ቅዱስ ጊዮርጊስ

ከደቡብ አፍሪካ ጋር ለሚደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታ ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ ያቀረቡት አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከፈረሰኞቹ የመረጧቸውን ተጫዋቾች አላገኙም። ኳታር ለምታስተናግደው የ2022 ዓለም ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ 7 ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባቡዌ ጋር እንደተደለደለ ይታወቃል። ብሔራዊ ቡድኑም ሁለት የምድብ ጨዋታዎችን አድርጎ ሦስት ነጥብ በማግኘት የምድቡዝርዝር

የቅዱስ ጊዮርጊስ አዲሱ አሠልጣኝ ዝላትኮ ክራምፖቲች ዛሬ ከሰዓት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ ከጋዜጠኞች ጋር ተዋውቀዋል። የ27 ጊዜ የኢትዮጵያ ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሳምንታት በፊት የ64 ዓመቱ ስርቢያዊ ዝላትኮ ክራምፖቲችን ዋና አሠልጣኝ አድርጎ መሾሙን መግለፁ ይታወቃል። ቅዳሜ አዲስ አበባ የደረሱት አሠልጣኙም ትናንት ወደ ቢሾፍቱ አቅንተው ከቡድኑ ተጫዋቾች ጋር ተዋውቀው የክለቡን አካዳሚ (ይድነቃቸውዝርዝር

ቡድኑን በአምበልነት ሲመሩ የነበሩት ተጫዋቾች ከክለቡ በመለያየታቸው ምክንያት ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አንበሎችን መምረጡ ታውቋል። ለ2014 የውድድር ዘመን አዲስ አሰልጣኝ የሾመው ቅዱስ ጊዮርጊሶች በትናንትናው ዕለት ቢሸፍቱ በሚገኘው የክቡር ይድነቃቸው አካዳሚ ለቅድመ ዝግጅት ከተሰባሰቡ በኃላ የክለቡ የቦርድ አመራሮች የቡድኑ አባላት እና አዲሱ አሰልጣኝ ዝላትኮ ክራምፓቲች በተገኙበት በይፋ ትውውቅ እና ምክክር አድርገዋል። በዚሁዝርዝር

ከሳምንታት በፊት የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት ሰርቢያዊ ቅዳሜ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይፋ ተደርጓል። የ64 ዓመቱ ሰርቢያዊ ዝላትኮ ክራምፖቲች በዋና አሰልጣኝነት የሾሙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች አዲሱ አሰልጣኝ ከሰርቢያዊው ምክትላቸው ኒኮላ ኮሮሊጃ ጋር በመሆን በመጪው ቅዳሜ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ያስታወቀ ሲሆን በተመሳሳይ ዕለት የዋናው ቡድን አባላት በዘሪሁን ሸንገታ እየተመሩ ለቅድመ ውድድር ዝግጅትዝርዝር

ስርቢያዊውን ዝላትኮ ክራምፖቲች ዋና አሠልጣኝ አድርገው የሾሙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ቶጎዋዊ አጥቂ የግላቸው ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ቀደም ብለው የበረከት ወልዴ፣ ቸርነት ጉግሳ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ቡልቻ ሹራ እና ምኞት ደበበን ዝውውር የጨረሱት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ዩጋንዳዊውን የግብ ዘብ ቻርለስ ሉክዋጎንም ለማስፈረም የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ ዘግበን ነበር። ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችውዝርዝር

በቅርቡ አዲስ አሠልጣኝ የሾሙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከደቂቃዎች በፊት የወጣቱን ግብ ጠባቂ ውል ማደሳቸውን ይፋ አድርገዋል። ዩጋንዳዊውን ግብ ጠባቂ ቻርለስ ሉክዋጎን ወደ ስብስባቸው ለመቀላቀል ከጫፍ የደረሱት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከደቂቃዎች በፊት ከ17 ዓመት በታች ቡድናቸው ጀምሮ ሲያገለግላቸው የነበረውን ወጣቱን ግብ ጠባቂ ተመስገን ዩሐንስን ውል ለተጨማሪ ዓመት አድሰዋል። ከ17 እና ከ20 ዓመት በታችዝርዝር

በዝውውር ገበያው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በዛሬው ዕለት የመሐል ተከላካያቸውን ውል አራዝመዋል። አንጋፋው የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣይ የውድድር ዓመት ተጠናክሮ ለመቅረብ ቅድመ ሥራዎችን እየከወነ እንደሚገኝ ይነገራል። ከትናንት በስትያ የጋቶች ፓኖምን ዝውውር የፈፀመው ክለቡ በዛሬው ዕለት ደግሞ የነባር ተጫዋቾችን ውል ማደስ መጀመሩን ሶከር ኢትዮጵያ ተረድታለች። ውሉን ያደሰው ተጫዋችዝርዝር

ከበርካታ ተጫዋቾች ዝውውር ጋር ስሙ እየተያያዘ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ የአማካይ መስመር ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል። በዘንድሮ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከዋንጫ ባለቤቱ ፋሲል ከነማ በ14 ነጥቦች ርቆ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣይ ዓመት ራሱን አጠናክሮ ለመምጣት የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል። እርግጥ ክለቡ የዋና አሠልጣኙን ጉዳይ እስካሁንዝርዝር

ከትናንት በስትያ የመኪና አደጋ ያጋጠመው ኬንያዊው የግብ ዘብ ስለ ወቅታዊ ጤንነቱ ሀሳብ ሰጥቷል። ከ2011 ጀምሮ በቅዱስ ጊዮርጊስ ሲጫወት የነበረው ኬንያዊው ግብ ጠባቂ ፓትሪክ ማታሲ ከትናንት በስትያ በቶዮታ ቪትስ መኪናው ባለቤቱን፣ ልጁን እና ሁለት ወንድሞቹን ጭኖ ከካካሜጋ ወደ ናይሮቢ ሲጓዝ አደጋ አስተናግዶ ነበር። የሀገሪቱ የብዙሃን መገናኛዎችም ከአደጋው በኋላ የተለያዩ መረጃዎችን ሲያወጡዝርዝር

ለ2014 የውድድር ዘመን ስብስባቸውን ለማጠናከር ከወዲሁ መንቀሳቀስ የጀመሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከሁለት ወጣት ተጫዋቾች ጋር ቅድመ ስምምነት እንደሚያርጉ ይጠበቃል። የእግርኳስ ህይወታቸውን በወላይታ ድቻ ከ17 ዓመት በታች ቡድን የጀመሩት በረከት ወልዴ እና ቸርነት ጉግሳ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ አድገው ባለፉት አራት የውድድር ዓመታት የተሳካ ጊዜ ማሳለፋቸው ይታወቃል። በተለይ በዘንድሮው ዓመት በቤትኪንግ የኢትዮጵያዝርዝር