እንደሚያስተናግድ ይጠበቃል። ድሬዳዋ ላይ ሁለት ድል እና ሁለት ሽንፈትን ያስመዘገቡት ሲዳማዎች ዛሬ አንድ ነጥብ ያገኘው ተፎካካሪያቸው ድሬዳዋ ከተማን ለመጠጋት ነገ አሸንፈው መውጣት የግድ ይላቸዋል። ባለፉት አራት ጨዋታዎች ከ12 ነጥቦች አስሩን ማሳካት የቻለው ሀዋሳ ከተማዝርዝር

የቀጣዩ ዳሰሳችን ትኩረት የነገ ምሽቱ ጨዋታ ይሆናል። በመካከላቸው በባህር ዳር የበላይነት የሰባት ነጥቦች እና የአራት ደረጃዎች ልዩነት ይኑር እንጂ ይህ ጨዋታ ጥሩ ፉክክር እንደሚኖርበት መናገር ይቻላል። የጣና ሞገዶቹ ማሸነፍ ከቻሉ በዚህ ሳምንት አራፊ ከሆነው ኢትዮጵያ ቡና ሁለተኛነቱን የመረከብ ዕድል በመኖሩ ውጤቱ አብዝቶ ያስፈልጋቸዋል። ኃይቆቹም የሚያስከፋ ሁኔታ ላይ ባይገኙም የታችኛውን የሰንጠረዥዝርዝር