ሲዳማ ቡና (Page 2)

ሲዳማ ቡና ጎፈሬ የስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር የስፖርት ትጥቅ እና የደጋፊዎች ቁሳቁስ ለማግኘት ስምምነት ፈፅሟል። በ2014 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ራሱን በሜዳ ላይ አጠናክሮ ለመቅረብ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ሲዳማ ቡና ከሜዳ ውጪ ያሉ ስራዎችንም ጎን ለጎን እያከናወነ ይገኛል። ከእነዚህ ስራዎች አንዱ የሆነው ደግሞ በክለቡ ስሩ የሚገኙትን ቡድኖች በትጥቅ ከሚደግፍ እንዲሁምዝርዝር

እስካሁን ስድስት ተጫዋቾችን ያስፈረመው ሲዳማ ቡና የሁለት ተከላካዮቹን ውል አድሷል፡፡ ጊት ጋትኮች ውሉን ያራዘመው ተጫዋች ነው፡፡ አዲስ አበባ ከተማን በመልቀቅ ሲዳማ ቡናን በ2012 በመቀላቀል ሁለት የውድድር ዓመታትን ያሳለፈው ቁመተ ረጅሙ ተከላካይ አሁንም ለተጨማሪ ዓመት በክለቡ መቆየቱ ተረጋግጧል፡፡ ሌላኛው ውሉን ያራዘመው የመስመር ተከላካዩ አማኑኤል እንዳለ ነው፡፡ የሲዳማ ቡና የታዳጊ ቡድን ፍሬዝርዝር

በዝውውሩ ላይ በፍጥነት እየሠሩ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች የአጥቂ አማካይ አስፈርመዋል፡፡ የአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌን ውል ለማራዘም የተቃረበውና ወደ ተጫዋቾች ዝውውር ጎራ ያለው ሲዳማ ቡና ተክለማርያም ሻንቆ፣ ብሩክ ሙሉጌታ፣ አንዋር ዱላ፣ ተስፋዬ በቀለ እና ሙሉዓለም መስፍንን በያዝነው ሳምንት ወደ ቡድኑ የቀላቀለ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ፍሬው ሰለሞንን በሁለት ዓመት ውል ወደ ቡድኑዝርዝር

የአማካይ መስመር ተጫዋቹ ወደ ቀደሞ ቡድኑ አምርቷል፡፡ በተጫዋቾች ዝውውር ላይ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘው የአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌው ሲዳማ ቡና ከደቂቃዎች በፊት ሙሉዓለም መስፍንን በሁለት ዓመት ውል አስፈርሟል። አምስተኛ ፈራሚ በመሆን ወደ ቀድሞ ክለቡ የተመለሰው የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አርባምንጭ ከተማን ከለቀቀ በኃላ ከዚህ ቀደም ወደ ሲዳማ ቡና በማምራት ለሁለት ዓመታት የቻለዝርዝር

ዘንድሮ ከቀደመው ጊዜያት ተዳክሞ የቀረበው ቡድናቸውን ለማጠናከር በዝውውር መስኮቱ ጠንካራ ሥራዎችን እየሰሩ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች የተከላካይ መስመር ተጫዋቾች አስፈርመዋል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና፣ መከላከያ፣ አዳማ ከተማ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በሀዲያ ሆሳዕና ያሳለፈው ተስፋዬ በቀለ የቡድኑ አራተኛ ፈራሚ ሆኖ ቡድኑን ተቀላቅሏል። የተጫዋቹ መፈረምም በቀላሉ ግብ ያስተናግድ ለነበረው የሲዳማዝርዝር

ከሁለት ቀናት በፊት ቡድኑን ለማጠናከር ወደ ዝውውር ገበያው ጎራ ያለው ሲዳማ ቡና ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡ የአሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌን ውል ለማራዘም በሒደት ላይ የሚገኘው ክለቡ ከሁለት ቀናት በፊት ወደ ተጫዋች ዝውውር ገበያው በመግባት ግብ ጠባቂው ተክለማሪያም ሻንቆን በሁለት ዓመት ውል ወደ ክለቡ ያመጣ ሲሆን አሁን ደግሞ የትግራይ ክልል ክለቦችዝርዝር

በዘንድሮ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላለመውረድ ሲፎካከር የነበረው ሲዳማ ቡና በቀጣይ ዓመት ተጠናክሮ ለመቅረብ በዝውውር ገበያው ላይ ተሳትፎ ማድረግ ጀምሯል። የ2013 ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመንን በአስቸጋሪ ሁኔታ አሳልፎ ከመውረድ በመጨረሻዎቹ የሊጉ ሳምንታት የተረፈው ሲዳማ ቡና ለቀጣዩ የ2014 የውድድር ዘመን ጠንካራ እንዲሁም የዋንጫ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት የአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌንዝርዝር

የሲዳማ ቡናን ደካማ የውድድር ዓመት ጉዞ መቀልበስ ከቻሉ ዋና ተጫዋቾች መካከል አንዱ ከሆነው ኦኪኪ አፎላቢ ጋር ቆይታ አድርገናል። በሀገራችን እግርኳስ የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾች ተሳትፎ በብዛት መታየት ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል። በሊጉ ለሌሎች ዜጎች የተሰላፊነት ዕድል መስጠቱ የሀገሪቷን ወጣቶች ዕድል ከመሻማቱ አንፃር ሲተች በተሻለ የብቃት ደረጃ ላይ ያሉ ተጫዋቾችን ከውጪዝርዝር

አምስት ግቦች ከተስተናገዱበት ጨዋታ በኋላ ሱፐር ስፖርት ከአሠልጣኞች አስተያየት ተቀብሏል። ገብረመድኅን ኃይሌ – ሲዳማ ቡና ስለ ጨዋታው? በጨዋታው ብልጫ እንደሚኖረን አስቤ ነበር። በዚህ ጨዋታ ሁሉንም ነገር ማጠናቀቅ ነበረብን። ጎልም ያስፈልገን ነበር። ሲዳማ ያለፉትን አስር ጨዋተዎች ጥሩ አመጣት ነው የመጣው። ዛሬ ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት ብቻ ሳይሆን ቡድኑ ምን እንደሚመስልም ማሳየት ነበርዝርዝር

ሦስተኛውን ወራጅ ቡድን ሊጠቁም የሚችለውን ጨዋታ በዳሰሳችን ተመልክተነዋል። ይህ ጨዋታ ለጅማ አባ ጅፋር የመርሐ ግብር ማሟያ ቢሆንም ለሲዳማ ቡና ግን እጅግ አስፈላጊ ነው። ቡድኑ ከዚህ ጨዋታ አንድ ነጥብ ብቻ ማግኘት ከቻለ ለከርሞው በሊጉ መቆየቱን ማረጋገጥ ሲችል ወልቂጤ ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ዕውን ይሆናል። በመሆኑም ተጠባቂነቱ ከጅማ ይልቅ ለወልቂጤ ያደላዝርዝር